.የኢሳት አማርኛ ዜና

የነዳጅ አቅርቦትን የማስተጓጎሉ ዘመቻ ተጀመረ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 4/2010) በቄሮዎች የተጠራው የነዳጅ አቅርቦትን የማስተጓጎል ዘመቻ ዛሬ ተጀመረ። ለአንድ ሳምንት የተጠራው ይህ ዘመቻ ነዳጅ የጫኑ ቦቴ ተሽከርካሪዎች ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ፣ በሀገር ውስጥም ከአንድ አካባቢ ወደሌላ እንዳያመላልሱ የሚያደርግ ነው። ዛሬ ዘመቻው ሲጀምር አዲስ አበባ ተጽዕኖው ጎልቶ ከታየባቸው አካባቢዎች የሚጠቀስ እንደሆነ መረጃዎች ያሳያሉ። በርካታ ማደያዎች ነዳጅ የላቸውም። በየቦታው ነዳጅ አመላላሽ ቦቴዎች ቆመው እንደሚታዩ የደረሰን መረጃ አመልክቷል። በሰሜን ኢትዮጵያ ...

Read More »

የባንግላዴሽ አይሮፕላን በካታማንዱ ተከሰከሰ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 3/2010) ንብረትነቱ የባንግላዴሽ አየር መንገድ የሆነ አውሮፕላን በኔፓል መዲና ካታማንዱ ተከሰከሰ። በትንሹ 40 ያህል መንገደኞችና የአውሮፕላኑ ሰራተኞች ሕይወታቸው አልፏል። አውሮፕላኑ የተከሰከሰው በማረፍ ላይ እያለ መሆኑም ታውቋል። ይህ በእንዲህ እንዳለም ትላንት ምሽት በኒዮርክ ከተማ አንድ ሔሊኮፕተር ተከስክሶ 5 ሰዎች ሞተዋል። ንብረትነቱ የባንግላዴሽ አየር መንገድ የሆነ ቦባርዲየር ዳሽ ኤይት የበረራ ቁጥር ቢኤስ 211 የሆነው አውሮፕላን ከባንግላዴሽ ዋና ከተማ ዳካ መነሳቱንም ...

Read More »

18 የፖለቲካና የሲቪክ ተቋማት በጋራ ለመስራት ተስማሙ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 3/2018) በአማራ ሕዝብ ስም የተደራጁ 18 የፖለቲካና የሲቪክ ተቋማት በጋራ ተደጋግፎ ለመስራትና በተቀናጀ መልኩ ለመታገል መስማማታቸውን ገለጹ። ይህንኑ ተግባራዊ ለማድረግም የአማራ ድርጅቶች አመራር ሰጭ አካል እንዲቋቋም በሜሪላንድ ሲሊቨር ስፕሪንግ ከየካቲት 30 እስከ መጋቢት 2 /2010 ባካሄዱት ዝግ ስብሰባ መወሰናቸውን ለኢሳት በላኩት መግለጫ አስታውቀዋል። በመግለጫው እንደተመለከተው የአማራ ሕዝብ ለሃገሩ ኢትዮጵያ ከፍተኛ ውለታ የከፈለ ቢሆንም በጨቋኝነት ተፈርጆ ከፍተኛ በደልና ግፍ ...

Read More »

በቂሊንጦ እስር ቤት ቃጠሎ የተከሰሱት ሰዎች የፍርድ ውሳኔ ተላለፈ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 3/2010) በቂሊንጦ እስር ቤት ቃጠሎ የተከሰሱት የ38ቱ ሰዎች የፍርድ ውሳኔ ለሌላ ጊዜ ተላለፈ። ፍርድ ቤቱ ውሳኔውን ለሌላ ጊዜ ያስተላለፈው በስራ መብዛት እና ሰንዶችን መርምሬ ባለመጨረሴ ነው ብሏል። በእነ ማስረሻ ሰጤ መዝገብ ዶክተር ፍቅሩ ማሩን ጨምሮ 38 ተከሳሾች በፍርድቤቱ ቀነ ቀጠሮ መራዘም ያላቸውን ቅሬታ መግለጻቸው ተነግሯል። በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት በቂሊንጦ እስር ቤት ቃጠሎ የተከሰሱ ሰዎችን ...

Read More »

የነዳጅ አቅርቦትን ለማስተጓጎል የታቀደው ዘመቻ ነገ ይጀመራል ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 3/2010) በቄሮ የተጠራውና የነዳጅ አቅርቦትን ለማስተጓጎል የታቀደው ዘመቻ ከነገ ጀምሮ እንደሚካሄድ ተገለጸ። ለአንድ ሳምንት በሚካሄደው በዚሁ ዘመቻ ቦቴዎች ከውጭ ሃገር ነዳጅ ጭነው ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ ይደረጋል። በሃገር ውስጥም ነዳጅ ጭነው ከቦታ ቦታ የሚንቀሳቀሱ ተሽከርካሪዎች ርምጃ ይወሰድባቸዋል ተብሏል። ዘመቻው የሚጀመረው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ተግባራዊ ከተደረገ ወዲህ በርካታ ሰዎች በመገደላቸው ነው። በቄሮ የተጠራው የነዳጅ አቅርቦትን የማስተጓጎል ዘመቻ ከነገ ጀምሮ ...

