የግብጽ፣ የሱዳንና የኢትዮጵያ ልኡካን በአባይ ግድብ ዙሪያ ለመምከር በካይሮ ተሰብስበዋል

16 ቀን 2004 /

ኢሳት ዜና:-ስብሰባው የሚካሄደው በግብጽ የውሃና መስኖ ልማት ሚኒሰትር ሂሻም ቃንዲል፣ በኢትዮጵያ የውና ሀይል ልማት ሚኒስትር አለማየሁ ተገኑ እና በሱዳኑ የመስኖና ውሀ ልማት ሚኒሰትር ካሚል አሊ ሙሀመድ ጋር ኔቬምበር 29 ተደርጎ በነበረው ስምምነት መሰረት ነው።

በስብሰባው ላይ ከሶስቱም አገሮች የተውጣጡ ኤክሰፐርቶች ይሳተፋሉ ተብሎአል።

ስብሰባው የአባይን ግድብ በማስቀጠልና ባለማስቀጠል ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል ተብሎ ይታመናል።

የመለስ መንግስት አዲስ የግብጽ መንግስት እስከሚመሰረት ድረስ በአባይ ላይ ምንም አይነት እንቅስቃሴ ላለማድረግ ስምነት መፈረሙ ይታወሳል።

ግብጽና ሱዳን የግድቡን ግንባታ አንቀበልም ካሉ ኢትዮጵያ መንግስት ስለሚወስደው እርምጃ የታወቀ ነገር የለም።

መንግስት ከህዝብ በሚዋጣ ገንዘብ አባይን ለመገደብ እንደማይቻል በማወቁ፣ የግብጽና ሱዳንን ድጋፍ በማግኘት፣ እርዳታ ለማፈላለግ ሙከራ እንደሚያደርግ የፖለቲካ ተንታኞች ይናገራሉ።