የህወሃት ባለስልጣናት ከኦብነግ ጋር አደገኛ ድርድር እያደረጉ እንደሆነ ተገለጸ (ኢሳት ዜና የካቲት 9 ቀን 2010ዓ/ም) በኢትዮጵያ ሶማሊ ያለውን የፖለቲካ ሁኔታ በቅርብ የሚከታተለው የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ አቶ አብዱላሂ ሁሴን እንደገለጸው በናይሮቢ የሚደረገው ድርድር ከዚህ ቀደም ይደረጉ ከነበሩት ድርድሮች በይዘቱ የተለዬ ነው። ህወሃቶች ሞቃዲሾ ያሉ የሶማሊ መንግስት ባለስልጣናትንና በገንዘብ የገዙዋቸውን ሽማግሌዎች ናይሮቢ ጋብዘው ማምጣታቸውንና እነዚህ ሰዎች በኦብነግ ላይ ተጽዕኖ ፈጥረው ከሶማሊ ክልል ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
በኮንሶ የታሰሩ 52 ሰላማዊ ሰዎች አልተፈቱም ጋዜጣ አንብባችኋል የተባሉ ስድስት ሰዎች ታሰሩ
በኮንሶ የታሰሩ 52 ሰላማዊ ሰዎች አልተፈቱም ጋዜጣ አንብባችኋል የተባሉ ስድስት ሰዎች ታሰሩ (ኢሳት ዜና የካቲት 9 ቀን 2010ዓ/ም) በኮንሶ የማንነት ጥያቄ ማንሳታቸውን ተከትሎ በተነሳው ሕዝባዊ ተቃውሞ ምክንያት መብታቸውን የተየቁ የአካባቢው ተወላጆች በጅምላ መታሰራቸው ይታወሳል። በወቅቱ በተነሳው ግጭት ምክንያት አመጽ አነሳስታችኋል ተብለው በጅምላ ከታሰሩት ውስጥ 52 ሰላማዊ ሰልፈኞች በምህረት አዋጁ ይፈታሉ ተብሎ ቢጠበቅም እስካሁን አልተፈቱም። በጂንካ፣ ጉዶሌ፣ ደራሼና በተለያዩ ፖሊስ ጣቢያዎች ...
Read More »የ19 አመቱ ወጣት በ17 የተለያዩ ወንጀሎች ይጠየቃል ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 9/2010) በአሜሪካ ፍሎሪዳ ግዛት በአንድ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት 17 ተማሪዎችን የገደለው የ19 አመቱ ወጣት በ17 የተለያዩ ወንጀሎች እንደሚጠየቅ ተገለጸ። በማርጆሪ ስቶን ማን ዳግላስ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ተኩስ በመክፈት ግድያ የፈጸመው ወጣት ኒኮላስ ጃኮብ ክሩዝ የ49 አመቱን የትምህርት ቤቱን የአትሌቲክስ ዳይሬክተር ጨምሮ እድሜያቸው ከ15 እስከ 18 አመት የሆኑ ተማሪዎችን ገድሏል። በሀገሬው አቆጣጠር እንደ አውሮፓውያኑ ...
Read More »በኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ መዝገብ ላይ ብይን ይሰጣል ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 9/2010) የአማራ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጎንደር ምድብ ችሎት በኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ መዝገብ ላይ ብይን ለመስጠት የመጨረሻ ቀጠሮ መስጠቱ ተሰማ ። በጎንደር የተሰየመው ችሎት በኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ መዝገብ ላይ “የከላከሉ፣አይከላከሉ” በሚለው ጉዳይ ላይ ብይን ለመስጠት ቀጠሮ ይዞ እንደነበርም ታውቋል። በጎንደር ዛሬ የተሰየመው ችሎት በኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ የክስ መዝገብ ላይ ዐቃቤ ሕግ ያቀረበውን ማስረጃ ይመረምራል። መርምሮም “ይከላከሉ፣ አይከላከሉ” ...
Read More »የአሜሪካ ኤምባሲ የጉዞ ማስጠንቀቂያ አወጣ
(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 9/2010) በኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ የስልጣን መልቀቂያ ጥያቄ ማቅረባቸውን ተከትሎ በአዲስ አበባ የአሜሪካ ኤምባሲ የጉዞ ማስጠንቀቂያ አወጣ። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርም ተመሳሳይ መግለጫ ማውጣቱ ታውቋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በሀገሪቱ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ በኢትዮጵያ ለአሜሪካ አምባሳደር ማብራሪያ ሰጥተዋል። በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ ባወጣው የቅድመ ማስጠንቀቂያ መግለጫ ሰራተኞቹ ከአዲስ አበባ ውጪ በምንም አይነት መንቀሳቀስ አደገኛ ...
