.የኢሳት አማርኛ ዜና

ዶክተር መረራ ጉዲና ከወህኒ ወጡ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 9/2010) የኦፌኮ ሊቀመንበር ዶክተር መረራ ጉዲና ዛሬ ከወህኒ ወጡ። ከሳቸው ሌላ በፖለቲካ ምክንያት የታሰሩ ሌሎች ታዋቂ ሰዎች ግን አልተፈቱም። ዶክተር መረራ እንዲፈቱ ተወስኖ ክሱ ከተቋረጠ በኋላ የመንግስት ቃል አቀባዩ ዶክተር ነገሬ ሌንጮ ትላንት በሰጡት መግልጫ የዶክተር መረራ ጉዲና ጉዳይ ውሳኔ የሚያገኘው በሁለት ወራት ጊዜ ውስጥ ነው ማለታቸው ይታወሳል። የህወሃት ንብረት የሆነው ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከልም በተመሳሳይ አይፈቱም የሚል ዘገባ ...

Read More »

ግብጽ ከሱዳንም ሆነ ከኢትዮጵያ ጋር ጦርነት አልፈልግም አለች

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 8/2010) የግብጹ ፕሬዝዳንት ጄኔራል አብዱልፈታህ አልሲሲ ከሱዳንም ሆነ ከኢትዮጵያ ጋር ጦርነት አንፈግም አሉ። በአካባቢው የተፈጠረው ውጥረት እንዲረግብ ፍላጎታችን ነው ያሉት ፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ አልሲሲ ሀገራቸው በማንም ሀገር ጉዳይ ጣልቃ የመግባት ፍላጎት እንደሌላትም በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል። የሱዳን መንግስት በበኩሉ በግብጽና በኤርትራ መንግስት ላይ ያቀረበውን ክስ በመሳብ ጉዳዩን ከሱዳን መንግስት ተቃዋሚዎች ጋር አያይዞታል። የግብጹ ፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ አልሲሲ ከሀገራቸው ቴሌቪዥን ጋር ትላንት ...

Read More »

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን በዳላስ አይሮፕላን ማረፊያ ለማረፍ ተገደደ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 8/2010) ሰኞ ረፋድ ላይ ከዋሽንግተን ዲሲ ወደ ኢትዮጵያ ይበር የነበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን በተፈጠረበት የቴክኒክ ችግር በዳላስ አይሮፕላን ማረፊያ ለማረፍ መገደዱ ተሰማ። በተሳፋሪውም ሆነ በአውሮፕላኑ ሰራተኞች ላይ ምንም ጉዳት ሳይደርስ አውሮፕላኑ በሰላም ማረፉም ታውቋል። ተሳፋሪዎቹን ሆቴል ያሳደረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዛሬ የአውሮፕላን ጥገናውን ጨርሶ ጉዞውን ይቀጥላል ተብሎ ይጠበቃል። የበረራ ቁጥር 501 ቦይንግ 777-300 የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ...

Read More »

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የ2018 ተሸላሚ ሆነ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 8/2010) ታዋቂው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ሁለት አለም አቀፍ ተቋማት በጋራ የ2018 ተሸላሚ አድርገው መረጡት። የሽልማት ስነስርአቱ ከነገ በስትያ በኔዘርላንድ ዘሄግ በከፍተኛ ስነስርአት የሚካሄድ መሆኑ ታውቋል። በስነስርአቱ ላይ የከተማዋ ከንቲባ እንደሚገኙም ከወጣው መርሃ ግብር መረዳት ተችሏል። በአለም አቀፍ ተቋማት ከፍተኛ አክብሮት እየተቸረውና ሽልማት እየተጎናጸፈ የሚገኘው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ በአሁኑ ወቅት በቃሊቲ ወህኒ ቤት የ18 አመታት እስር ተፈርዶበት ይገኛል። ኦክስፋም ...

Read More »

ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ለአለም ጤና ድርጅት ራስ ምታት ሆነዋል ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 8/2010) ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ለአለም ጤና ድርጅት ራስ ምታት ሆነው መቀጠላቸውን ዘገባዎች አመለከቱ። የቀድሞውን የዚምባቡዌ ፕሬዝዳንት ሮበርት ሙጋቤን የአለም ጤና ድርጅት የበጎ ፈቃድ አምባሳደር በሚል በመሾማቸው ከፍተኛ ተቃውሞ ደርሶባቸው ውሳኔውን መሰረዛቸው ይታወሳል። አሁን ደግሞ ምንም እውቅናና ችሎታ የሌላቸውን ሩሲያዊ ባለስልጣን የአለም ጤና ድርጅት የሳምባ በሽታ ፕሮግራምን እንዲመሩ በመወሰናቸው ከቀድሞው በባሰ እየተብጠለጠሉ መሆኑ ታውቋል። ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ለአለም ጤና ...

