ታህሳስ 08 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአቶ መለስ ቀኝ እጅ የሚባሉት የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ሚንስትር አቶ በረከት ስምዖን ”የሁለት ምርጫዎች ወግ‘ በሚል ምርጫ 19 97 ዓ.ም እና 2002 ዓ.ም አነፃጽረው የጻፉት መጽሐፍ ማክሰኞ በሸራተን አዲስ ላሊበላ አዳራሽ ይመረቃል፡፡ የክብር እንግዶች የሆኑ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት፣ የዩኒቨርስቲ ምሁራን ይበልጡኑ የስነጽሑፍና የታሪክ ምሑራን እና የሀገር ውስጥና የውጭ አገር ጋዜጠኞች ተለይተው ተጋብዘዋል፡፡ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
በዱባይ የመንግስት ተወካዮች ለህዳሴዉ ግድብ ማሰገንቢያ የሚሆን ያደረጉት የገቢ ማሰባሰቢያ ስብሰባ የተሳካ አልነበረም ተባለ
ታህሳስ 08 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በዱባይ የመንግስት ተወካዮች ለህዳሴዉ ግድብ ማሰገንቢያ የሚሆን ያደረጉት የገቢ ማሰባሰቢያ ስብሰባ የተሳካ አለመሆኑን ከስፍራው የደረሰን መረጃ አመለከተ ባለፈው ቅዳሜ ዲሰምበር 17/2011 በዱባይ ከተማ መራቅባት አካባቢ በሚገኘዉ የማርየት ሆቴል ውስጥ በአንድ የኢህአዴግ ሚንስትር ዴኤታ የሚመራ የተወካዮች ቡድን ለህዳሴዉ ግድብ ማሰገንቢያ የሚሆን ስብሰባ ጠርተው የነበረ ቢሆንም፣ ስብሰባውን ወደ 100 ሺህ ኢትዮጵያዉያን ይኖሩባታል ተብሎ በሚታሰበው የአረብ ኢምሬትስ፣ ...
Read More »በአምስተርዳም ከተማ እና አካባቢዋ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የኔሰው ገብሬን ዘከሩ
ታህሳስ 08 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአምስተርዳም የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ባዘጋጀው የመምህር የኔሰው ገብሬ መታሰቢያ ስነስርአት ላይ የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች እና የሲቪክ ማህበረሰብ ተወካዮች ንግግር አድርገዋል። በሆላንድ የሲቪክ ማህበራት ተወካይ የሆኑት አቶ ቦጋለ ካሳየ እንደተናገሩት የኔሰው ገብሬ ለቀረው ትውልድ ከፍተኛ የሆነ እዳ ጥሎ አልፎአል። አቶ ቦጋለ አክለውም ” ከራሳችን ጋር በመታረቅ፣ ጭቆናን አምርረን በመጥላትና በትናንንሽ ጥቅማጥቅሞች ባለመደለል በጋራ የምንቆም ከሆነ የኔሰው ...
Read More »በእነ አንዷለም አራጌ የክስ መዝገብ በተከሰሱ ዜጎች ላይ 35 ሰዎችን የዐቃቤ- ሕግ ምስክር አድርጎ ማቅረብ ጀመረ
ታህሳስ 07 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአቶ መለስ መንግሥት በእነ አንዷለም አራጌ የክስ መዝገብ (112546) በከሰሳቸው 24 የፖለቲካ ፓርቲ አመራር አባላት፣ ጋዜጠኞች እና ነፃ አሳቢ ዜጎች ላይ 35 ሰዎችን የዐቃቤ- ሕግ ምሥክር አድርጎ ማቅረብ ጀመረ። መንግሥት የምስክሮቹን የቀን ውሎ አበል፣ የቁርስ፣ ምሳ ፣ እራት የምግብ ፍጆታ በመሸፈን ሌሎች ጥቅማ- ጥቅሞችን እንደሚያስብ የፍርድ ቤት ምንጮች አስታወቁ፡፡ በከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ...
Read More »በስልጢ ዞን አስተዳዳሪዎች አመራር ሰጪነት በመቶዎች የሚቆጠሩ የአካባቢው ሙስሊሞች በስልጢ ዞን- በኮቶ ባሰሎ የምትገኝን አንዲት ቤተ-ክርስቲያን በእሳት አቃጠሉ
ታህሳስ 07 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአካባቢው ክርስቲያኖች እያለቀሱ ሲናገሩ እንደተደመጡት፤ የቤተ-ክርስቲያኒቱን ጣራ ቀደም ሲል ያፈረሱት የመንግስት ፖሊሶች ነበሩ። ሰሞኑን ደግሞ በመስተዳድሩ እና በፖሊሶች አስተባባሪነት በቀጠለ ሁለተኛ ዙር የጥቃት ዘመቻ ቤተ-ክርስቲያኒቱ ሙሉ በሙሉ በእሳት ተቃጥላለች። ክርስቲያንና ሙስሊም ለዘመናት ተከባብረው የሚኖሩባት ኢትዮጵያ በተለይ ካለፉት 20 ዓመታት ወዲህ ተደጋጋሚ ሀይማኖታዊ ግጭቶችን ስታስተናግድ መስተዋሏ ብዙዎችን ማነጋገር ከጀመረ ውሎ አድሯል። ግጭቱ፤በህዝብ እየተጠላ የመጣው ገዥው ...
