ኢሳት ዜና:- የመለስ መንግሰት ከጊዜ ወደ ጊዜ በከፋ ደረጃ በህዝብ ላይ በሚፈፅመዉ የሰብኣዊ መብት ረገጣ ላይ የተነጋገረዉ ታላቅ ሀዝባዊ ስብሰባ የተካሄደዉ በለንደን ፍሬንድ ሃዉስ አዳራሽ ሲሆን ቁጥራቸዉ በሁለት መቶዎች የሚገመቱ ኢትዮጵያዊያን ተገኝተዋል። ስብሰባዉን በንግግር የከፈቱት የ3ኛዉ አለም የሁሉም የፓርላማ ቡድኖች ህብረት ሊቀመንበር የተከበሩ ካዉንስለር ሙሽራክ ላሺር ናቸዉ። ካዉንስለሩ በመክፈቻ ንግግራቸዉ በኢትዮጵያ ዉስጥ ያለዉ የሰብኣዊ መብት አያያዝ እጅግ አሳሳቢ እንደሆነ በመግለፅ ከዚህ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
በበየዳ ቀበሌ የሚገኙ ነዋሪዎች ወደ ትግራይ ክልል እንዲዛወሩ ግፊት መደረጉን ተቃወሙ
ኢሳት ዜና የራሽ ደጀን ተራራ በሚገኝበት በሏሪ ቀበሌ በበዬዳ ወረዳ አካባቢ የሚኖሩ ነዋሪዎችን፣ በትግራይ ክልል ውስጥ እንዲካተቱ ለማሳመን ለ7 ተከታታይ ቀናት የተደረገው ውይይት ሳይሳካ መቅረቱን ስማቸው እንዳይገለጥ የፈለጉ የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢሳት ገልጠዋል። የትግራይ ክልል ባለስልጣናት የቀበሌው ነዋሪዎች ወደ ትግራይ ክልል እንዲዛወሩ ተደጋጋሚ ሙከራ ቢያደርጉም፣ ህዝቡ ግን እና በታሪክ ተወቃሽ አንሆንም፣ አያት ቅድመ አያቶቻችን አጥንታቸው የተቀበረው በዚሁ ቦታ ነው። ግዛቱ ማን እንደሆነ ...
Read More »ብዙ ኢትዮጵያዊያንን ለሞት፤ ለእስራትና ለሰቆቃ ሲዳርግ የነበረዉ የቀድሞዉ የህወሃት/ኢህአዴግ የደህንነት ባለስልጣን ለፍርድ ሊቀርብ እንደሚችል ተገለፀ
ኢሳት ዜና:- የቀድሞዉ የህወሃት የደህንነት ሹም የነበረዉና በአሁኑ ወቅት በዩናይትድ ስቴትስ ኮለምበስ ኦሃዮ ነዋሪ በመሆን ለኢህአዴግ መንግስት የስለላና የመረጃ ስራ የሚያከናዉነዉ ብስራት አማረ የተባለዉን ግለሰብ ለፍርድ ለማቅረብ የሚያስችል ስራ በመሰራት ላይ እንዳለ ለማወቅ ተችሏል። አቶ ደምሴ በላቸዉ የተባሉ የኮሎምበስ ነዋሪ ከአንድ ኢትዮጵያዊ የሬዲዮ ጣቢያ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ግለሰቡ በ2002 በዩናይትድ ስቴትስ የፖለቲካ ጥገኝነት ጠይቆ በተቃዋሚ ጎራ የቆመ በማስመሰል ገፅታዉን ካሳየ ...
Read More »በጥቁር አንበሳ የህክምና ዶክተሮች ባለባቸዉ መሰረታዊ የኑሮ ጫና ምክንያት የስራ ማቆም አድማ እንደሚያደርጉ አስጠነቀቁ : ጥያቄያቸዉ እስከ ጥቅምት 15/2004 መልስ እንዲሰጠዉ የጊዜ ገደብ ሰጥተዋል
ኢሳት ዜና:- ከ400 በላይ የሚሆኑት በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በማስተማርና የህክምና አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኙ የህክምና ዶክተሮች በአገሪቱ ያለዉ የኑሮ ዉድነትና የመኖሪያ ቤት ችግር በህይወታቸዉ ላይ ከፍተኛ ድቀት እያደረሰባቸዉ በመሆኑ መንግስት አስቸኳይ መፍትሄ እንዲሰጣቸዉ ጠይቀዋል። አዲስ ነገር የመረጃ መረብ አዲስ አድማስ ጋዜጣን በመጥቀስ እንደገለፀዉ የህክምና ባለሙያዎቹ በጥቁር አንበሳ ግቢ ውስጥ ባደረጉት ስብሳባ ጥያቄያቸዉ የፖለቲካ ወይም የዐመፅ ሳይሆን ከጊዜ ወደጊዜ እየተባባሰ በመሄድ ላይ ...
