.የኢሳት አማርኛ ዜና

በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ሙስሊሞች መጅሊሱ እንዲፈርስ ምርጫ እንዲደረግ በድጋሜ ጠየቁ

ጥር 11 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአወልያ ታሪክ ታይቶ አይታወቅም በተባለው በዛሬው የስግደት ቀን በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ሙስሊሞች ተገኝተዋል። ሙስሊሞቹ መጅሊስ ይፍረስ፣ ሙስሊሙ የራሱን አመራር ይምረጥ፣ አወልያ ኮሌጅ ይከፈት፣ አህባሽ ከአገራችን ይውጣ፣ የሀይማኖት ነጻነት ይከበር፣ እስልምና የሰላም ሀይማኖት ነው፣ እስልምና አሸባሪ አይደለም እና የመሳሰሉትን መፈክሮች አሰምተዋል። የአወልያ መስጊድ ግቢ በመጥበቡ ህዝቡ ከግቢው ውጭ ሲሰግድ መዋሉን በስፍራው የተገኘው ዘጋቢያችን ገልጧል። በሙስሊሙ ...

Read More »

በሽብርተኝነት ክስ የተመሰረተባቸዉ ጋዜጠኞችና የፖለቲካ መሪዎች ጥፋተኛ መባላቸውን የተለያዩ አለማቀፍ ድርጅቶች እያወገዙት ነው

ጥር 11 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በነኤልያስ ክፍሌ  የክስ መዝገብ በአሸባሪነት ተጠርጥረው በታሰሩት 3 ጋዜጠኞች ፣ ሁለት የተቃዋሚ ፖለቲካ ድርጅት አባልና ደጋፊ  ላይ የኢትዮጵያ ፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 3ኛ ወንጀል ችሎት ትናንት የጥፋነተኝነት ብይን መስጠቱ ይታወሳል ። በሌለበት ብይኑ የተላለፈበትን የEthiopian Review ድረ ገፅ ዋና አዘጋጅ ኤልያስ ክፍሌን ጨምሮ፤ የፍትህ ጋዜጣ አምደኛ ርዕዮት ዓለሙ፤ በቅርቡ ከህትመት የወጣዉ የሳምንታዊው አውራምባ ታይምስ ...

Read More »

በሶማሊያ በኢትዮጵያ ወታደሮች ተሽከርካሪ ላይ የቦምብ ፍንዳታ ደረሰ

ጥር 11 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በማእከላዊ ሶማሊያ ባላዲወይኒ ሂራን  የኢትዮጵያ ወታደሮችን ባሳፈረ ተሽከርካሪ ላይ በቅርብ ርቀት መቆጣጠሪያ / ሪሞት ኮንትሮል/ የተቀሰቀሰ የቦንብ ፍንዳታ መድረሱን ሸበሌ ሚዲያ ኔት ወርክ የዜና ወኪል ገለጸ። በተሽከርካሪዉ ላይ በተጫኑት የኢትዮጵያ ወታደሮች ላይ የደረሰ ጉዳት አለመኖሩ የተገለፀ ሲሆን ፍንዳታዉን ተከትሎ የኢትዮጵያ ወታደሮች በአካባቢዉ በነበሩ ሰላማዊ ሰዎች ላይ በከፈቱት ተኩስ ሁለት ሰዎችን ሲገድሉ አምስት ሰዎችን ማቁሰላቸዉን ...

Read More »

ኢትዮጵያዊዉ ቤተ እስራኤላዊ ባለቤቱን በስለት ገድሎ እራሱን ሰቅሎ አጠፋ

ጥር 11 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ላዋካ አማራ የተባለዉ የ37 አመት ኢትዮጵያዊ ቤተ እስራኤላዊ የ32 አመት እድሜ ያላትን የሶስት ልጆቹን ወላጅ እናት በስለት ወግቶ በመግደል እራሱን ሰቅሎ እንዳጠፋ ሃሬትዝ የዜና ምንጭ ገለጿል። ከአምስት አመት በፊት ወደ እስራኤል የተጓዙት ሁለቱ የትዳር ጓደኞች በአንድ ትልቅ የምግብ ሸቀጣ ሸቀጥ መደብር ዉስጥ የሚሰሩ ሲሆን ለዚህ መጠፋፋት የደረሱበት የግጭት መንስኤ ምን እንደሆነ እስካሁን አልተገለፀም። እድሜያቸዉ ...

Read More »

ቀነኒሳ በቀለንና ጥሩነሽ ዲባባን ጨምሮ ታዋቂ የኢትዮጵያ አትሌቶች ከውድድር ታገዱ

ጥር 11 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ቀነኒሳ በቀለ፣ ጥሩነሽ ዲባባ፣ መሰለች መልካሙ ፣ ስለሺ ስህንና ሌሎች በአለማቀፍ ውድድሮች ከወርቅ እስከ ነሀስ ያገኙ አትሌቶች ከውድድር እንዲታገዱ የተደረገው በመጪው መጋቢት ወር በሚካሄደው አለማቀፍ የአትሌቲክስ ውድድር እና ለለንደን ማራቶን ልምምድ እንዲያደርጉ ተጠይቀው በጊዜው ሪፖርት ለማድረግ ባለመቻላቸው ነው ተብሎአል። 35 አትሌቶችን በአንድ ጊዜ ሪፖርት አላደረጉም በሚል ማገድ አሳማኝ ሆኖ አልተገኘም። አትሌቶቹ ፕሮፌሽናል እንደመሆናቸው የወድድርና ...