Read More »በሆላንድ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የኔሰው ገብሬን ለመዘከር የሻማ ማብራት ስነስርአት ያደርጋሉ
ታህሳስ 07 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ኢትዮጵያኑ እሁድ ዲሰምበር 18 በአምስተርዳም ከተማ በሚያካሂዱት የሻማ ማብራት ስነስርአት ፣ የኔሰው ገብሬ ለኢትዮጵያ ህዝብ የከፈለውን መስዋትነት በመዘከር፣ በውጭ የሚገኘው ኢትዮጵያዊ በአገሩ ጉዳይ ላይ ስለሚኖረው ሀላፊነት ምክክር እንደሚደረግ የአምስተርዳም የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ሊቀመንበር አቶ ወንድወሰን ገብረህይወት ለኢሳት ገልጠዋል። በአሪቢሞንድ ስትራት ከሰአት በሁዋላ 5 ፒኤም በሚደረገው ስነስርአት ላይ የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅት ተወካዮች፣ የመገናኛ ብዙሀን ወኪሎችና የሲቪክ ...
Read More »አምነስቲ ኢንተርናሽናል በኢትዮጵያ ውስጥ በጸረ ሽብርተኝነት ሰበብ የሚካሄደው እስር የፖለቲካ ተቃውሞን ለማፈን ተብሎ የተደረገ ነው አለ
ታህሳስ 06 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አምነስቲ ባወጣው ሪፖርት እንዳመለከተው በኢትዮጵያ ውስጥ ካለፈው መጋቢት ወር ጀምሮ 108 የተቃዋሚ አባላትና 8 ጋዜጠኞች ታስረዋል። የኢትዮጵያ መንግስት፣ ተቃዋሚዎችንና ተችዎችን በጸረ ሽብር ትግል ስም ዘብጥያ እያወረደ ነው ሲል የሰብአዊ መብት ተቋሙ በሪፖርቱ አመልክቷል። አብዛኞቹ አሸባሪ ተብለው የታሰሩት በሙሉ መንግስትን በመተቸት የሚታወቁ ናቸው የሚለው አምነስቲ፣ የታሰሩበት ምክንያትም መንግስት የፖለቲካ ለውጥ እንዲያካሂድ ያሳሰቡ፣ ሰላማዊ ሰልፍ እንዲፈቀድላቸው ...
Read More »በእነ አንዷለም አራጌ የክስ መዝገብ ላይ የቀረቡት የህግ ምስክሮች በናዝሬት ለሌላ ‘አካልዳማ’ የችሎት ተዉኔት የቃል አሰጣጥ ስልጠና መዉሰዳቸዉ ታወቀ
ታህሳስ 06 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በቅርቡ ከመንግሥት ጋር በመደራደር እና በግዴታ “አኪልዳማ‘ በተሰኘው የኢቲቪ የፕሮፓጋንዳ ዝግጅት ላይ ራሳቸውን፣ ሌሎች ሰዎችን እና ፓርቲዎችን በመውቀስ ለመንግሥት የድጋፍ ቃላቸውን የሰጡ ሰዎች ይገኙበታል የተባሉት በእነ አንዷለም አራጌ የክስ መዝገብ የሚጠሩት የዐቃቤ ሕግ ምስክሮች እነማን እንደሆኑ በዝርዝር አልታወቁም። ለምስክሮች ደኅንነት ሲባል ስማቸዉ እንዳይገለፅ የተደረገው ቁጥራቸዉ ከ30 በላይ የሆኑት የአቃቤ ህግ ምስክሮች በናዝሬት ከተማ አንድ ...
Read More »በሁለቱ ስዊድናውያን ጋዜጠኞች ላይ በሚቀጥለው ሳምንት ረቡዕ ይሰጣል የተባለው ብይን የኢትዮጵያና የስዊድን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ይበልጥ ያበላሸዋል ተባለ
ታህሳስ 05 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በሁለቱ ስዊድናውያን ጋዜጠኞች ላይ በሚቀጥለው ሳምንት ረቡዕ ይሰጣል የተባለው ብይን ለወትሮው በቋፍ ላይ የሚገኘውን የኢትዮጵያና የስዊድን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት መውጫ ይበልጥ ያበላሸዋል የሚል ስጋት እንዳላቸው ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ አንድ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ገለጹ። የተቃዋሚ ፓርቲ መሪው ለኢሳት ዘጋቢ እንዳሉት፤ በተለይ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በሁለቱ አገሮች መካከል እየተፈጠረ ያለው መቃቃር በጋዜጠኞቹ ላይ በሚሰጠው ብይንም ሆነ የመጨረሻ ...
Read More »የቀድሞው የአንድነት ፓርቲ ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር የነበሩት ኢ/ር ግዛቸው ሽፈራው፤ ከፓርቲ አመራርነት እራሳቸውን አገለሉ
ታህሳስ 05 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ኢንጂነር ግዛቸው ይህን ያስታወቁት፤ ባለፈው እሁድ በዲ.አፍሪክ ሆቴል ብርሃን ለአንድነትና ለዲሞክራሲ እና አንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲዎች በይፋ ውህደት በፈፀሙበት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ነው። ኢንጂነር ግዛቸው በዕለቱ ለውህዱ ፓርቲ የብሄራዊ ምክር ቤት አባል ዕጩ ሆነው ቢቀርቡም፦ ‘‘እኔ የፖለቲካ ኃይሌ ከውስጤ ተሟጥጦ ስላለቀ፤ የብሄራዊ ምክር ቤት አባልም ሆነ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ሆኜ መቀጠል አልችልም’’ ማለታቸው ...
Read More »