.የኢሳት አማርኛ ዜና

በዋሽንግተን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የሻማ መብራት ስነስርአት አካሄዱ

ታህሳስ 24 ቀን 2004 ዓ/ ም ኢሳት ዜና:-በ”ማርች ፎር ፍሪደም”ና በሌሎች የሰብአዊ መብት ድርጅቶች አስተባባሪነት በየወሩ በአሜሪካን ፕሬዚዳንት መኖሪያ ፊት ለፊት የሚካሄደውና በኢትዮጵያ የታሰሩ ፖለቲከኞችና ጋዜጠኞችን የሚያስበው የሻማ ማብራት ስነስርአት በሞቀ ሁኔታ ተካሂዷል።  እስክንደር ነጋ እና አንዱአለም አራጌን ጨምሮ ሌሎች ጋዜጠኞችና የፖለቲካ ድርጅት መሪዎች  ከታሰሩበት ጊዜ ጀምሮ፣ ለሶስተኛ ግዜ በተካሄደው የሻማ ማብራት ስነስርአት ላይ አያሌ በዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ...

Read More »

በሱዳን የሚገኙ ኢትዮጵያን አቶ በረከት ስምኦን ወደ ሱዳን መጥተው ከተመለሱ በሁዋላ፣ የሚደርስብን እንግልት ጨምሮአል ይላሉ

ታህሳስ 24 ቀን 2004 ዓ/ ም ኢሳት ዜና:-ስደተኞች እንደሚሉት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ኢትዮጵያውያን ፓስፖርታቸውን እየተጠየቁ በመንገላታት ላይ ናቸው። ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ስደተኛ ፓስፖርት ከሌለው ስራ መስራት አይችልም የሚል መመሪያ መውጣቱን ስደተኞች ይናገራሉ። አላማው በሱዳን  የሚገኙ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ስደተኞችን ወደ አገራቸው ለመመለስ የሱዳን መንግስት ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ያደረገው ስምምነት መሆኑን ስደተኞች ይናገራሉ። በሱዳን የሚገኙ ስደተኞች የሚደርስባቸውን በደል በተመለከተ በተደጋጋሚ አቤቱታ እንደሚያሰሙ ቢታወቅም፣ ...

Read More »

ሶማሊያ የገባው የኢትዮጵያ ጦር ከአልሸባብ ጋር የሚያደርገው ጦርነት እንደቀጠለ ነው

  ታህሳስ 24 ቀን 2004 ዓ/ ም ኢሳት ዜና:-ባለፈው ቅዳሜ በለደወይን የምትባለውን የሶማሊያን  ግዛት ከአልሸባብ እጅ መልሶ የነጠቀው የኢትዮጵያ ጦር በሚቀጥሉት ቀናት ከአልሸባብ ተዋጊዎች ብርቱ ፍልሚያ ይጠብቀዋል ሲሉ የመገናኛ ብዙሀን እየዘገቡ ነው። ወል ስትሪት ጆርናል እንደዘገበው አልሸባብ በበለደወይን አጎራባች ስፍራዎች  ላይ የነበሩትን ተጠባባቂ ወታደሮቹን ወደ ከተማዋ በማስጠጋት ከኢትዮጵያ ጋር ለመዋጋት ዝግጅት እያደረገ ነው። በሌለ በኩል የኬንያ ጦር የአልሸባብን የኢኮኖሚ ምንጭ ...

