ድምጻዊ ኮይሻ ሴታ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 6/2010) ድምጻዊ ኮይሻ ሴታ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።

በዘመናዊ የወላይትኛ ሙዚቃው ከፍተኛ  ዕውቅናን ያገኘው ኮይሻ ሴታ በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ትላንት ማረፉን ለማወቅ ተችሏል።

የወላይትኛን ሙዚቃ በዘመናዊ መልክ በመጫወት ፈር ቀዳጅ እንደሆነ የሚነገርለት ድምጻዊ ኮይሻ ሴታ 2 አልበሞችን ለአድማጮቹ አድርሷል።

የወላይትኛ ሙዚቃን ቀድሞ በማቀንቀን ለዛሬው የወላይትኛ ሙዚቃ የተሻለ መሆን ከፍተኛ ድርሻ እንዳበረከተም ይነገርለታል።

በ1980ዎቹ አጋማሽ በኢትዮጵያ የሙዚቃ መድረክ ስማቸው በመነሳት ከሚጠቀሱ ድምጻውያን አንዱ ለመሆንም በቅቷል።

ለተወሰኑ ዓመታት በሀገር ፍቅር ቲያትር ቤት በተጋባዥ ድምጻዊነትም ማገልገሉን ከህይወት ታሪኩ ለመረዳት ተችሏል።

ድምጻዊ ኮይሻ ሴታ ባደረበት ህመም በራስ ደስታ ሆስፒታል ህክምናውን ሲከታትል ቆይቶ ትላንት ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ ተገልጿል።