Read More »

ህወሃት በክልሉና በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ እየተወያየ ነው

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 8/2010) ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ህወሃት በክልሉና በሀገራዊ ጉዳዮች እየተወያየ መሆኑን አስታወቀ። ሀገሪቱን ስጋት ላይ የጣሉ አመራሮች ላይም ርምጃ እንደሚወሰድም አስታውቋል። የህወሀት የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል አቶ ጌታቸው ረዳ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ የትግራይ ህዝብ በአመራሮቹ ላይ ጥርጣሬ እንዲያድርበት ተደርጓል ሲሉም በስም ያልጠቀሷቸውን አመራሮች ተጠያቂ አድርገዋል። የህወሀት 7ኛው ድርጅታዊ ጉባዔ ከተጀመረ አንድ ሳምንቱን አጠናቋል። ከመላው ዓለም የህወሃት ደጋፊዎችና ...

Read More »

የፖለቲካ እስረኞች አፈታት አፈጻጸሙ አጠራጣሪ ነው ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 8/2010) የፖለቲካ እስረኞች በምህረት ሳይሆን በይቅርታ ህጉ መሰረት ሊፈቱ እንደሚችሉ በፌደራሉ ዋና አቃቢ ህግ መገለጹ አፈጻጸሙን አጠራጣሪ ማድረጉን ታዛቢዎች ገለጹ። ዋና አቃቢ ሕጉ አቶ ጌታቸው አምባዬ ከዚህ ቀደም እስረኞች በምህረት ይለቀቃሉ በሚል በጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ የተገለጸውን በመቃረን መግለጫ ሰጥተዋል። ታዛቢዎች እንደሚሉት በአቶ ጌታቸው መግለጫ መሰረት እስረኞቹ ይቅርታ ካልጠየቁ ሊፈቱ የሚችሉበት ሁኔታም አይኖርም። በኢትዮጵያ የእስረኞች አፈታት ህግ መሰረት ...

Read More »

ሱዳን ተጨማሪ ወታደሮቿን ወደ ኤርትራ ድንበር አስጠጋች

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 7/2010) ከግብጽ ጋር ውዝግብ ውስጥ የገባችው ሱዳን ተጨማሪ ወታደሮቿን ወደ ኤርትራ ድንበር ከሰላ ማስጠጋቷን የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ። ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ወርቅነህ ገበየሁ ጋር ትላንት በሱዳን ካርቱም የተገናኙት የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኢብራሂም ጋንዱር ርምጃውን የወሰድነው በደረሰን መረጃ ላይ ተመስርተን ነው ብለዋል። በወሩ መጀመሪያ ላይ ከኤርትራ ጋር የሚያዋስናትን ድንበር ሙሉ በሙሉ የዘጋችው ሱዳን ቀደም ሲል በሺዎች የሚቆጠሩ ...

Read More »

አራት የመከላከያ ሰራዊት አባላት ተገደሉ 10 ቆሰሉ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 7/2010) የአርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ ታጣቂዎች አራት የመከላከያ ሰራዊት አባላትን መግደላቸውንና 10 ማቁሰላቸው ተገለጸ። ዛሬ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎት በ14 የፖለቲካ እስረኞች ላይ የጥፋተኝነት ብይን ተሰቷል። በችሎቱ እንደተገለጸውም የንቅናቄው ታጣቂዎች በ2007 በሁመራ በኩል በመግባት በሰነዘሩት ጥቃት የመንግስት ወታደሮች ላይ ጉዳት አድርሰዋል። ፍርድ ቤቱ ተከሳሾቹ እንዲከላከሉም ውሳኔ አሳልፏል። በኢትዮጵያ አቆጣጠር ከሰኔ 25 እስከ ሰኔ ...

Read More »

የፋሲል ከነማ ደጋፊዎች ታሰሩ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 7/2010) በአዲስ አበባ ከተማ በርካታ የፋሲል ከነማ ደጋፊዎች መታሰራቸው ተገለጸ። ትላንት በአዲስ አበባ ስታዲየም የተደረገውን የመቀሌ ከነማና የፋሲል ከነማ የእግር ኳስ ግጥሚያን ተከትሎ በተነሳ ተቃውሞ የፋሲል ከነማ ደጋፊዎች ከባድ ድብደባ እንደደረሰባቸው ታውቋል። ለጊዜው ቁጥራቸው ያልታወቀ ደጋፊዎችም ታፍሰው መታሰራቸውን መረጃዎች አመልክተዋል። በተለያዩ የአዲስ አበባ እስር ቤቶች የሚገኙት ደጋፊዎች ፍርድ ቤት ይቀርባሉ ተብሎም እየተጠበቀ ነው። የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ወደ አዲስ ...

Read More »