Read More »

በጄኔራል ከማል ገልቹ የሚመራው የኦሮሞ ነጻ አውጭ ግንባር (ኦነግ) የመገንጠል አጀንዳውን ሰርዞ ለአዲስ ኢትዮጵያ ግንባታ እንደሚታገል አስታወቀ

ታህሳስ 23 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት:- ድርጅቱ በፈረንጆች አቆጣጠር ዲሰምበር 30 እና 31 ባደረገው ጉባኤ ፣ ለረጅም አመታት ሲታገልበት የነበረውን የመገንጠል አጀንዳ በመሰረዝ ፣ የኢትዮጵያን ህዝብ ፍላጎትና ጥያቄ የሚመልስ የመታገያ አጀንዳ ማሻሻያ ማድረጉን አስታውቋል። ግንባሩ ሁሉም የኦሮሞ እና ሌሎችም የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ሀይሎች ይህን አዲስ ራእይ እውን ለማድረግ በጋራ እንዲሰሩ  ጥሪ አቅርቧል። የድርጅቱ ጉባኤ ከመካሄዱ ጥቂት ቀናት በፊት በአቶ ዳውድ ኢብሳ ...

Read More »

አቶ መለስ ዜናዊ ዲሞክራሲን ለመገንባት የገቡትን ቃል አጥፈዋል ሲሉ አንድ የቀድሞ የአሜሪካ ዲፕሎማት ተናገሩ

ታህሳስ 23 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት:- በ1980ዎቹ መጨረሻ ላይ በአሜሪካ የአፍሪካ ጉዳዮች ተጠሪ የነበሩትና በኮ/ል መንግስቱ ሀይለማርያም ይመራ የነበረውን የኢትዮጵያን መንግስት ከ ኢህአዴግና ከሻእብያ ጋር ሲያደራድሩ የነበሩት አምባሳደር ሄርማን ኮህን፣ “መለስ ዜናዊ በምርጫ 97 የተሸነፈ ቢሆንም ፣ የህዝቡን ድምጽ ሰርቆ የመንግስት ስልጣን ይዞአል” ብለዋል። “በዚህም የተነሳ” ይላሉ አምባሳደሩ ፣ “ስልጣን ከመያዙ በፊት የገባውን ቃል አጥፏል።” አምባሳደር ኮህን ከኢሳት ጋር ባደረጉት ...

Read More »

በአዲስ አበባ የሚገኙ የመጽሀፍ አዙዋሪዎች በአቶ በረከት ስምኦን መጽሀፍ ያተረፍነው ስም ሳይሆን ስድብ ነው አሉ

ታህሳስ 23 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት:- የኢሳት የአዲስ አበባ ዘጋቢ እንደገለጠው፣ የመጽሀፍ አዙዋሪዎች የአቶ በረከትን አዲሱን “የሁለት ምርጫዎች ወግ” መጽሀፍ በተጽእኖ እንዲሸጡ ቢደረግም፣ ከመጽሀፉ ሽያጭ ያገኙት ትርፍ ስድብና ውግዘት ብቻ ነው። ዘጋቢያችን “አንዱን የመጽሀፍ አዟሪ ” በቀን ውስጥ ስንት የአቶ በረከትን መጽሀፎች ትሸጣለህ?” ብሎ ሲጠይቀው፣ ” በቀን ውስጥ ስንት ስድቦችን አተረፍክ?” ብለህ ብትጠይቀኝ ይሻለኛል” ብሎ እንደመለሰት ገልጧል። ዘጋቢያችን እንደሚለው የአዲስ ...

Read More »

የአቦሬ ገበያን ቃጠሎ ተከትሎ፣ በአካባቢው ኗሪ የነበሩ ሰዎች ጐዳና መውደቃቸውንና የወረዳ ስድስት አስተዳደርም ሕገወጥ ናችሁ በማለት ጊዜያዊ መጠለያ እንዳያገኙ ማድረጉን ተዘገበ

ታህሳስ 23 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት:- በየካ ክፍለ ከተማ በሚገኘው የአዋሬ ገበያ ከሁለት ሳምንት በፊት በተነሳ ቃጠሎ በርካታ የንግድ ቤቶችና መኖሪያዎች መውደማቸውን ተከትሎ፣ በአካባቢው ኗሪ የነበሩ ሰዎች ጐዳና መውደቃቸውንና የወረዳ ስድስት አስተዳደርም ሕገወጥ ናችሁ በማለት ጊዜያዊ መጠለያ እንዳያገኙ ማድረጉን ሪፖርተር ዘገበ ላለፉት 22 ዓመታት በአዋሬ ገበያ አካባቢ እንደኖረችና ተወልዳ ያደገችው እዚያው የወደመው ሠፈር ውስጥ እንደነበር የተናገረችው ወጣት ገበያነሽ ለማ፣ የእሷን ...

