በሆላንድ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የኔሰው ገብሬን ለመዘከር የሻማ ማብራት ስነስርአት ያደርጋሉ

07 ቀን 2004 /

ኢሳት ዜና:-ኢትዮጵያኑ እሁድ ዲሰምበር 18 በአምስተርዳም ከተማ በሚያካሂዱት የሻማ ማብራት ስነስርአት ፣ የኔሰው ገብሬ ለኢትዮጵያ ህዝብ የከፈለውን መስዋትነት በመዘከር፣ በውጭ የሚገኘው ኢትዮጵያዊ በአገሩ ጉዳይ ላይ ስለሚኖረው ሀላፊነት ምክክር እንደሚደረግ የአምስተርዳም የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ሊቀመንበር አቶ ወንድወሰን ገብረህይወት ለኢሳት ገልጠዋል።

በአሪቢሞንድ ስትራት ከሰአት በሁዋላ 5 ፒኤም በሚደረገው ስነስርአት ላይ የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅት ተወካዮች፣ የመገናኛ ብዙሀን ወኪሎችና የሲቪክ ማህበረሰብ አባላት ንግግር ያደርጋሉ።

በሆላንድ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በስፍራው ተገኝተው የኔሰው ገብሬን እንዲዘክሩ ሊቀመንበሩ ጥሪ አቅርበዋል።