የነዳጅ አቅርቦት እቅባን ተከትሎ ወታደሮች የነዳጅ ቦቴዎችን ለማጀብ ተገደዋል

የነዳጅ አቅርቦት እቅባን ተከትሎ ወታደሮች የነዳጅ ቦቴዎችን ለማጀብ ተገደዋል
(ኢሳት ዜና ማጋቢት 05 ቀን 2010 ዓ/ም) ቄሮ የጠራው የነዳጅ አቅርቦትን የማስተጓጎል አድማ አጠቃላይ የነዳጅ አቅርቦቱን እንቅስቃሴ እንደገታው የሚደርሱን መረጃዎች ያመለክታሉ። በአሁኑ ሰዓት ነዳጅ ከጅቡቲም ሆነ ከሱዳን ወደ ኢትዮጵያ ለማጓጓዝ የሚደፍሩ ሾፌሮች በመጥፋታቸው ወታደሮች መኪኖችን አጅበው ለማስገባት ሙከራ ቢያደርጉም፣ ዛሬም እንቅስቃሴው ተስተጓጉሎ መዋሉን የደረሰን መረጃ ያመለክታል።
በአዲስ አበባ ዛሬም የነዳጅ እጥረት ሊከሰት ይችላል በሚል ምክንያት በአንዳንድ ማደያዎች አካባቢ መጨነናቅ ታይቷል።
ቄሮ ለሳምንት የጠራው የነዳጅ አቅርቦት የማስተጓጎል አድማ አሁንም እንደቀጠለ ሲሆን፣ ማንኛውም አድማውን ጥሶ የተገኘ የነዳጅ አሽከርካሪ እርምጃ እንደሚወሰድበት አስጠንቅቋል።