Read More »

በአየር ጤና አካባቢ የሚገኙ ሙስሊሞች እየደረሰ ያለውን ጭቆና እንደሚቃወሙ ባወጡት መግለጫና በአሰባሰቡት ፊርማ አስታወቁ

ታህሳስ 21 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአየር ጤና አካባቢ የሚገኙ ከ1 ሺ በላይ የአንሳር መስጂድ አባላት ፣ በሙስሊሞች እየደረሰ ያለውን ጭቆና እንደሚቃወሙ ባወጡት መግለጫና በአሰባሰቡት ፊርማ  አስታወቁ:: ሙስሊሞቹ ታህሳስ 16 ቀን 2004 ዓም ለኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ስራ አስፈጻሚ በጻፉት ደብዳቤ ” የህገ መንግስቱ ቁልፍ ድንጋጌዎች የሆኑት አንቀጽ 9/10/27ን በሚቃረን መልኩ የሙስሊም ዜጎችን የሀይማኖት በነጻነት ማራመድ የሚጋፉ ድርጊቶች ...

Read More »

የኢትዮጵያ ጦር በለወደይን በምትባለው የሶማሊያ ግዛት ከፍተኛ ጦርነት እያካሄደ ነው ተባለ

ታህሳስ 21 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ቢቢሲ እንደዘገበው ከ3 ሺ እስከ 5ሺ የሚገመተው የኢትዮጵያ ጦር አብዛኛውን  የበለደውይን ከተማ ተቆጣጥረዋል። የኢትዮጵያ ጦር ከባድ መሳሪያዎችን በመጠቀም ውጊያ መክፈቱንም የአካባቢው ነዋሪዎች ለቢቢሲ ገልጠዋል። በለደወይን ወደ ሞቃዲሾ የምትወስድ በኢትዮጵያ እና በሶማሊያ ድንበር መካከል የምትገኝ ስትራቴጂክ ከተማ ናት። ቢቢሲ እንደዘገበው በእስካሁ ጦርነት  20 የኢትዮጵያ ወታደሮች እና የአልሸባብ ተዋጊዎች ተገድለዋል። አልሸባብ ባለፈው ነሀሴ ወር ከሞቃዲሾ መውጣቱን ...

Read More »

የዳርፉር አማጽያን መሪ የነበሩት ዶ/ር ካህሊል ኢብራሂም በአካባቢ እና አለማቀፍ ሀይሎች ጥምረት መገደላቸውን ምክትላቸው አስታወቁ

ታህሳስ 21 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የፍትህና የእኩልነት ምክትል ሊቀመንበር የሆኑት ዶ/ር ሙሀመድ ሱሌይማን ባወጡት መግለጫ፣ መሪያቸው የተገደለው የአካባቢው ሀይሎች ከሱዳን መንግስት ጋር በጋራ በመመሳጠር ባወጡት እቅድ መሰረት መሆኑን አመልክተዋል። እነዚህ አገሮች የራሳቸውን ጥቅም ለማስከበር ሲሉ ዶ/ር ካሊልን ማስገደላቸውን የጠቀሱት ምክትላቸው፣ አሁን ባለበት ደረጃ የአገሮችን ስም ለማውጣት ባንፈቅድም፣ ከጥንስሱ ጀምሮ ያለውን እንቅስቃሴ የሚያሳይ ሙሉ መረጃ እንደደረሳቸው አመልክተዋል። ንቅናቄው ወንጀሉን የፈጸሙትን ...

Read More »