ካለፉት 3 ዓመታት ጀምሮ በመካሄድ ላይ ያለውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ የስልጣን መልቀቂያ አቀረቡ

ካለፉት 3 ዓመታት ጀምሮ በመካሄድ ላይ ያለውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ የስልጣን መልቀቂያ አቀረቡ
(ኢሳት ዜና የካቲት 8 ቀን 2010ዓ/ም) ጠ/ሚኒስትሩ የስልጣን መልቀቂያውን ያቀረቡት ዘላቂ ሰላም እንዲረጋገጥና ዋስት ያለው ዲሞክራሲ እንዲሰፍን የመፍትሄ አካል ለመሆን ነው ብለዋል።
አቶ ሃይለማርያም በአገሪቱ በመካሄድ ላይ ባለው ተቃውሞ የበርካታ ዜጎች ህይወት መጥፋቱን፣ ንብረት መውደሙንና ኢንቨስትመንት መዳከሙን ገልጸዋል። ከኢህአዴግ ሊ/መንበርነታቸው ለመልቀቅ ያቀረቡትን ጥያቄ ድርጅታቸው ደኢህዴን እንዲሁም የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ እንደተቀበለው የገለጹት አቶ ሃይለማርያም፣ የኢህአዴግ ምክር ቤት በሚያደርገው ስብሰባ የመጨረሻ ውሳኔ እንደሚሰጣቸው ተናግረዋል። የጠ/ሚኒስትርነቱን መልቀቂያም ፓርላማው እንደሚቀበለው አምናለሁ ብለዋል። የመጨረሻ ውሳኔ ሰጪው አካል ውሳኔውን እስከሚሰጥ ድረስ በሃላፊነት ቦታቸው ላይ እንደሚቆዩ አቶ ሃይለማርያም ተናግረዋል።
በአርሲ ነጌሌ እና በጅማ ዩኒቨርስቲ ቂጦ ግቢ የሚማሩ ተማሪዎች አቶ ሃይለማርያምን መልቀቅ እንደሰሙ ደስታውቸውን በጭፈራ ገልጸዋል።
ይህን ዜና ለማንበብ ስቱዲዮ በገባንበት ወቅት ለ3 ኛ ጊዜ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሊታወጅ መሆኑን አስተማማኝ መረጃ ደርሶናል።