የዳርፉር አማጽያን መሪ የነበሩት ዶ/ር ካህሊል ኢብራሂም በአካባቢ እና አለማቀፍ ሀይሎች ጥምረት መገደላቸውን ምክትላቸው አስታወቁ

21 ቀን 2004 /

ኢሳት ዜና:-የፍትህና የእኩልነት ምክትል ሊቀመንበር የሆኑት ዶ/ር ሙሀመድ ሱሌይማን ባወጡት መግለጫ፣ መሪያቸው የተገደለው የአካባቢው ሀይሎች ከሱዳን መንግስት ጋር በጋራ በመመሳጠር ባወጡት እቅድ መሰረት መሆኑን አመልክተዋል።

እነዚህ አገሮች የራሳቸውን ጥቅም ለማስከበር ሲሉ ዶ/ር ካሊልን ማስገደላቸውን የጠቀሱት ምክትላቸው፣ አሁን ባለበት ደረጃ የአገሮችን ስም ለማውጣት ባንፈቅድም፣ ከጥንስሱ ጀምሮ ያለውን እንቅስቃሴ የሚያሳይ ሙሉ መረጃ እንደደረሳቸው አመልክተዋል።

ንቅናቄው ወንጀሉን የፈጸሙትን የውች ሀይሎች በአለማቀፍ ህግ መሰረት ለመጠየቅ እንደሚሰራም አስታውቋል።

የኢትዮጵያ መንግስት በዶ/ር ካሊል ግድያ ዙሪያ እጁ ሳይኖርበት እንዳልቀረ መረጃዎች እንደደረሱት መዘገቡ ይታወሳል።