Read More »

ወደ ኬንያ የገቡ ኢትዮጵያውያን ቁጥር 50 ሺህ ደረሰ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 3/2010) በሞያሌ እየተፈጸመ ያለውን ጭፍጨፋ በመሸሽ ኬኒያ የገቡ ኢትዮጵያውያን ቁጥር 50 ሺህ መድረሱ ተገለጸ። የአጋዚ ወታደሮች የሚፈጽሙት ግድያም ቀጥሏል። ወደ ኬኒያ በሽሽት ላይ በነበሩ የሞያሌ ከተማ ነዋሪዎች ላይ ትላንት ተኩስ የከፈተው የአጋዚ ሃይል 2 ሰዎች መግደሉን የደረሰን መረጃ አመልክቷል። በሌላ በኩል የሞያሌው ጭፍጨፋ በስህተት የተፈጸመ ነው የሚለው የአገዛዙ መግለጫ ቁጣን ቀስቅሷል። ቅዳሜ  ለሞያሌ ነዋሪዎች ጥሩ ቀን አልነበረም። በጠዋት ...

Read More »

በሞያሌ ከተማ ዛሬም ግድያ አለመቆሙን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ

በሞያሌ ከተማ ዛሬም ግድያ አለመቆሙን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ (ኢሳት ዜና ማጋቢት 03 ቀን 2010 ዓ/ም) ባለፈው ቅዳሜ በሞያሌ ከተማ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ከ13 ሰዎች በላይ መግደላቸውን ተከትሎ ግድያውና ውጥረቱ አሁንም ድረስ ያለ መሆኑን ነዋሪዎች ተናግረዋል። ትናንት ምሽት አንድ የኮንሶ ብሄረሰብ ተወላጅ ሌሊት ላይ በ10 ጥይቶች ተደብድቦ ተገድሎአል። አንድ የምዕራብ ጉጂ አካባቢ ተወላጅ የሆነ ወጣት ደግሞ በ 2 ጥይቶች ተመትቶ ቆስሏል። ...

Read More »

በርካታ ባለስልጣናት ሰዎችን በመኪና ገጭተው ቢገድሉም እስካሁን ለፍርድ አልቀረቡም

በርካታ ባለስልጣናት ሰዎችን በመኪና ገጭተው ቢገድሉም እስካሁን ለፍርድ አልቀረቡም (ኢሳት ዜና ማጋቢት 03 ቀን 2010 ዓ/ም) የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት የአገዛዙ ባለስልጣናት ሰዎችን በመኪና እየገጩ ቢገድሉም እስከዛሬ ግን ለፍርድ ቀርበው ሲቀጡ አልታዬም። ወብሸት ገብረ-እግዚአብሄር የተባለው የኢህአዴግ ወጣቶች ሊግ መስራችና የአዲስ አበባ ወጣቶች ሊግ ሰብሳቢ የነበረና በልደታና ቂርቆስ ክፍለ ከተሞች ኢህአዴግ ጽ/ቤት ሃላፊ አንድ በድህነት ውስጥ የሚገኙ እናት በመኪና ገጭቶ ቢገድልም ፣ ...

Read More »

አዲ ረመጥ በሚገኘው ሱር ኮንስትራክሽን ላይ የቦንብ ጥቃት ተፈጸመ

አዲ ረመጥ በሚገኘው ሱር ኮንስትራክሽን ላይ የቦንብ ጥቃት ተፈጸመ (ኢሳት ዜና ማጋቢት 03 ቀን 2010 ዓ/ም) የአካባቢው ምንጮች በፎቶ ግራፍ አስደግፈው በላኩልን መረጃ ባለፈው አርብ አዲ ረመጥ ላይ በሚገኘውና የህወሃት ንብረት በሆነው ሱር ኮንትስራክሽ ኩባንያ ንብረት ላይ ከሌሊቱ 7 ሰዓት ላይ የቦንብ ጥቃት ተፈጽሞ በንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል። ጥቃቱ የደረሰው የሱር አማካሪ በሆነው ልደት ኮንሳልታንት የግል ድርጅት ላይ መሆኑን የአካባቢው ...

Read More »

በነ መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤ መዝገብ የተከሰሱት ተከሳሾች “ ትገደላላችሁ” የሚል ዛቻ እንደደረሰባቸው ተናገሩ

በነ መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤ መዝገብ የተከሰሱት ተከሳሾች “ ትገደላላችሁ” የሚል ዛቻ እንደደረሰባቸው ተናገሩ (ኢሳት ዜና ማጋቢት 03 ቀን 2010 ዓ/ም) ችሎቱ የተሰየመው በአቃቢ ህግ ምስክር ላይ ብይን ለመስጠት የነበረ ቢሆንም፣ “ባለው የስራ ሂደትና መዝገቡ ሰፊ ስለሆነ፣ ለዛሬ ሊደርስልን አልቻለም፣ ስለሆነም ለመጨረሻ ግዜ አንድ ቀጠሮ መስጠት ግድ ሆኖብናል” በማለት መሃል ዳኛው ተናግረዋል። ጠበቆች “እስረኞቹ ያሉበትን ሁኔታ ግንዛቤ ውስጥ አስገብታችሁ አጭር ...

Read More »