በቦሌ ለሚ የኢንዱስትሪ ዞን የሚሰሩ ሰራተኞች የስራ ማቆም አድማ አደረጉ

በቦሌ ለሚ የኢንዱስትሪ ዞን የሚሰሩ ሰራተኞች የስራ ማቆም አድማ አደረጉ
(ኢሳት ዜና ግንቦት 07 ቀን 2010 ዓ/ም) በአዲስ አበባ በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ የሚሰሩ ሰራተኞች የሚከፈላቸው ክፍያ ከስራው ክብደት ጋር የማይመጣጠን መሆኑን በመግለጽ የስራ ማቆም አድማ ጀምረዋል።
ሰራተኞቹ በስራቸው መጠን የደሞዝ ጭማሪ እንዲደረግላቸው በተወካዮቻቸው አማካኝነት ተደጋጋሚ ጥያቄ ቢያቀርቡም መልስ ሊያገኙ አልቻሉም። በገዢው ፓርቲ በኩልም የሰራተኞችን ጥያቄ ለመመለስ ፈቃደኝነት ባለመኖሩ ሰራተኞች በመጨረሻ ስራ ለማቆም ተገደዋል።
የስራ ማቆሙ እንደተጀመረ አድማውን በሃይል ለመበተን በማስፈራራት ሙከራ የተደረገ ቢሆንም፣ ሰራተኞቹ ግን አድማውን ከማድረግ ወደ ሁዋላ አላሉም።
በኢንዱስትሪ ፓርኩ ውስጥ በርካታ የውጭ ድርጅቶች ቢኖሩም፣ ለሰራተኞች የሚከፍሉት ክፍያ እጅግ አነስተኛ በመሆኑ፣ ሰራተኞች ዘወትር ምሬታቸውን ይገልጻሉ። በሌሎች አገሮች የሚደረጉትን መሰረታዊ የሚባሉ የሰራተኞች መብቶች ያልተሟሉ መሆናቸውንም ሰራተኞች ይናገራሉ።