(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 2/2010) የቀድሞው የቻድ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሀብሬ የዘረፉትን ገንዘብ ለማስመለስ የአፍሪካ ህብረት ጥረት መጀመሩ ታወቀ። በእርሳቸው የስልጣን ዘመን ለተገደሉና ለተሰቃዩ ሰለባዎች ማቋቋሚያ ከቀድሞ አምባገንን መሪ እንዲከፈል መወሰኑም ታውቋል። ገንዘቡ ገቢ ባለመሆኑም ሀሰን ሀብሬን ወደ ስልጣን እንዲወጡ ያገዙት ፈረንሳይና አሜሪካም ለማቋቋሚያ የገንዘብ ድጋፍ እንዲያደረጉ እየተጠየቁ መሆኑን መረጃዎች አመልክተዋል። በሴኔጋል ዳካር ያለጠያቂ ለ25 አመታት ያህል በተንደላቀቀ ሕይወት የቆዩት ሀሰን ሃብሬ ሰለባዎቹ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
ሕወሃት የንጹሃንን ደም ከማፍሰስ እንዲቆጠብ ተጠየቀ
(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 2/2010) በኢትዮጵያ በስልጣን ላይ ያለው መንግስት የንጹሃንን ደም ከማፍሰስ ድርጊቱ እንዲቆጠብ እንዲሁም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አንድነት እንዳይመጣ መሰናክል ከመሆን እንዲታቀብ ብጹእ አቡነ ኤዎስጣጤዎስ ጥሪ አቀረቡ። የመከላከያ ሰራዊት አባላትም ተግባራቸው የውጭ ወራሪን መመከት እንጂ ወገንን መግደል እንዳልሆነም መገንዘብ ይኖርባቸዋል ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የካሊፎርኒያ ሊቀጳጳስ የነበሩትና በአሁኑ ወቅት በዋሽንግተን ሲያትል ከተማ የሚያገለግሉት ብጹእ ዶክተር አቡነ ...
Read More »የባህርዳር እግር ኳስ ቡድን ደጋፊዎችን በመለየት የእስር ርምጃ ሊወሰድ ነው
(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 2/2010) በአማራ ክልል የባህርዳር እግር ኳስ ቡድን ደጋፊዎችን በመለየት የእስር ርምጃ ሊወሰድ መሆኑን የኢሳት የመረጃ ምንጮች ገለጹ። የእስር ርምጃውን ለመውሰድ ወሳኔ ላይ የተደረሰው በከተማዋ ያለውን ተቃውሞ የሚያንቀሳቅሱት የባህርዳር ከነማ ደጋፊዎች ናቸው የሚል የደሕንነት መረጃ በመቅረቡ ነው። በጉዳዩ ላይ ከብሔራዊ መረጃና ደህንነት፥ ከመከላከያ መረጃ ክፍል፥ ከአድማ ብተና እና ከመደበኛ ፖሊስ የተውጣጡ ሃላፊዎች በክልሉ ርእሰ መስተዳድር ጽህፈት ቤት ምክክር አድርገዋል። ...
Read More »ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋና ታዋቂው ፖለቲከኛ አንዱአለም አራጌ ላይፈቱ ይችላሉ ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 2/2010) ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋና ታዋቂው ፖለቲከኛ አንዱአለም አራጌ የይቅርታ ሰነድ አንፈርምም በማለታቸው ከእርስ ላይለቀቁ ይችላሉ ተባለ። ሁለቱም እስረኞች የአርበኞች ግንበት 7 አባል ነን ብላችሁ ፈርሙ ተብለው በሌለንበት ነገር አንፈርምም፣ያጠፋነውም ነገር ስለሌለ ይቅርታ አንጠይቅም ብለዋል። ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች እንደገለጹት በእስርቤቱ ሃላፊዎችና በጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እንዲሁም በታዋቂው ፖለቲከኛ አንዷለም አራጌ መካከል አለመግባባት ተፈጥሯል። ችግሩ ደግሞ ሁለቱም እስረኞች ይቅርታ ...
Read More »ወደ ባህር ከተጣሉ ኢትዮጵያውያን 25ቱ መጥፋታቸው ታወቀ
(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 2/2010) ወደ ባህር ከተጣሉ ኢትዮጵያውያን 25ቱን ማግኘት እንዳልተቻለ የመንግስታቱ ድርጅት የስደተኞች ጽ/ቤት አስታወቀ። በ4 ጀልባዎች ተጭነው ትላንት ወደ የመን እየተጓዙ ከነበሩትና በዋና እንዲሻገሩ ከተገደዱት ስደተኞች መካከል 25ቱ ኢትዮጵያውያን እስከዛሬ ድረስ ሊገኙ እንዳልቻሉ ጽ/ቤቱ ገልጿል። በሌላ ዜና ሞዛምቢክ 50 ኢትዮጵያውያንን ማባረሯ ታውቋል። ኢትዮጵያውያኑ በዓለም ዓቀፉ የስደተኞች ድርጅት ትብብር ወደ ኢትዮጵያ መላካቸው ተገልጿል። 600 የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በ4ቱ ጀልባዎች ተሳፍረው ...
