.የኢሳት አማርኛ ዜና

በዴንቨር የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት የጠሩት ስብሰባ ሳይሳካ ቀረ

ህዳር 20 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በዴንቨር ኮለራዶ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የመንግስት ባለስልጣናት ለአባይ ግድብ ማሰሪያ ቦንድ ለመሸጥና አዲሱን የዲያስፖራ ፖሊሲ ለማስተዋወቅ የጠሩት ስብሰባ ሳይሳካ ቀረ በአምባሳደር ተበጀ በርሄ የተመራው የልኡካን ቡድን ያቀደውን ሳይፈጽም፣ በአካባቢው በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ተቃውሞ ወደ ዋሽንግተን ዲሲ እንዲመለስ መደረጉን በኮለራዶ ኢትዮጵያውያን አክቲቪስቶች የላኩት ዜና ያመለክታል። አምባሳደሩ ስበሰባው የህዝብ ስብሰባ እንዳልሆነ በማስታወቅ በስፍራው የነበሩት ተቃዋሚዎች አካባቢውን ለቀው እንዲሄዱ ...

Read More »

አንድ የፖሊስ ሆስፒታል ምግብ አቅራቢ በ3 የፌደራል ፖሊሶች ተደፈረች

ህዳር 19 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የፖሊስ ሆስፒታል ምግብ አብሳይ የሆነችው ማርታ ጉልላት የተባለችው የ23 አመት ወጣት ፣ ህዳር 11 ቀን ሌሊት ላይ በሶስት የፌደራል ፖሊሶች ተደፍራ ህይወቱዋ አስጊ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኝ የደረሰን ዜና አመልክቷል። የማርታ ጉልላት ቤተሰቦች ፖሊሶቹ ለፍርድ እንዲቀርቡ መንግስትን ቢጠይቁም፣ መንግስት ግን ጉዳዩን ሆን ብሎ እያጉዋተተው ለማወቅ ተችሎአል። የፌደራል ፖሊሶቹ ወጣቷ የተለመደ ምግብ የማቅረብ ስራዋን ስትሰራ በነበረበት ...

Read More »

በጎንደር ሆስፒታል በደረሰ የምግብ መመረዝ በሺ የሚቆጠሩ ተማሪዎች ለበሽታ ተዳረጉ

ህዳር 19 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከሆስፒታል ምንጮች የደረሰን ዘገባ እንደሚያሳየው የምግብ መመረዙ የተከሰተው ማራኪና ቴዎድሮስ በሚባሉ ሁለት የዩኒቨርስቲው ካምፓሶች ውስጥ ነው። በአንደኛው ግቢ ውስጥ የሆስፒታል አልጋዎች በመጣበባቸው ተማሪዎች በዬመኝታ ክፍላቸው ተኝተው እንዲታከሙ ተደርጓል። መንግስት መረጃው ወደ ውጭ እንዳይወጣ ለሀኪሞቹ ትእዛዝ መሰጠቱንም ለማወቅ ተችሎአል። ከዩኒቨርስቲው አስተዳደር ሰራተኞች እንዳገኘነው መረጃ ከሆነ ችግሩ የተፈጠረው የኑሮ ውድነቱን ተከትሎ ለተማሪዎች የሚቀርበው ምግብ ጥራት የጎደለው ...

Read More »

በኢትዮጵያ ውስጥ ጋዜጠኞችን በሽብር እያሳበቡ መክሰስ መጀመሩን ተከትሎ ፣ ከፍተኛ ፍርሀት መንገሱን ረዩተር ዘገበ

ህዳር 19 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ታዋቂው የዜና ማሰራጫ በአገር ቤት የሚገኙ ጋዜጠኞችን ጠቅሶ እንደዘገበው፣ ጋዜጠኞች በአሁኑ ጊዜ “የትኛው በሽብርተኝነት ያስከስሳል፣ የትኛው አያስከስስም” በማለት  እየተጨነቁ ነው። የሲፒጄ የአፍሪካ ተወካይ ሙሀመድ ኬታ እንዳለው ከሆነ ደግሞ ኢትዮጵያ በጋዜጠኞች ስደት አለምን በመምራት ላይ ናት። ሂውማን ራይትስ ወችን ጨምሮ በርካታ አለማቀፍ ድርጅቶች የኢትዮጵያን የጸረ ሽብር ህግ በአገር ውስጥ የሚካሄዱትን የፖለቲካ እንቅስቃሴዎች ለመግታት ታስቦ የተረቀቀ ...

Read More »

በሞያሌ ከተማ በተነሳው ግጭት 7 ሰዎች ተገደሉ

ህዳር 18 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በሞያሌ ከተማ የኦሮሞ ተወላጅ በሆኑት ቦረናዎችና የሶማሊ ተወላጅ በሆኑት ገሪዎች መካከል በተነሳ ግጭት ሰባት ሰዎች ተገድለዋል፣ ከሟቾች መካከል ሁለት ሴቶች  ይገኙበታል። ህዳር 10 ቀን የተነሳው ግጭት ገሪዎች ወይም ሶማሊዎች በከተማው የሚገኘውን አንድ ትምህርት ቤት ለእኛ መሆን አለበት የሚል ጥያቄ ማቅረባቸውን ተከትሎ ሲሆን፣ ቦረናዎች ደግሞ በእኛ መሬት ላይ ያለን ትምህርት ቤት ሶማሊዎች ሊወስዱት አይገባም ማለታቸውን ...

