.የኢሳት አማርኛ ዜና

በአዲስ አበባ ከተማ በአንድ ሳምንት ውስጥ ከፍተኛ የሆነ የዋጋ ጭማሪ በመፈጠሩ ሸማቾች መቸገራቸውን ተናገሩ

በአዲስ አበባ ከተማ በአንድ ሳምንት ውስጥ ከፍተኛ የሆነ የዋጋ ጭማሪ በመፈጠሩ ሸማቾች መቸገራቸውን ተናገሩ (ኢሳት ዜና ማጋቢት 06 ቀን 2010 ዓ/ም) ላለፉት ሶስት ዓመታት አገዛዙን በማውገዝ የተነሳውን ሕዝባዊ እምቢተኝነት ተከትሎ በመላው አገሪቱ የዋጋ ጭማሪና የኑሮ ውድነት በከፋ ሁኔታ እየተባባሰ መጥቷል። በተለይም መዲናዋ አዲስ አበባ በአንድ ሳምንት ውስጥ ብቻ በሸቀጦች ላይ እጥፍ የዋጋ ጭማሪና የገበያ መቀዛቀዝ መፈጠሩን የገዥው ፓርቲ ልሳን የሆነው ...

Read More »

የነዳጅ አቅርቦት እቅባን ተከትሎ ወታደሮች የነዳጅ ቦቴዎችን ለማጀብ ተገደዋል

የነዳጅ አቅርቦት እቅባን ተከትሎ ወታደሮች የነዳጅ ቦቴዎችን ለማጀብ ተገደዋል (ኢሳት ዜና ማጋቢት 05 ቀን 2010 ዓ/ም) ቄሮ የጠራው የነዳጅ አቅርቦትን የማስተጓጎል አድማ አጠቃላይ የነዳጅ አቅርቦቱን እንቅስቃሴ እንደገታው የሚደርሱን መረጃዎች ያመለክታሉ። በአሁኑ ሰዓት ነዳጅ ከጅቡቲም ሆነ ከሱዳን ወደ ኢትዮጵያ ለማጓጓዝ የሚደፍሩ ሾፌሮች በመጥፋታቸው ወታደሮች መኪኖችን አጅበው ለማስገባት ሙከራ ቢያደርጉም፣ ዛሬም እንቅስቃሴው ተስተጓጉሎ መዋሉን የደረሰን መረጃ ያመለክታል። በአዲስ አበባ ዛሬም የነዳጅ እጥረት ...

Read More »

ወደ ኬንያ የተሰደዱ በሺህዎች የሚቆጠሩ የኢትዮጵያ ሞያሌ ነዋሪዎች በወታደሮች የደረሰባቸውን ግፍ ተናገሩ

ወደ ኬንያ የተሰደዱ በሺህዎች የሚቆጠሩ የኢትዮጵያ ሞያሌ ነዋሪዎች በወታደሮች የደረሰባቸውን ግፍ ተናገሩ (ኢሳት ዜና ማጋቢት 05 ቀን 2010 ዓ/ም) እንደ ኬንያው ኔሽን ዘገባ ከ8ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ትናንት ማክሰኞ ማርሳቢት ተብላ በምትጠራው የኬንያ ከተማ የገቡ ሲሆን፣ ከመኖሪያ ቤታቸው ተገደው እንዲወጡ መደረግን ጨምሮ በወታደሮች የተፈጸመባቸውን ግፍ ተናግረዋል። መንግስታቸው በንጹሀን ዜጎች ላይ ወታደራዊ እርምጃ መውሰድ በመጀመሩ ሀገራቸውን ለመልቀቅ መገደዳቸውን ነዋሪዎቹ ገልጸዋል። ኮማንድ ...

Read More »

በሽንሌ ዞን የትጥቅ ትግል እንቅስቃሴ ተጀምሯል በሚል ወጣቶች ተይዘው ታሰሩ

በሽንሌ ዞን የትጥቅ ትግል እንቅስቃሴ ተጀምሯል በሚል ወጣቶች ተይዘው ታሰሩ (ኢሳት ዜና ማጋቢት 05 ቀን 2010 ዓ/ም) ምንጮች እንደገለጹት በሶማሊ ክልል በሺኒሌ ዞን የትጥቅ ትግል እንቅስቃሴ የተጀመረ ሲሆን፣ ይህንን ተከትሎ የተወሰኑ ወጣቶች ተይዘው ታስረዋል። 90 በመቶ የሚሆነው የአገሪቱ የወጪ ንግድ በዚህ አቅጣጫ የሚካሄድ በመሆኑ ፣ በአካባቢው የሚካሄደው ትግል በአገሪቱ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ላይ ተጽዕኖ እንደሚፈጠር ከጉዳዩ ጋር ቅርበት ያላቸው ምንጮች ይገልጻሉ። ...

Read More »

በአዲስ አበባ ብቻ ዋጋ ጨምራችሁዋል በሚል ከ 4 ሺ በላይ ሱቆች ታሸጉ

በአዲስ አበባ ብቻ ዋጋ ጨምራችሁዋል በሚል ከ 4 ሺ በላይ ሱቆች ታሸጉ (ኢሳት ዜና ማጋቢት 05 ቀን 2010 ዓ/ም) የአዲስ አበባ መስተዳደር ንግድ ቢሮ ምክትል ኃላፊን ጠቅሶ ሪፖርተር እንደዘገበው የዋጋ ጭማሪ አድርገዋል የተባሉ 4 ሺ 22 ሱቆች የታሸጉ ሲሆን፣ 7 ሺ ሱቆች የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ፣ 8 ሺ የሚሆኑት ደግሞ የቃል ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል። የዋጋ ጭማሪው ከውጭ ምንዛሬ እጥረትና ከአቅርቦት እጥረት ጋር የተያያዘ ...

