.የኢሳት አማርኛ ዜና

አርዱፍ 2ቱን ጀርመኖች የጠለፍኳቸው እኔ ነኝ አለ። ግለሰቦቹ በጥሩ ሁኔታ እንደሚገኙም ገልጧል

ጥር 14 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአፋር አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት ግንባር ( አርዱፍ) 2ቱን ጀርመኖች የጠለፍኳቸው እኔ ነኝ አለ። ግለሰቦቹ በጥሩ ሁኔታ እንደሚገኙም ገልጧል። የአፋር አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ ግንባርን በመጥቀስ ረዩተርስ እንደዘገበው፤ ቱርስቶቹ የተገዱለት በኢትዮጵያ ወታደሮች ነው በማለት ግንባሩ ለሟቾቹ የ ኢትዮጵያን መንግስት ተጠያቂ አድርጓል። በአካባቢው የአርዱፍ ግብረሀይል ቅኝት በማድረግ ላይ ሳለም፤ ከኢትዮጵያ መንግስት ጦርነት እንደተከፈተበት -ግንባሩ ገልጧል። በተኩሱ ልውውጥ መሀል ...

Read More »

የአቶ መለስ መንግስት ኤርትራን ለመውጋት እየተዘጋጀ ነው ሲል ደብረብርሀን ብሎግ ዘገበ

ጥር 14 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ብሎጉ እንደዘገበው ፤ሰሞኑን የመከላከያ ኢንጄነሪንግ ኮሌጅ ሲቪል ሰራተኞች በግዴታ እረፍት እንዲወስዱ ታዘዋል። ብሎጉ በማያያዝም፦”ለተለያዩ የኮሌጁ ሰራተኞችም የደሞዝ ጭማሪ ተደርጎላቸዋል። እንዲህ አይነት ሁኔታዎች የሚከሰቱት አገሪቱ ለጦርነት ስትዘጋጅ ነው”ሲል ምንጮቹን ጠቅሶ ዘግቧል። በሌላ በኩል መንግስት አንዳንድ የአዲስ አበባ የቀበሌ ነዋሪዎችን ኤርትራ በወሰደችው እርምጃ ዙሪያ እያወያየ ነው። የአፋር ህዝብ ባወጣው መግለጫ ደግሞ መንግስት ከኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት በሁዋላ ...

Read More »

“የሰብኣዊ መብት ሁኔታና ኢትዮጵያ የምትጫወተዉ አፍራሽ ሚና “ በሚል ርዕስ በለንደን ኮንፈረንስ ተካሄደ

ጥር 14 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:- “እያሽቆለቆለ በመሄድ ላይ ያለዉ የምስራቅ አፍሪቃ የሰብኣዊ መብት ሁኔታና ኢትዮጵያ የምትጫወተዉ አፍራሽ ሚና “ በሚል ርዕስ በለንደን ኮንፈረንስ ተካሄደ በምስራቅ አፍሪቃ ከጊዜ ወደ ጊዜ ከመሻሻል ይልቅ ይበልጥ እያሽቆለቆለ በመሄድ ላይ ባለዉ የሰብኣዊ መብት ሁኔታና በተለይም በኢትዮጵያ የሚገኘዉ የጠ/ሚር መለስ ዜናዊ መንግሰት የሚከተለዉ የተሳሳተ አቅጣጫ በአፍሪቃ ቀንድ ያለዉን ችግር እንዳወሳሰበው በስብሰባው ተገልጧል። በለንደን የአምነስቲ ...

Read More »

ከ80 ሺ በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን በረሀብ ልናልቅ ነው ይላሉ

ጥር 14 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በሶማሊ ክልል በመንግስት የጸጥታ ሀይሎች በደረሰባቸው የሀይል ጥቃት የተነሳ ወደ ኦሮሚያ ክልል መሰደዳቸውን የገለጡ 80 ሺ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን፣ በቂ የሆነ የምግብ እርዳታ ስላልቀረበላቸው በቀን አራትና አምስት ሰዎች እየሞቱባቸው እንደሆነ ተናገሩ። ቁጥራቸው ከ300 ሺሕ በላይ የሆነውና በሶማሌ ክልል ይኖሩ የነበሩት የፊቅ ዑመር  ወይም የሸካሽ  ጎሳ ማኅበረሰብ አባላት በቂ እህልና ውሀ እንዲቀርብላቸው በተደጋጋሚ መንግስትን  ሲጠይቁ ቆይተዋል። ...