Read More »

የፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት በጋዜጠኞችና ፖለቲከኞች ላይ የጥፋተኝተነት ብይን አስተላለፈ

ጥር 10 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በጋዜጠኛ ኤልያስ ክፍሌ መዝገብ በተከሰሱት ፖለቲከኞች እና ጋዜጠኞች ላይ በዳኛ እንዳሻው አዳነ የተመራው ፍርድ ቤት ባስተላለፈው ውሳኔ ጋዘጠኛ ኤልያስ ክፍሌ በ4 የሽብርተኝነት ክሶች ጥፋተኛ ተብሎአል።  ፍርድ ቤቱ የኢትዮጵያ አንድነት ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ዘሪሁን ገብረእግዚአብሄር፣ የአውራምባ ታይምስ ምክትል ዋና አዘጋጅ የነበረውን ጋዜጠኛ ውብሸት ታየ፣ መምህርትና የፍትህ ጋዜጠኛ አምደኛ የሆነችውን ርእዮት አለሙን እና ሂሩት ክፍሌን በሶስት ...

Read More »

ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በሽብር ፈጣሪው የኤርትራ መንግስት ላይ የማያዳግም ርምጃ ካልወሰደ የኢትዮጵያ መንግስት አስመራ ውስጥ ያለውን መንግስት የመከላከል ሕጋዊ ርምጃ ለመውሰድ ይገደዳል ሲል የመለስ መንግስት አስታወቀ

ጥር 10 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ማበወጣው መግለጫ የኢትዮጵያ መንግስት በአሁኑ ጊዜ የኤርትራ መንግስት የሚያካሂዳቸውን የሽብር ድርጊቶችና ለአሸባሪዎች የሚሰጠውን እርዳታ መታገስ የማይችልበት ደረጃ ላይ ደርሷል ብሏል፡፡፡ የኤርትራ መንግስት ያሰማራቸውአሸባሪዎች በአፋር ክልል የሚገኙ የቱሪስት መስህቦችን በመጎበኘት ላይ በነበሩ 27 ቱሪስቶች ላይ ከትናንትበስቲያ ጥቃት ማድረሳቸውንና አምስቱ መገደላቸውን ሚኒስቴሩ አስታውሷል። የሽብር ጥቃቱ ከአንድ ዓመት በፊት በአዲስ አበባ የተካሄደውን የአፍሪካ ህብረት ...

Read More »

“የመኢአድ አባል የሆነ ሁሉ ይታሰራል እየተባለ ነው” ሲል መኢአድ ገለጸ

ጥር 10 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በተለየ መልኩ በደቡብ ክልል በመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት(መኢአድ) አባላት ላይ እየተፈፀመ ያለው የሰብዓዊ መብት ረገጣ እየከፋ በመምጣቱ ፤  የዘንድሮ ጠቅላላ ጉባኤውን  እዚያው ክልል ውስጥ ለማድረግ መወሰኑን ፓርቲው አስታወቀ። መኢአድ በመግለጫው እንዳለው፤ ጠቅላላ ጉባዔውን በክልሉ ማካሄድ ያስፈለገው፤ በክልሉ በሚገኙ የድርጅቱ አባላት ላይ ኢህአዴግ የሚያደርሰው ጭቆና እየበረታ በመምጣቱ፤ ጭቆናውን በህጋዊ መንገድ እንዴት መግታት እንደሚቻል ውሳኔ ለማሳለፍ ...

Read More »

የኢጋድ አባል አገራት “ወንጀለኞችን አሳልፎ የመስጠት ስምምነት “ መፈራረማቸውን ተከትሎ ኡጋንዳ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ከፍ ያለ ስጋት ውስጥ መውደቃቸውን ገለጹ

ጥር 10 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ሰሞኑን የ ኢጋድ አባል አገራት “ወንጀለኞችን አሳልፎ የመስጠት ስምምነት “ መፈራረማቸውን ተከትሎ  በተለይ በ ኡጋንዳ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ፖለቲከኞች፣ ጋዜጠኞችና አክቲቪስቶች ከፍ ያለ ስጋት ውስጥ መውደቃቸውን ገለጹ። በአቶ መለስ መንግስት ግንባር ቀደም ፊታውራሪነት  ሁሉም  የኢጋድ አገሮች እንዲፈረም ግፊት እየተደረገበት ያለውና ሥራ ላይ ለመዋል ጥቂት ሳምንታት የቀረው ይህ ስምምነት  ዋነኛ ዓላማው፤ በጎረቤት አገር የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ተቃዋሚዎችን ...

Read More »

“ክዋክብት ኢንተርናሽናል” የተሰኘ አማካሪ ድርጅት ጋዜጣ የማሳተም ፈቃድ መከልከሉን ፍትህ ጋዜጣ ዘገበ የአቶ በረከት ግብረ-ሀይል የጋዜጣ ፈቃድ መስጠት አቁሜያለሁ አለ

  ጥር 10 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ  እንዳሉት፤በሀገሪቱ የነፃ ጋዜጣ ህትመት ስራ ዙሪያ ረጅም ጊዜ የወሰደ ምልከታና ጥናት በማካሄድ በቅርቡ‹‹ርግብ›› በሚል ስያሜ ሳምንታዊ ጋዜጣ ለማሳተም አስፈላጊ ዝግጅቶችን አጠናቅቀው እና አስፈላጊ ነገሮችን አሟልተው ከኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን የምዝገባ ምስክር ወረቀት ለማግኘትያቀረቡት ጥያቄ ከሁለት ወራት በላይ ምላሽ ሊያገኝ አልቻለም። ለዚህም የሚሰጠው ምክንያት ፦” በቅድሚያ የድርጅቶቹን ባለቤቶች ማንነት ማጥናት አለብን”የሚል እንደሆነ ...

Read More »