መጋቢት ፳፱ (ሃይ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በደቡብ ክልል በሲዳማ ዞን በጩኮ ወረዳ ማንጉዶ ቀበሌ በግብርና ስራ ይተዳዳሩ የነበሩት አቶ ካሚሶ ካያሞ የቀበሌው ሊቀመንበር የይዞታ መሬታቸውን ስለቀማቸው ለተለያዩ የመንግስት አካላት አቤቱታ ቢያቀርቡም የሚሰማቸው ባለማግኘታቸው ነው ራሳቸውን አጠፉት። አርሶ አደሩ ራሳቸውን ከማጥፋታቸው በፊት መጋቢት 20 ቀን 2004ዓም ” ልጆቼና ቤተሰቤ በችጋር ሲያልቁ አላይም፣ ፍትህ የለም በግፍ መሬቴን ስለተነጠኩ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
የአፋር ሽማግሌዎች ከመሬታችን የሚለየን ሞት ብቻ ነው ይላሉ
መጋቢት ፳፰ (ሃይ ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ሰሞኑን ኢሳት በአፋር አካባቢ የሚገኙ ሰፋፊ ቦታዎችን መንግስት ለሸንኮራ አገዳ እርሻ ልማት እንደሚፈልገው ማስታወቁን ተከትሎ የአካባቢው ህዝብ ተቃውሞ ማሰማቱን መዘገቡ ይታወሳል። የህዝቡ ተቃውሞ ያሰጋው መንግስት በአካባቢው የእርሻ ስራ እየሰሩ ያሉት ዶዘሮች በልዩ ሀይል እንዲጠበቁ በማድረግ የእርሻውን ስራ በጉልበት ለማካሄድ ወስኗል። የመንግስትን እርምጃ የተቃወሙ አፋሮች ተደብድበዋል ብዙዎችም ታስረዋል። ቤታችን አናፈርስም ብለው በመቃወማቸው ከታሰሩት ...
Read More »በዱባይ በአሰሪዋ ተገድላ ግቢ ውስጥ ተቀብራለች የተባለችው ወጣት እጣ ፋንታ መጨረሻው አልታወቀም
መጋቢት ፳፰ (ሃይ ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በዱባይ በአሰሪዋ ተገድላ ግቢ ውስጥ ተቀብራለች የተባለችው ወጣት እጣ ፋንታ አልታወቀም ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉት የኢትዮጵያው ዲፕሎማት መረጃ አልሰጥም ብለዋል። በዱባይ በአሰሪዋ ተገድላ ጓሮ ውስጥ ስለተቀበረችው ወጣት ኢትዮጵያ ኢምባሲ በቂ ክትትል እንዳላደረገ ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉት በዱባይ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ገልጠዋል። በተለይም አረጋሽ እየተባለች የምትጠራዋ ኢትዮጵያዊት ድርጊቱን ይፋ ካደረገች በሁዋላ አሁንም ድረስ በኢትዮጵያ ኢምባሲ ውሰጥ ...
Read More »በ2011ዓ/ም የመን የገቡት ኢትዮጵያዉያን ስደተኞች ቁጥር 65ሺህ መሆኑ ታወቀ
መጋቢት ፳፰ (ሃይ ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በየመን ኢትዮጵያዉያን ስደተኞች ከፍተኛ ችግር፤ እስራትና እንግልት እየደረሰባቸዉ መሆናቸዉን የዘገበዉ የመን ታይምስ ጋዜጣ የመንግስታቱ ድርጅት የስደተኛ ከፍተኛ ኮሚሽነርን በመጥቀስ እንደገለፀዉ እኤአ በ20110 የመን የገቡት ስደተኞች ቁጥር 34ሺህ 422 ሲሆን በ2011 ይኸዉ ቁጥር ወደ 65ሺህ ከፍ ማለቱን አመልክቷል። በ2010 ከገቡት መካከል 616 ሰዎች እስካሁን የት እንደደረሱ የማይታወቅ ተገልጿል። የየመን መንግስት ወታደሮች ህገወጥ ናቸዉ ...
Read More »የመለስ መንግስት በመሬት ሽያጭ ፖሊሲው ተደጋጋሚ ነቀፌታ ቢደርስበትም ፖሊሲውን ለመቀየር ፍላጎት አላሳያም ተባለ
መጋቢት ፳፰ (ሃይ ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ መንግሰት በአገር ዉስጥና በዉጭ የሰላ ተቃዉሞ ቢሰነዘርበትም በኢትዮጵያ አነስተኛ ድሃ ገበሬዎችን ከአያት ቅድመ አያት ይዞታቸዉ ያለፈቃዳቸዉ እያፈናቀለ መሬታቸዉን ለዉጭ ከበርቴዎች የሚያከራየዉ እጅግ አነስተኛ በሆነ አመታዊ የኪራይ ዋጋ ክፍያ እንደሆነ ሮይተርስ ገለፀ። ሮይተርስ የዜና ወኪል ይህንን ያስታወቀዉ አነስተኛ ክፍያዉን ከፍ ለማድረግ አስፈላጊ የመሰረተ ልማት አዉታሮችን ለመዘርጋት እቅድ እንዳለዉ በግብርና ሚኒስቴር ...