Read More »በኦሮሚያ እና በአማራ ክልሎች የሰፈነው የመልካም አስተዳደር እጦት በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ሕዝባዊ አመጽን ሊቀሰቅስ እንደሚችል የፌዴራል ጉዳዮች ሚንስትር መሥሪያ ቤት ያስጠናው አንድ ጥናት አመለከተ።
ኢሳት ዜና:- ጥናቱ በአማራና በኦሮሚያ ክልሎች የሚታየው የመልካም አስተዳደር እጦት ህብረተሰቡን ወደ አመጽ መንገድ እየመራው መሆኑን አመልክቷል። የሙያተኞች ግብረ ኃይል የሕዝብ አደረጃጀትና የደህንነት ጉዳይ በሚል ርእስ ባጠናው ጥናት ሁልቆ መሳፍርት ችግሮችን ዘርዝሯል። በኦሮሚያና አማራ ክልሎች በምክትል ከንቲባዎች የሚመሩ ከህብረተሰቡ የተውጣጡ የአማካሪዎች ምክር ቤት እንዲቋቋም እና የግምገማና የክትትል ሥራ እንዲሰራ የሚል የመፍትሄ ሀሳብ በጥናቱ ውስጥ ቀርቧል። ከመፍትሄዎች አንዱ ከነዋሪዎች፣ ከምሑራን፣ ነጋዴዎች፣ የሀገር ...
Read More »ኢሳት የአጭር ሞገድ ሬዲዮ በቀጥታ ወደ ኢትዮጵያ መጀመሩን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ፣
ኢሳት የአጭር ሞገድ ሬዲዮ በቀጥታ ወደ ኢትዮጵያ መጀመሩን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ፣
Read More »ኢሳት የአጭር ሞገድ ሬዲዮ በቀጥታ ወደ ኢትዮጵያ መጀመሩን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ፣
መስከረም 26 2004 ዓ.ም የኢሳት ማኔጅመንት እና መላው የኢሳት ቤተሰቦች የኢትዮጵያ ሕዝብ ነፃ እና ትክክለኛ መረጃ የማግኘት መብት አለው በሚል እምነት ከተነሳን አንድ ዓመት ተሻገርን፤ ይህንንም ከግብ ለማድረስ ማናቸውንም መሰናክል ሰብረን ለማለፍ ባልተቋረጠ ትግል ውስጥ ቀጥለናል። ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ እንዳሳወቅነው የኢትዮጵያ ህዝብ ትክክለኛና ሚዛናዊ መረጃ ማግኘት ተፈጥሮዓዊና ሰብዓዊ መብቱ ነው። ስልጣን ላይ ያለው የአቶ መለስ መንግስት ይህንን መብት ገፎ የፈለገውንና ...
Read More »የኢሳትን ወደ ፕሮግራም ሥርጭት መመልስ አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ፣
ሰኔ 3፣ 2003 ዓም ከሁለት ወር በላይ በደረሰበት ከፍተኛ የዓየር ሞገድ የፕሮግራሙን ሥርጭቅ አቁሞ የነበረው ኢሳት በሰኔ 2፣ 2003 ዓም ወደ መደበኛ ሥርጭቱ መመለሱን ለህዝብ ይፋ ሲያደርግ በታላቅ ደስታ ነው። መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ ማንም ሊከለክልህና ሊገድብብህ ሥልጣን የሌለውን እውነተኛ መረጃ የማግኘት ተፈጥሯዊ መብትህን ለማፈን እና እነርሱ የፈለገውን የውሸት ትርኪ ምርኪ ካልሆነ በቀር፣ ሌላ ምንም ዓይነት መረጃ እንዳታገኝ፣ በሥልጣን ላይ ...
Read More »የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴለቪዥን (ኢሳት) ከጥር እስከ ሚያዚያ 2003 ዓ/ም የአደረገው የገንዘብ ድጋፍ ማሰባሰቢያ ዘመቻ አስመልክቶ የወጣ መግለጫ
ሐምሌ 6 ቀን 2003 ዓ/ም የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴለቪዥን (ኢሳት) ከጥር እስከ ሚያዚያ 2003 ዓ/ም የአደረገው የገንዘብ ድጋፍ ማሰባሰቢያ ዘመቻ አስመልክቶ የወጣ መግለጫ በሃገራች በሥልጣን ላይ ያለው የፈላጭ ቆራጭ አገዛዝ የኢትዮጵያን ህዝብ በመረጃ ጨለማ ውስጥ ለመግዛት ያሰፈነውን የአፈና ቀንበር ለመስበርና፣ ፍትህና ዴሞክራሲን ለማስፈን የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴለቪዥን የህዝብ አይንና ጆሮ በመሆን የበኩሉን አስተዋጾ ሲያደርግ መቆየቱን ይታወሳል። እንደሚታወቀው ኢሳት በእቅድ ...
Read More »ለኢሳት የገንዘብ ማሰባሰብ ዘመቻ ለ10 ቀናት ተራዘመ ከኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን (ኢሳት) የተሰጠ መግለጫ፣
መጋቢት 11 ቀን 2003 ዓ/ም የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን (ኢሳት) ሥራ ከጀመረ ካለፈው የሚያዚያ ወር 2002 ዓም ጀምሮ በተለያዩ ደረጃዎች ያጋጠሙትን ችግር እየተቋቋመ በርካታ ፕሮግራሞችን በቀጥታ ወደ ሀገር ቤት በማስተላለፍ ከፍተኛ የህዝብ ቀልብ ለመሳብ በቅቷል፣ ይህን ሥራውን ዛሬም ቀጥሏል። ኢሳት አሁን ባለበት ደረጃ ወደ ሀገር ቤት የሚሰጠውን አግልግሎት እንዲቀጥልና በውጭ ሀገርም የቴሌቪዥን አገልግሎት ስርጭት ለመጀመር ያለውን ዕቅድ ተግባራዊ ለማድረግ፣ ከዚህ በፊት ...
Read More »