.የኢሳት አማርኛ ዜና

በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ውስጥ የሚደረገው ቅነሳ ሁለት ብሄሮችን ማእከል ያደረገ ነው ሲሉ የሰራዊት አባላት ገለጡ

ታህሳስ 16 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ አባላት ለኢሳት የአዲስ አበባ ወኪል እንደገለጡት በሰራዊቱ ውስጥ፣ የብሄር ተዋጽኦን ለመቀነስ ተብሎ እየተወሰደ ባለው እርምጃ እንዲቀነሱ የሚደረጉት በብዛት የአማራ እና የኦሮሚያ ክልል ተወላጆች ናቸው። የመከላከያ ሚኒስትር የሆኑት አቶ ሲራጅ ፈርጌሳ የሰራዊቱን የብሄር ተዋጽኦ ለመጠበቅ መንግስት የማመጣጠን ስራ እየሰራ ነው በማለት ለፓርላማ መናገራቸው ተከትሎ፣ አባላቱ እንደገለጡት፣ የሰራዊቱን ተዋጽኦ ለማስተካካል በሚል ሽፋን አገዛዙን ...

Read More »

በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ንብረት አውድመዋል የተባሉ 52 ተማሪዎች ተቀጡ

ታህሳስ 16 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ተማሪዎች እርምጃ የተወሰደባቸው በግቢው ውስጥ ተከስቶ የነበረውን በሽታ ምክንያት በማድረግ ረብሻ አስነስተዋል ተብሎ ነው። ከ50 ተማሪዎች ውስጥ 22ቱ በአንደኛ ደረጃ ጥፋተኝነት ተፈርጀው ለአንድ ዓመት ከትምህርታቸው እንዲገለሉ ሲደረግ ፣ 18ቱ ደግሞ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል፡፡ ተማሪዎች ላወደሙት ንብረት ተጠያቂ እንደሆኑና እንዲከፍሉ ታዘዋል። ገንዘቡን ካልከፈሉ የትምህርት ማስረጃቸው የማይሰጣቸው ሲሆን፣ ከዚህ በኋላም በማንኛውም ዓይነት ጥፋት ውስጥ ቢሳተፉ ያለምንም ...

Read More »

የግብጽ፣ የሱዳንና የኢትዮጵያ ልኡካን በአባይ ግድብ ዙሪያ ለመምከር በካይሮ ተሰብስበዋል

ታህሳስ 16 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ስብሰባው የሚካሄደው በግብጽ የውሃና መስኖ ልማት ሚኒሰትር ሂሻም ቃንዲል፣ በኢትዮጵያ የውና ሀይል ልማት ሚኒስትር አለማየሁ ተገኑ እና በሱዳኑ የመስኖና ውሀ ልማት ሚኒሰትር ካሚል አሊ ሙሀመድ ጋር ኔቬምበር 29 ተደርጎ በነበረው ስምምነት መሰረት ነው። በስብሰባው ላይ ከሶስቱም አገሮች የተውጣጡ ኤክሰፐርቶች ይሳተፋሉ ተብሎአል። ስብሰባው የአባይን ግድብ በማስቀጠልና ባለማስቀጠል ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል ተብሎ ይታመናል። የመለስ መንግስት አዲስ ...

Read More »

የፍትህ ጋዜጠኞችን ማዋከብ ቀጥሏል

ቅዳሜ ታህሳስ 14 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና፡- የሳምንታዊው ፍትህ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ተመስገን ደሳለኝ፣ የጋዜጣው አዘጋጆች፣ ሪፖርተሮች እና የጋዜጣው ሠራተኞች ከዛሬ 7፡00 ሰዓት ጀምሮ ጠንከር ወዳለ ሁለተኛ ዙር የደህንነት ሠራተኞች ክትትልና ቁጥጥር ሥር መውደቃቸውን የጋዜጣው ምንጮቻችን አስታወቁ፡፡ የሣምንታዊው ፖለቲካዊ ፍትህ ጋዜጣ ባልደረቦች ከዕረቡ ታህሳስ 11 ቀን 2004 ዓ.ም ከሰሃት በኋላ ጀምሮ የጋዜጣው ቢሮ እና ቀበና አካባቢ የሚገኘው የዋና አዘጋጁ  ...

Read More »

መንግስት የሚያሰለጥናቸው የአህባሽ የእስልምና አስተምህሮ ተከታዮች ወደ ሀይል እርምጃ እየገቡ ነው በወረታ አንድ ሰው ገድለዋል

ታህሳስ 14 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በመንግስት ከፍተኛ በጀት ተመድቦላቸው እና ስልጠና ተሰጥቶአቸው የሚንቀሳቀሱት የአህባሽ የእስልምና አስተምሮ ተከታዮች የሌሎች አስተምህሮ ተከታዮችን ለማጥፋት ሰፊ ዘመቻ በማካሄድ ላይ መሆናቸውን የተለያዩ የእስልምና አስትምህሮ ተከታዮች ለኢሳት ገልጠዋል። በአማራ ክልል በባህርዳር ከተማ መንግስት አሰልጥኖ ያሰማራቸው የአህባሽ ተከታዮች የአልሱና እምነት ተከታዮችን ለማጥፋት ዘመቻ መክፈታቸውን በአደባባይ ሲናገሩ መሰማቱን አንዳንድ ሙስሊሞች ለኢሳት ተናግረዋል። የአህባሽ ተከታዮች ጥቅምት 1 ቀን ...

