በሽንሌ ዞን የትጥቅ ትግል እንቅስቃሴ ተጀምሯል በሚል ወጣቶች ተይዘው ታሰሩ

በሽንሌ ዞን የትጥቅ ትግል እንቅስቃሴ ተጀምሯል በሚል ወጣቶች ተይዘው ታሰሩ
(ኢሳት ዜና ማጋቢት 05 ቀን 2010 ዓ/ም) ምንጮች እንደገለጹት በሶማሊ ክልል በሺኒሌ ዞን የትጥቅ ትግል እንቅስቃሴ የተጀመረ ሲሆን፣ ይህንን ተከትሎ የተወሰኑ ወጣቶች ተይዘው ታስረዋል።
90 በመቶ የሚሆነው የአገሪቱ የወጪ ንግድ በዚህ አቅጣጫ የሚካሄድ በመሆኑ ፣ በአካባቢው የሚካሄደው ትግል በአገሪቱ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ላይ ተጽዕኖ እንደሚፈጠር ከጉዳዩ ጋር ቅርበት ያላቸው ምንጮች ይገልጻሉ።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ ኡሴን ኡመር፣ ኤሊዬ አህመድ፣ ጣህር ፉሬ ሮብሌ፣ እልሚ ኡመር ሙሴ፣ ማሪያን እጌ፣ ጀመዓ ሃሰን ቡህና ሙሚን ኡመር የተባሉ ወጣቶች አደይቱ፣ ኡንዱፎና ገደማሉ በሚባሉ የኢትዮ-ጅቡቲ መገናኛ መንገድ ላይ ተይዘዋል።
በአካባቢው የትጥቅ ትግል እንቅስቃሴ የጀመረው፣ ከሁለት አመት በፊት በእንግሊዝ የተቋቋመውና የሶማሊ አካባቢ ዲሞክራቲክ ጥምረት የተባለው ድርጅት መሆኑን ምንጮች አክለው ገልጸዋል።