በቦሌ ለሚ የኢንዱስትሪ ዞን የሚሰሩ ሰራተኞች የስራ ማቆም አድማ አደረጉ (ኢሳት ዜና ግንቦት 07 ቀን 2010 ዓ/ም) በአዲስ አበባ በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ የሚሰሩ ሰራተኞች የሚከፈላቸው ክፍያ ከስራው ክብደት ጋር የማይመጣጠን መሆኑን በመግለጽ የስራ ማቆም አድማ ጀምረዋል። ሰራተኞቹ በስራቸው መጠን የደሞዝ ጭማሪ እንዲደረግላቸው በተወካዮቻቸው አማካኝነት ተደጋጋሚ ጥያቄ ቢያቀርቡም መልስ ሊያገኙ አልቻሉም። በገዢው ፓርቲ በኩልም የሰራተኞችን ጥያቄ ለመመለስ ፈቃደኝነት ባለመኖሩ ሰራተኞች ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
በጠምባሮ ዞን 10 መምህራን ቆስለው ሆስፒታል ሲገቡ በርካቶች ደግሞ ታሰሩ
በጠምባሮ ዞን 10 መምህራን ቆስለው ሆስፒታል ሲገቡ በርካቶች ደግሞ ታሰሩ (ኢሳት ዜና ግንቦት 07 ቀን 2010 ዓ/ም) በደቡብ ክልል በከምባታ ጠምባሮ ዞን የሚገኙ መምህራን ለልማት በሚል ያለፍላጎታቸው ከወር ደሞዛቸው ላይ መቆረጡን በመቃወማቸው 10 መምህራን በፖሊሶች ድብደባ ተፈጽሞባቸው ሆስፒታል ሲገቡ፣ 20 መምህራን ደግሞ የለምንም ጥያቄ ተስረዋል። በዚህም የተነሳ ካለፈው ሳምንት መጨረሻ ጀምሮ ትምህርት ተቋርጧል። መምህራኑ ከዚህ በፊት ለአባይ ግድብ በሚል የወር ...
Read More »ዶክተር ፍቅሩ ማሩ ከእስር ተለቀቁ
(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 7/2010)የልብ ቀዶ ሕክምና ባለሙያው ዶክተር ፍቅሩ ማሩ ከእስር ተለቀቁ። የ66 አመት እድሜ ያላቸው ስዊዲናዊውው ትውልደ ኢትዮጵያዊ ዶክተር ፍቅሩ ማሩ ከ5 አመታት እስር በኋላ ከቃሊቲ ወህኒ ቤት ወጥተዋል። በቅሊንጦ ቃጠሎ በግድያ ወንጀል ተከሰው ከነበሩት 38 ሰዎች ክሳቸው እንዲነሳ ሲወሰን አራቱ በነጻ ተለቀው ቀሪዎቹ ደግሞ የፍርድ ሂደታቸው እንዲቀጥል መባሉ ይታወሳል። በእነመቶ አለቃ ማስረሻ ስጤ መዝገብ አግባው ሰጠኝን ጨምሮ 62 ሰዎች ...
Read More »በባለስልጣናት የውጭ አካውንቶች ላይ ምርመራ እየተደረገ መሆኑን ዶ/ር አብይ ተናገሩ
በባለስልጣናት የውጭ አካውንቶች ላይ ምርመራ እየተደረገ መሆኑን ዶ/ር አብይ ተናገሩ (ኢሳት ዜና ግንቦት 07 ቀን 2010 ዓ/ም) ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ለተሰበሰቡ የተለያዩ የመንግስት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በአሰራራቸው ዙሪያ በሰጡት መግለጫ በውጭ አገራት ባንኮች የባንክ ሂሳብ ደብተር ያላቸው ባለስልጣናት ምርመራ እየተደረገባቸው ነው። የካቢኔ ስብሰባቸውን ከአርብ ወደ ቅዳሜ እንደተለወጠና ጊዜን በስራ ሰዓት በስብሰባ ማባከን እንደሚያስቀር ተናግረዋል። ባለስልጣናት አሰራራቸውን ...
Read More »ዶ/ር ፍቀሩ ማሩና ጨምሮ የተወሰኑ እሰረኞች ተፈቱ
ዶ/ር ፍቀሩ ማሩና ጨምሮ የተወሰኑ እሰረኞች ተፈቱ (ኢሳት ዜና ግንቦት 07 ቀን 2010 ዓ/ም) በእነ መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤ ከቂሊንጦ ቃጠሎ ጋር በተያያዘ ክሳቸው የተነሳላቸው የህክምና ባለሙያውን ዶ/ር ፍቅሩ ማሩን ጨምሮ፣ አቶ አግባው ሰጠኝ፣ አቶ ሲሳይ ባቱ፣ ፋሲል አለማየሁ እና አቶ ከመደ ጨመዳ ከእስር ቤት ወጥተዋል። በእነ መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤ ክስ መዝገብ ከ38 ተከሳሾች መካከል በነፍስ ይከላከሉ ከተባሉት አራት ...
