አርዱፍ 2ቱን ጀርመኖች የጠለፍኳቸው እኔ ነኝ አለ። ግለሰቦቹ በጥሩ ሁኔታ እንደሚገኙም ገልጧል

ጥር 14 ቀን 2004 ዓ/ም

ት ዜና:-የአፋር አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት ግንባር ( አርዱፍ) 2ቱን ጀርመኖች የጠለፍኳቸው እኔ ነኝ አለ። ግለሰቦቹ በጥሩ ሁኔታ እንደሚገኙም ገልጧል።

የአፋር አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ ግንባርን በመጥቀስ ረዩተርስ እንደዘገበው፤ ቱርስቶቹ የተገዱለት በኢትዮጵያ ወታደሮች ነው በማለት ግንባሩ ለሟቾቹ የ ኢትዮጵያን መንግስት ተጠያቂ አድርጓል።

በአካባቢው የአርዱፍ ግብረሀይል ቅኝት በማድረግ ላይ ሳለም፤ ከኢትዮጵያ መንግስት ጦርነት እንደተከፈተበት -ግንባሩ ገልጧል።

በተኩሱ ልውውጥ መሀል 4ቱ የውጭ አገር ዜጎች በኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ተገድለዋል ብሎአል-አርዱፍ።

አክሎም ከግንባሩ ጋር በእለቱ በተካሄደው የተኩስ ልውውጥ  16 የኢትዮጵያ ወታደሮችም ተገድለዋል ብሎአል።

በቁጥጥሩ ስር ያሉት ጀርመናውያን እና ኢትዮጵያውያን በጥሩ ሁኔታ የሚገኙ መሆኑን የገለጠው አርዱፍ ፣ ሰዎችን በሽምግልና ለማስለቀቅ ሙከራ እየተደረገ መሆኑንም አስታውቋል።

ግንባሩ ኤርትሪያ በጠለፋውም ሆነ በግድያው፤ እጇ የለበትም ሲልም የ ኢትዮጵያን መንግስት ክስ አጣጥሏል ።

አርዱፍ በኢትዮጵያ፣ በኤርትራ እና በጂቡቲ የሚገኙ አፋሮችን አንድነት ለመመስረት የሚታገል ድርጅት ነው።