Read More »ሁለት የአገዛዙ የጸጥታ ሃይሎች ተገድለው ተገኙ
(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 9/2010) በባህር ዳር ሁለት የአገዛዙ የጸጥታ ሃይሎች ተገድለው ተገኙ። በደብረታቦር በውስጣዊ አሰራር የሰዓት እላፊ ቁጥጥር ተደርጓል። ከምሽቱ አንድ ሰዓት በኋላ የተገኘ ማንኛውም እግረኛና ተሽከርካሪ ፍተሻ እንደሚደረግለትም ታውቋል። በሌላ ዜና በመተሀራ ትላንት የቦንብ ጥቃት ተፈጽሟል ። በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች ዛሬም የተቃውሞ ሰልፎች ሲደረጉ እንደነበር የደረሰን መረጃ ይጠቁማል። ባህርዳር በዚህ ሳምንት በተለየ ወታደራዊ ጥበቃ ስር መቆየቷን ተከትሎ ትላንት ምሽት የተፈጸመው ...
Read More »በወልቂጤ ሁለት ሰዎች ተገደሉ
(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 9/2010) በወልቂጤ ለሶስተኛ ቀን በቀጠለው ተቃውሞ ሁለት ሰዎች ተገደሉ። በወልቂጤ የተጀመረው አድማና ተቃውሞ ወደ ሌሎች የጉራጌ ዞን ወረዳዎች መዛመቱ ታወቋል። ጉብሬና አገና በተባሉ አካባቢዎች ዛሬ ሙሉ በሙሉ የስራ ማቆም አድማ ተደጓል። የአገና ወራዳ ከተማ ህዝቡ አደባባይ ወጥቶ ተቃውሞ በማሰማት ላይ ነው ተብሏል። በእንድብር የልዩ ሃይል ሰራዊት ከተማዋን በመቆጣጠር የህዝቡን ተቃወሞ ለማፈን እየተንቀሳቀሰ መሆኑ ታወቋል። በወልቂጤ የጀመረው የጉራጌ አብዮት ...
Read More »ካለፉት 3 ዓመታት ጀምሮ በመካሄድ ላይ ያለውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ የስልጣን መልቀቂያ አቀረቡ
ካለፉት 3 ዓመታት ጀምሮ በመካሄድ ላይ ያለውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ የስልጣን መልቀቂያ አቀረቡ (ኢሳት ዜና የካቲት 8 ቀን 2010ዓ/ም) ጠ/ሚኒስትሩ የስልጣን መልቀቂያውን ያቀረቡት ዘላቂ ሰላም እንዲረጋገጥና ዋስት ያለው ዲሞክራሲ እንዲሰፍን የመፍትሄ አካል ለመሆን ነው ብለዋል። አቶ ሃይለማርያም በአገሪቱ በመካሄድ ላይ ባለው ተቃውሞ የበርካታ ዜጎች ህይወት መጥፋቱን፣ ንብረት መውደሙንና ኢንቨስትመንት መዳከሙን ገልጸዋል። ከኢህአዴግ ሊ/መንበርነታቸው ለመልቀቅ ያቀረቡትን ጥያቄ ድርጅታቸው ...
Read More »በጉራጌ ዞን በወልቂጤ ከተማ በተካሄደው ተቃውሞ የአንድ ሰው ህይወት ጠፋ
በጉራጌ ዞን በወልቂጤ ከተማ በተካሄደው ተቃውሞ የአንድ ሰው ህይወት ጠፋ (ኢሳት ዜና የካቲት 8 ቀን 2010ዓ/ም) ትናንት በስራ ማቆም አድማ የተጀመረው የወልቂጤ ተቃውሞ ዛሬ ወደ አደባባይ ተቃውሞ ተለውጡ በሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች ተቃውሟቸውን ሲያሰሙ ውለዋል። “ በኢህአዴግ መገዛት በቃን፣ የታሰሩት ይፈቱ፣ ለውጥ እንፈልጋለን” የሚሉና ሌሎችንም መፈክሮች አሰምተዋል። በተቃውሞው አንድ ሰው ሲገደል ሌሎች 3 ሰዎች ደግሞ በጽኑ ቆስለው ሆስፒታል ገብተዋል። 7 መኪኖች ...
Read More »ከእስር ቤት በግድ ተጎትተው መውጣታቸውን ወ/ሮ እማዋይሽ አለሙ ገለጹ
ከእስር ቤት በግድ ተጎትተው መውጣታቸውን ወ/ሮ እማዋይሽ አለሙ ገለጹ (ኢሳት ዜና የካቲት 8 ቀን 2010ዓ/ም) በመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ተከሰው ላለፉት 9 ዓመታት በእስር ያሳለፉት ወ/ሮ እማዋይሽ አለሙ በመፈታታቸው ብዙም የተሰማቸው የተለዬ ደስታ እንደሌለ ገልጸዋል። ልጆቻቸው አንደኛው በትግል ላይ ሌላኛዋ ደግሞ በስደት ላይ በመሆናቸው በአካል እንዳላገኙዋቸውም ተናግረዋል። “ብዙ ስቃይ ያዩት አባሪዎቼ በእስር ቤት ሆነው የእኔ መፈታት ምንም ደስታ አልሰጠኝም” ያሉት ወ/ሮ ...
Read More »