Read More »የባለስልጣናት አካውንቶች ላይ ምርመራ እየተደረገ ነው
(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 7 /2010) በውጭ አገራት ባንኮች አካውንት ያላቸው ባለስልጣናት በአካውንቶቻቸው ላይ ምርመራ እየተደረገ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ገለጹ። ዶክተር አብይ አህመድ በጽህፈት ቤታቸው ለተሰበሰቡ የተለያዩ የመንግስት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በስራዎቻቸው ዙሪያ ገለጻና ማሳሰቢያ ሰጥተዋል ። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በዚህ መድረክ ላይ የራሳቸውን ጥናታዊ ጽሁፍ አቅርበዋል። በዚሁ ጽሁፋቸውም የአመራር ጥበብን በተመለከተ ገለጻ ማድረጋቸው ነው የተገለጸው ። የህዝብ ...
Read More »የሕወሃት የቀድሞ ባለስልጣናት በጡረታ ተገለሉ
(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 7/2010)አቶ ስብሃት ነጋን ጨምሮ 5 የሕወሃት እና የኢሕአዴግ አመራር የነበሩ ባለስልጣናት ከመንግስት ሓላፊነታቸው በጡረታ ተገለሉ። በጠቅላይ ሚኒስትር ትዕዛዝ በጡረታ ከተገለሉት ባለስልጣናት መካከል ዶ/ር ካሱ ኢላላን ጨምሮ ሁለቱ ከፖሊሲ ምርምር እና ጥናት ማዕከል መሆኑን ለመረዳት ተችሏል። የብሮድካስት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር የህወሃቱ ዘርዓይ አስገዶምም ከስልጣናቸው ተባረዋል። ከአቶ መለስ ዜናዊ በፊት የህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ /ሕወሓት / ሊቀመንበር የነበሩት የ83 ዓመቱ ...
Read More »በእስራኤል ጋዛ ድንበር በተነሳ ተቃውሞ 37 ሰዎች ተገደሉ
(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 6/2010) አሜሪካ ኤምባሲዋን ወደ ኢየሩሳሌም ማዛወሯን ተከትሎ በተነሳ ተቃውሞ 37 የሚሆኑ ፍልስጤማውያን ተገደሉ። በጋዛ ድንበር የእስራኤል ወታደሮች በከፈቱት ተኩስ ከ1 ሺ 3 መቶ በላይ ፍልስጤማውያን መቁሰላቸውም ታውቋል። አሜሪካ ዛሬ ቢሮዋን በይፋ ከቴላቪቭ ወደ ወደ ኢየሩሳሌም ማዛወሯን ተከትሎ በሚደረገው የመክፈቻ ዝግጅት ላይ ለመገኘት የአሜሪካ ባለስልጣናት ኢየሩሳሌም መግባታቸው ታውቋል። ባለፈው ታህሳስ ወር ነበር የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለእስራኤሏ ኢየሩሳሌም እውቅና ...
Read More »ድምጻዊ ኮይሻ ሴታ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ
(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 6/2010) ድምጻዊ ኮይሻ ሴታ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ። በዘመናዊ የወላይትኛ ሙዚቃው ከፍተኛ ዕውቅናን ያገኘው ኮይሻ ሴታ በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ትላንት ማረፉን ለማወቅ ተችሏል። የወላይትኛን ሙዚቃ በዘመናዊ መልክ በመጫወት ፈር ቀዳጅ እንደሆነ የሚነገርለት ድምጻዊ ኮይሻ ሴታ 2 አልበሞችን ለአድማጮቹ አድርሷል። የወላይትኛ ሙዚቃን ቀድሞ በማቀንቀን ለዛሬው የወላይትኛ ሙዚቃ የተሻለ መሆን ከፍተኛ ድርሻ እንዳበረከተም ይነገርለታል። በ1980ዎቹ አጋማሽ በኢትዮጵያ የሙዚቃ መድረክ ስማቸው ...
Read More »አምባሳደር ካሳ ተክለብርሃን የጠሩት ስብሰባ በተቃውሞ ተበተነ
(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 6/2010) በአሜሪካን የኢትዮጵያ አምባሳደር ካሳ ተክለብርሃን የጠሩት ስብሰባ በተቃውሞ መበተኑ ተገለጸ። ባለፈው ቅዳሜ በአሜሪካ ሚኒሶታ ግዛት ብሉሚንግተን ከተማ የተጠራውን ስብሰባ በአካባቢው የሚኖሩ የተለያዩ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲዎች ባሰሙት ተቃውሞ ተቋርጧል። በተለይም የሶማሌ ኢትዮጵያውያን በከፍተኛ ቁጥር ወደ ስብሰባ አዳራሽ በመግባት እንዲቋረጥ ማደረጋቸውን በቪዲዮ ተደግፎ ከወጣው መረጃ ለማወቅ ተችሏል። አምባሳደር ካሳ ተክለብርሃን ከስብሰባ አዳራሹ በጓሮ በኩል እንዲሸሹ መደረጉንም ያገኘነው መረጃ አመልክቷል። ያለፈው ...
Read More »