Read More »

ፕሮፌሰር ስቴፈን ሆውኪንግ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 5/2010) ታዋቂው ሳይንቲስት ፕሮፌሰር ስቴፈን ሆውኪንግ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። በወጣትነት ዕድሜያቸው በደረሰባቸው አደጋ በህይወት የሚቆዩት ለሁለት ዓመታት ብቻ እንደሆነ ቢነገራቸውም ታላላቅ ሳይንሳዊ ግኝቶችን ለዓለም እያበረከቱ ተጨማሪ 50 ዓመታትን በዚህች መድር ላይ የኖሩት ስቴፈን ሃውኪንግ ረቡዕ ማለዳ በካምብሪጅ ብሪታኒያ በ76 ዓመታቸው በመኖሪያ ቤታቸው ህይወታቸው አልፏል። የዘመናችን ምርጥ ሳይንቲስት እና የምጡቅ አእምሮ ባለቤት እንደሆኑ የተመሰከረላቸው ፕሮፌሰር ስቴፈን ሃውኪንግ የ22 ...

Read More »

የኢትዮጵያ የንግድ ሚዛን ጉድለት 14 ቢሊየን ደረሰ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 5/2010) የኢትዮጵያ የንግድ ሚዛን ጉድለት 14 ቢሊየን ዶላር ደረሰ። የብር ምንዛሪ ለውጡ የወጪ ንግዱ ላይ ያመጣው ለውጥ የለም ሲሉ የኢኮኖሚ ባለሙያዎች ገልጸዋል። የንግድ ሚኒስቴር የሕዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ወንድሙ ፍላቴ ለመንግስት እና ለፓርቲ ሚዲያዎች በሰጡት መግለጫ ኢትዮጵያ ወደ ውጭ ሃገራት ከምትልካቸው የግብርና ምርቶች 3 ቢሊየን ዶላር ገቢ ብታገኝም ወደ ሃገር ውስጥ በምታስገባቸው ምርቶች ከ17 ቢሊየን ዶላር በላይ ወጪ ...

Read More »

የስዊዲን መንግስት የኢትዮጵያን አምባሳደር ጠርቶ አነጋገረ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 5/2010) የስዊዲን መንግስት የኢትዮጵያን አምባሳደር ጠርቶ ማነጋገሩ ተገለጸ። የስዊዲን የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት አምባሳደሩን የጠራው በቂሊንጦ እስር ቤት በሚገኙት በዶክተር ፍቅሩ ማሩ ጉዳይ ላይ ለማነጋገር መሆኑን የስዊዲን ጋዜጦች ዘግበዋል። በስዊዲን የኢትዮጵያ አምባሳደር ፕሮፌሰር መርጋ በቃና ስለተጓተተው የዶክተር ፍቅሩ ማሩ የፍርድ ቤት ጉዳይ ቀርበው እንዲያብራሩ ተጠይቀዋል። ስዊዲን በዶክተሩ የፍርድ ቤት መራዘም ምክንያት በግልጽ ቅሬታ እንዳደረባት ለአምባሳደሩ ማሳወቋን ጋዜጦቹ ጠቅሰዋል። ...

Read More »

ለዋልድቦ መነኮሳት ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጠ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 5/2010) በእስር ላይ የሚገኙት የዋልድቦ መነኮሳት የክህነት ልብሳቸውን እንዲያወልቁ መገደዳቸውን ተከትሎ አቤት በማለታቸው ለውሳኔ ዛሬ ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ቢደረግም ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን አላየነውም በሚል ለመጋቢት 10 /2010 ተለዋጭ ቀጥሮ መስጠቱ ታወቀ። አባ ገብረኢየሱስ ያሉበት ሁኔታም አሳሳቢ መሆኑ ተገልጿል። በመነኮሳቱ ጉዳይ ላይ ቤተክርስቲያኒቱም ሆነች ምእመናኑ ዝም ማለታቸው አነጋጋሪ ጉዳይ መሆኑ ታውቋል። ሁለት ግዜ በምህረት ይለቀቃሉ ተብሎ ነገር ግን የፍርድ ...

Read More »

የነዳጅ አቅርቦትን የማስተጓጎል ዘመቻ ለሁለተኛ ቀን መቀጠሉ ታወቀ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 5/2010) በመላ ኢትዮጵያ የተጠራው የነዳጅ አቅርቦትን የማስተጓጎል ዘመቻ ለሁለተኛ ቀን መቀጠሉ ታወቀ። ዛሬም ነዳጅ የጫኑ ቦቴዎችና ሊጭኑ በጉዞ ላይ የነበሩ ከባድ ተሽከርካሪዎች በየመንገድ ዳሩ ቆመው እንደሚታዩም ተገልጿል። በሰሜን ኢትዮጵያ በሱዳን በኩል የሚገባው የነዳጅ ስርጭትም ከፍተኛ መስተጓጎል እንደተፈጠረበት የደረሰን መረጃ ያመለክታል። የተጠራውን ዘመቻ በመጣስ ሲንቀሳቀስ የነበረ ተሽከርካሪ በጎጃም አማኑዔል በተባለ አካባቢ ከጫነው ነዳጅ ጋር መቃጠሉ ታውቋል። አገዛዙ ግን ምንም ...

Read More »