Read More »የጁባ መንግስት በዋሽንግተን የሚገኙትን አምባሳደሩን ጠራ
(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 1/2010) አሜሪካ በደቡብ ሱዳን መንግስት ላይ የጣለችውን የጦር መሳሪያ ማዕቀብ ተከትሎ የጁባ መንግስት በዋሽንግተን የሚገኙትን አምባሳደሩን መጥራቱ ተሰማ። በዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካና በደቡብ ሱዳን መካከል ዲፕሎማሲያዊ ውዝግብ ያስከተለው የጦር መሳሪያ ማዕቀብ በደቡብ ሱዳን ያለውን ችግር ለመቀነስ አስተዋጽኦ እንደሚኖረውም ተመልክቷል። አሜሪካ በደቡብ ሱዳን ያለውን ቀውስ ለመፍታት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በደቡብ ሱዳን መንግስት ላይ የጦር መሳሪያ ማዕቀብ እንዲጥል በወሩ መጀመሪያ ...
Read More »የወልቃይት አማራ ማንነት ኮሚቴ አባላት ከፍተኛ ስቃይ እየተፈጸመባቸው ነው
(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 1/2010) በእስር ላይ የሚገኙት የወልቃይት አማራ ማንነት ኮሚቴ አባላት ከፍተኛ ስቃይ እየተፈጸመባቸው መሆኑን ለፍርድ ቤት ገለጹ። ችሎት ቀርበው የደረሰባቸውን በደልና ስቃይ የገለጹት የኮሚቴው አባላት በቀል እየተፈጸመብን ነው ሲሉም ተናግረዋል። በወልቃይት ጉዳይ በአደባባይ አቋማቸውን ያሳወቁትን ዳኛ ዘርአይ ወልደሰበትን በመቃወሜ ከህዳር 26 ጀምሮ ከ2 ወራት በላይ በጨለማ ቤት ታስሬ እገኛለሁ ሲሉ የኮሚቴው አባል የሆኑት አቶ መብራቱ ጌታሁን ለችሎቱ ገልጸዋል። በዛሬው ...
Read More »ለያያ ማዳበሪያ ፋብሪካ ተጨማሪ 9 ቢሊየን ብር ተጠየቀ
(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 1/2010) ሜቴክ ያያ ማዳበሪያ ፋብሪካን ሰርቶ ለማጠናቀቅ ተጨማሪ 9 ቢሊየን ብር እንዲከፈለው ጠየቀ። ማዳባሪያ ፋብሪካው ተሰርቶ መጠናቀቅ የነበረበት ከ6 አመት በፊት እንደነበር መረጃዎች ያመለክታሉ። በሕወሃት ጄኔራሎች የሚመራው የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን /ሜቴክ/ከያዛቸው ግዙፍ ፕሮጀክቶች መካከል ያያ ማዳበሪያ ፋብሪካ አንዱ ነው። ሜቴክ ማዳበሪያ ፋብሪካውን አጠናቆ ለመጨረስ የሚፈጅበት ሁለት አመት ብቻ እንደሆነና የፕሮጀክቱ ወጪም 11 ቢሊየን ብር እንደሆነ የገባው ውል ...
Read More »ኢትዮጵያ የኢንተርኔት አገልግሎትን በመገደብ ሁለተኛ ሆነች
(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 1/2010) ኢትዮጵያ የኢንተርኔት አገልግሎትን በመገደብ ከቻይና ቀጥሎ በአለም ሁለተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች መባሉን የሀገሪቱ አገዛዝ አስተባበለ። በሕወሃት የሚመራው አገዛዝ በኢትዮ ቴሌኮም በኩል በሰጠው መግለጫ ኢንተርኔት በኢትዮጵያ ተዘግቶ አያውቅም ሲል አስተባብሏል። ፍሪደም ሃውስ የተባለው አለም አቀፍ ድርጅት ሰሞኑን ኢትዮጵያ ኢንተርኔትን በማፈን ከአለም ከቻይና ቀጥሎ 2ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች የሚል ሪፖርት ማውጣቱ ይታወሳል። በፍሪደም ሃውስ ሪፖርት መሰረት ቻይና፣ ኢትዮጵያና ሶሪያ ...
Read More »ከ700 የሚበልጡ እስረኞች እንዲፈቱ ተወሰነ
(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 1/2010) ላለፉት 7 አመታት ያህል በወህኒ የቆዩት ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋና አቶ አንዱአለም አራጌን ጨምሮ ከ700 የሚበልጡ እስረኞች እንዲፈቱ መወሰኑን የመንግስትና የፓርቲ መገናኛ ብዙሃን ዘገቡ። ጠቅላይ አቃቢ ህግን ጠቅሰው መገናኛ ብዙሃኑ እንደዘገቡት በይቅርታና ክሳቸው ተቋርጦ እንዲፈቱ የተወሰነላቸው እስረኞች ቁጥር በአጠቃላይ 746 ናቸው። ከመስከረም 3/2004 ጀምሮ በወህኒ ቤት የሚገኙት ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋና አንዱአለም አራጌ ከተፈቺዎቹ ውስጥ በስም ተጠቅሰዋል። ነገር ግን ...
Read More »