Read More »

‹‹አራት ኪሎ የፀደቀ የኢትዮጵያ ሕግ መርካቶን ማስተዳደር አይችልም፤›› ሲሉ የአቶ መለስ ዜናዊ የህግ አማካሪ የነበሩ ሰው ተናገሩ

ታህሳስ 14 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት የነበሩትና በአሁኑ ወቅት የህግ ስርአት ምርምር ተቋም ዳይሬክተር የሆኑት አቶ መንበረጸሀይ ታደሰ መቀሌ ተደርጎ በነበረው የሰብአዊ መብቶች ቀን በአል ላይ ባቀረቡት ጽሁፍ “ኢትዮጵያ ውስጥ  ፍትህ የሚባል ነገር ጠፍቷል፤ ገንዘብ ያለው ሰው እውነት ባይኖረውም፣ እውነት የያዘውን ሰው እያሸነፈው” ሲሉ ገለጡ የመንግስት ባለስልጣናትን ሳይቀር ያስደነገጠ ንግግር ያቀረቡት የጠቅላይ ሚኒስትሩ የአንድ ...

Read More »

ፍርድ ቤት በእነ ኤልያስ ክፍሌ የክስ መዝገብ በሽብርተኝነት ወንጀል በተከሰሱት የመከላከያ ምሥክሮችን ትላንት አደመጠ

ታህሳስ 13 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የፌዴራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ሦስተኛ ወንጀል ችሎት በእነ ኤልያስ ክፍሌ የክስ መዝገብ በሽብርተኝነት ወንጀል በተከሰሱት የፖለቲካ ፓርቲ የአመራር አባል አቶ ዘሪሁን ገብረእግዚሃብሄር፣ የአውራምባ ታይምስ ምክትል ዋና አዘጋጅ ውብሸት ታዬ፣ ጋዜጠኛ ርዮት ዓለሙ እና ሂሩት ክፍሌ ላይ የመከላከያ ምሥክሮችን ትላንት አደመጠ፡፡ አርቲስት ደበበ እሸቱ የርእዮት ዓለሙ የመጀመሪያ ተከላካይ ምሥክር ሆኖ ርዮትን ከኢትየጵያን ሪቪዩ ...

Read More »

የፍትህ ጋዜጣ ቢሮ እና የዋና አዘጋጁ ቤት አሁንም በደህንነት ሀይሎች እንደተከበበ ነው

ታህሳስ 13 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የደህንነት ሀይሎች ከትናንት በስቲያ ከቀኑ 5 ሰአት ጀምሮ የፍትህን ቢሮ እና የዋና አዘጋጁን የተመስገን ደሳለኝን መኖሪያ ቤት መክበባቸው ታውቋል የአዘጋጁን የሀይለመስቀል ባሸዋምየለህን ስልክ ሲም ካርድ አውጥተው በመውሰድና ማንነቱን የሚያንቋሽሽ ስድብ ከመስደብ ውጭ ፣ የደህንነት ሰራተኞቹ ጋዜጠኞችን ለማሰርም ሆነ ለመደብደብ ሙከራ አላደረጉም። ይሁን እንጅ ጋዜጠኞቹ ከፍተኛ የስነ ልቦና ጫና የደረሰባቸው በመሆኑ ስራቸውን ተረጋግተው ለመስራት አልቻሉም። ...

Read More »

የአንድነት ፓርቲ ፕሬዝዳንት በመሆን በጠቅላላ ጉባኤ የተመረጡት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ፓርቲውን የሚመሩ የካቢኔ አባላት እንደሚያቀርቡ አስታወቁ

ታህሳስ 13 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአንድነት ለፍትህና ዴሞክራሲ ፓርቲ (አንድነት) ፕሬዝዳንት በመሆን በጠቅላላ ጉባኤ የተመረጡት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ፓርቲውን የሚመሩ አስር አባላት ያሉትን የካቢኔ አባላት   ቅዳሜ እንደሚያቀርቡ አስታወቁ።  ለኢሳት የደረሰው መረጃ እንደሚያመለክተው፤አዲሱ ፕሬዚዳንት ነገ ታህሳስ 14 ቀን  በሚካሄደው የፓርቲው ብሔራዊ ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ፓርቲውን የሚመሩ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት (ካቢኔ) መርጠው በመለየት ለብሔራዊ ምክር ቤቱ ያቀርባሉ። ከዚህ ጎን ...

Read More »

በጋሞጎፋ ዞን በጨንቻ ወረዳ ነዋሪ የሆኑ አርሶ አደሮች መሬታቸው ያለ አግባብ በመነጠቁ ከመንግስት ጋር ግጭት ውስጥ ገቡ

ታህሳስ 13 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል በጋሞጎፋ ዞን በጨንቻ ወረዳ ነዋሪ የሆኑ አርሶ አደሮች መሬታቸው ያለ አግባብ በመነጠቁ ሳቢያ ከመንግስት ሹመኞችና ፖሊሶች ጋር ግጭት ውስጥ ገቡ። አርሶ አደሮቹ  ወደ ግጭት ለመግባት የተገደዱት፤”የጨንቻ ከተማን ለማስፋት” በሚል ሰበብ እየተካሄደ ባለው የከተማ ማካለል ስራ፤ ከይዞታቸው አላግባብ ሊፈናቀሉ እንደሚችሉ በመገንዘባቸው እንደሆነ ተናግረዋል። ሰንደቅ እንደዘገበው፤በከተማዋ ዙሪያ የሚኖሩ አርሶአደሮች የከተማዋን መስፋፋት ...

Read More »