Read More »

በኦሮሚያና በሶማሊ ክልሎች በመጪዎቹ ስድስት ወራት ከፍተኛ የምግብ እርዳታ ያስፈልጋል ተባለ

ጥር 12 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ መንግስት በሚቀጥሉት ስድስት ወራት ከሶስት ሚሊዮን በላይ የሚሆን ህዝብ አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ያስፈልገዋል ብሎአል። የአለማቀፍ የእርዳታ ድርጅቶች በበኩላቸው መንግስት አሁንም የተረጂዎችን ቁጥር ቀንሶ አቅርቧል ይላሉ። የኢትዮጵያ መንግስት ያወጣው ቅድመ ማስጠንቀቂያ አሀዝ እንደሚያሳየው በመጪዎቹ ስድስት ወራት ከ365 ሜትሪክ ቶን በላይ የምግብ እርዳታ የሚያስፈልግ ሲሆን፣ አብዛኛው በኦሮሚያ እና በሶማሊ ክልሎች የሚከፋፋል ነው ብሎአል። ከተረጅዎች ውስጥ ...

Read More »

በአለፈው አመት ከመንግስት አልባዋ ሶማሊያ ይልቅ በርካታ ኢትዮጵያውያን ወደ የመን ተሰደዋል

ጥር 12 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-መንግስት አልባዋ ሶማሊያ ለአለፉት 10 አመታት ስደተኞችን በማምረት በኩል የሚስተካካላት አልነበረም፡ አሁን ግን ይህን ሪኮርድ ኢትዮጵያ ውስዳለች። ረዩተር ባወጣው ዘገባ በአሳለፍነው የፈረንጆች አመት በሪከርድነት የተመዘገበ 103 ሺ ኢትዮጵያውያን እና ሶማሊያውያን በሰላም እጦት አደጋ ውስጥ ወዳለችው የመን አቀንተዋል። ከእነዚህ ስደተኞች መካከል ከአራቱ እጅ ሶስቱ ወይም ከ77 ሺ በላይ የሚሆኑት ኢትዮጵያዊ  ቀሪዎቹ 25 ሺ ደግሞ ሶማሊያውያን ...

Read More »

ኦብነግ የኢትዮጵያ መንግስት ወታደሮች በአካባቢው ነዋሪዎች ላይ የሚያደርሱት ወቅታዊ ጥቃት ተከላከልኩ ሲል አስታወቀ

ጥር 12 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኦጋዴን ነጻ አውጭ ድርጅት ወታደራዊ መግለጫ እንደማለከተው የመንግስት የጸጥታ ሀይሎች በየወቅቱ የሚያደርጉትን ህዝቡን የማስፈራራትና ማዋከብ ዘመቻ ጀምረዋል። በዋርዴር ቀብሪ ደሀርና ደገሀቡር አካባቢዎች የሚገኘው የመከላከያ ሰራዊት የአካባቢውን እያመሰነ ነው ሲል ገልጧል። ግንባሩ ሂጋን በተባለው አካባቢ ከኢትዮጵያ ወታደሮች ጋር ባደረገው የተኩስ ልውጥጥ 50 ገድሎ 70 ማቁሰሉን ገልጧል። 5 ቢኬኤም ከባድ ጠመንጃዎችን፣ 40 የነፍስ ወከፍ መሳሪያዎችን ከወታደሮች ...

Read More »

በ35 አትሌቶች ላይ የወሰደው የእግድ እርምጃ ለአመታት ሲንከባለሉ የቆዩትን ችግሮች ለማስተንፈስ ተብሎ የተወሰደ ሊሆን እንደሚችል ተናገረ

ጥር 12 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በ35 አትሌቶች ላይ የወሰደው የእግድ እርምጃ ለአመታት ሲንከባለሉ የቆዩትን ችግሮች ለማስተንፈስ ተብሎ  የተወሰደ ሊሆን እንደሚችል አንድ ታዋቂ የስፖርት ጋዜጠኛና ተንታኝ ተናገረ በስፖርት ተንታኝነቱ የሚታወቀው ኤርምያስ አማረ ለኢሳት እንደገለጠው በኢትዮጵያ አትሌቲክ ፌዴሬሽን ውስጥ የሚታዩት ችግሮች ለረጅም ጊዜ የዘለቁና ሲሸፋፈኑ የቆዩ ናቸው። ኤርምያስ ወና ዋና ችግሮች የሚላቸው ፌደሬሽኑን፣ አትሌቶችንና አሰልጣኞችን የሚመለከቱ ናቸው የአትሌቲክስ ...

Read More »

በኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ዘንድ የሚከበረው የጥምቀት በአል ዘንድሮም በደመቀ ሁኔታ ተከብሯል።

ጥር 11 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በየአመቱ ከጥር 10 እስከ  ጥር 11 በኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ዘንድ የሚከበረው የጥምቀት በአል ዘንድሮም በደመቀ ሁኔታ ተከብሯል። ታቦታቱ በአዲስ አበባ በ16 ቦታዎች ያደሩ ሲሆን፣ በዛሬው እለት ከቅዱስ ሚካኤል ታቦት በስተቀር ሁሉም ወደ መጡበት ተመልሰዋል። በጎንደር በአሉ የካርኒባል በአል የሚል ስያሜ ተሰጥቶት ለአንድ ሳምንት እንደሚከበር ታወቋል።

Read More »