Read More »

በአዲስ አበባ እሁድ እለት በተካሄደው 11ኛው ታላቁ ሩጫ ማህበረሰቡ ገዢውን ፓርቲ ሲያወግዝና ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ብሶቶችን ሲያስተጋባ ዋለ

ህዳር 18 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ዘጋቢያችን እንደገለጠው መንግስት መድረኩ የብሶት ማሰሚያ መድረክ እንዳይሆን በመስጋት ከፍተኛ ጥረት አድርጎ ነበር። ከዚህ ቀደም ህዝቡ መስቀል አደባባይ ሲደርስ ” መለስ ሌባ፣ መለስ ይውረድ” የሚል ጩኸት በማሰማቱ፣ የመሮጫው አቅጣጫ ከአምና ጀመሮ እንዲቀዬር ተድረጎአል። የዘንድሮው የመሮጫ አቅጣጫ ለገጽታ ግንባታ በሚል የጎተራን የማሳለጫ መንገድ እንዲያካትት ተድረጎአል። ይህም ሁሉ ጥረት ተደርጎ ህዝቡ ገዢውን ፓርቲ ከማውገዝና ብሶቱን ...

Read More »

የአቶ መለስ ዜናዊ መንግሥት በእነ ኤሊያስ ክፍሌ የክስ መዝገብ በ”ሽብርተኝነት ወንጀል‘ የከሰሳቸውን ተከላከሉ ሲል ውሳኔ አስተላለፈ

ህዳር 18 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአቶ መለስ ዜናዊ መንግሥት በእነ ኤሊያስ ክፍሌ የክስ መዝገብ በ”ሽብርተኝነት ወንጀል‘ የከሰሳቸውን የፖለቲካ ፓርቲ የአመራር አባላትና እና ጋዜጠኞች ተከላከሉ ሲል በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሦስተኛ ወንጀል ችሎት በኩል ውሳኔ አስተላለፈ፡፡ የፌዴራል ፍርድ ቤት ሦስተኛ ወንጀል ችሎት ለዛሬ ጠዋት ይዞት የነበረውን የችሎት ጊዜ ቀጠሮ ወደ ከሰዓት በኋላ ያስተላለፈ  ሲሆን ለዚህም በሰዓቱ ለተገኙት ተከሳሾች፣ የተከሳሽ ቤተሰቦችና ...

Read More »

አስደንጋጭ ዜና የደረሰው ኢህአዴግ የከተማውን ህዝብ በመከፋፈል ኮንፈረንስ ሊጠራ መሆኑ ታወቀ

ህዳር 16 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-“የአዲስ አበባ ህዝብ በአስተዳደር በደል ምክንያት ከስርአቱ ጋር ሆድና ጀርባ ሆኗል” የሚል አስደንጋጭ ዜና የደረሰው ኢህአዴግ የከተማውን ህዝብ በመከፋፈል ኮንፈረንስ ሊጠራ መሆኑ ታወቀ የብሄር ብሄረሰቦችን ቀን ምክንያት በማድረግ ገዢው ፓርቲ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር በከተማዋና በመላ አገሪቱ ተፈጥረዋል ባለቸው ችግሮች ዙሪያ ውይይት እንደሚያደርግ የደረሰን ዜና አመልክቷል። በዚህም መሰረት ህዳር 17 ከንግዱ ማህበረሰብ አባላት ጋር፣ ...

Read More »

በእስር ላይ ይገኝ የነበረ አንድ የቀድሞው የቅንጅት አባል በማረሚያ ቦት ውስጥ ህይወቱ ማለፉ ታወቀ

ህዳር 16 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢሳት ምንጮች እንዳሉት መስፍን አድማሱ የተባለው የቀድሞው ቅንጅት ተማራጭ በሙስና ወንጀል ተከሶ ለ 3 አመት ከስድት ወር በእስር ሲማቅቅ ነበር። ግለሰቡ በሶስት አመት የእስርቤት ቆይታው አንድም ቀን ፍድር ቤት ቀርቦ እንደማያውቅ የደረሰን መረጃ ያመለክታል። ስለግለሰቡ አሟሟት ምክንያት ዝርዝር መረጃ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም። ይሁን እንጅ ግለሰቡ ማረፉን ከቤተሰቦቹ የተገኘው መረጃ አረጋግጧል። በርካታ ዜጎች በሚደርስባቸው ...

Read More »

ኢትዮጵያ ጦሯ ወደ ሶማሊያ ግዛት ዘልቆ መግባቱን አመነች

ህዳር 16 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ አንድ የ ኢትዮጵያ ባለስልጣን ለሮይተርስ እንደገለጹት፤በጣም አነስተኛ ቁጥር ያለው የኢትዮጵያ ጦር ወደ ሶማሊያ ግዛት ገብቷል። የደቡባዊ ሶማሊያን አብዛኛውን ክፍል ከተቆጣጠሩት የአልሸባብ ሚሊሻዎች ጋር እየተዋጉ የሚገኙትን የኬንያንና የሶማሊያን የሽግግር መንግስት ሰራዊት ለማገዝ  ኢትዮጵያ ተጨማሪ ጦር እንደምትልክም፤ እኚሁ ባለስልጣን ተናግረዋል። ኢትዮጵያ ቀደም ሲል ጦሯ ወደ ሶማሊያ ግዛት እንዳልገባ ስታስተባብል መቆየቷ  ይታወሳል። እኚሁ የኢትዮጵያ ...

Read More »