Read More »አቶ መለስ የላኩዋቸው ሽማግሌዎች ቃሊቲ እየተመላለሱ ነው
መጋቢት ፳፯ (ሃይ ሰባት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አቶ መለስ የላኩዋቸው ሽማግሌዎች ቃሊቲ እየተመላለሱ ነው የአቶ መለስ መንግሥት የወከላቸው ሽማግሌዎች ወደ ማረሚያ ቤት በመሄድ የፖለቲካ እሥረኛ የሆኑ ፍርደኛ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችንና ጋዜጠኞችን ይቅርታ ለማስጠየቅ የማግባባት ሙከራ ማድረግ መጀመራቸውን ለማወቅ ተችሎአል። የፍትህ ሚኒስቴር ምንጮቻችን እንደገለጹት፤ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የተወከሉ ሽማግሌዎች ወደ ማረሚያ ቤት እየተመላለሱ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አብዴፓ) ሊቀመንበርን ...
Read More »የፌዴራል አቃቤ ህግ በፍትህ ጋዜጣ ላይ አቤቱታ አቀረበ
መጋቢት ፳፯ (ሃይ ሰባት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- “ፍትህ ጋዜጣ የተከሳሾችን ቃል ብቻ በጋዜጣ በማስተናገድና ዐቃቤ ሕግ ከመንግሥት ፖለቲካዊ ጫና ነፃ ሆኖ እንደማይሰራ በማተት በህዝብ ላይ እምነት እንድናጣ አድርጎናል ሲል”የፌዴራል አቃቤ ህግ አቤቱታ አቀረበ። አቃቤ ህግ ይህን ክስ ያቀረበው፤ከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ሦስተኛ ወንጀል ችሎት ትናንት ከሰዓት በኋላ በእነአንዷለም አራጌ የክስ መዝገብ በማረሚያ ቤት ሆነው ከሚከራከሩ ስምንት ተከሳሾች ...
Read More »ኢትዮጵያውያን ለዘመዶቻቸው የላኩት ገንዘብ የኢትዮጵያ ኩባንያዎች ወደ ውጭ በመላክ ካስገኙት ገንዘብ በለጠ
መጋቢት ፳፯ (ሃይ ሰባት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ መንግስት ላለፉት 7 አመታት 11 በመቶ የኢኮኖሚ እድገት እንዳገኘ በተደጋጋሚ መናገሩ ይታወቃል። የአለማቀፍ የገንዘብ ተቋም ወይም አይኤም ኤፍ የኢትየጵያ እድገት የተጋነነ ነው በማለት እድገቱ ከ6 እስከ 7 በመቶ ሊደርስ እንደሚችል በመግለጥ የመንግስትን መከራከሪያ ውድቅ ሲያድርግ ቆይቷል። ገዢው ፓርቲ የኢኮኖሚ እድገቱ የመጣው መንግስት የውጭ ንግድን ማእከል ያደረገ ፖሊሲ ቀርጾ በመንቀሳቀሱ መሆኑን ይገልጣል። ...
Read More »የኢሳትን ህልውና የማረጋገጥ ጥሪ
መጋቢት 27 ቀን 2004 ዓ/ም የኢሳት – ማኔጅመንት ኢሳት ከተቋቋመ ከዛሬ ሁለት አመት ጀምሮ ህዝባችን የሞራል የገንዘብ እና የተለያዩ እርዳታዎች በማድረጉ ይህ የህዝብ አይንና ጆሮ የሆነ የሚድያ ተቋም ዛሬ የሚገኝበት ደረጃል ለመድረስ በቅቷል። ይህም ለኢትዮጵያ ህዝብ በቀላሉ የማይዳፈን የተስፋ ብርሃን መፈንጠቅ አስችሏል። ላለፉት ሶስት ወራት የኢሳትን ወርሃዊ ወጪ በአስተማማኝ ሁኔታ ለመሸፈንና የድርጅቱን ህልውና ለመታደግ ይሆናል ብለን ያቀረብነውን የመፍትሄ ...
Read More »የአማራ ተወላጆችን በግዳጅ ወደ መጡበት ለመመለስ የሚደረገው ጥረት ተወገዘ
መጋቢት ፳፮ (ሃይ ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በደቡብ ክልል በቤንቺ ማጂ ዞን ጉራፈርዳ ወረዳ ይኖረ የነበሩ ከ20 እስከ 80 ሺ የሚጠጉ የአማራ ተወላጆች ለአካባቢው ህዝብ አደጋ ናቸው ተብለው እየተፈናቀሉ መሆናቸውን በአገር ውስጥ እና በውጭ የሚገኙ ጋዜጦች ሰፊ ትኩረት ሰጥተው በመዘገብ ላይ ናቸው። በዛሬው እለት ለንባብ የበቃው ሰንደቅ ጋዜጣ ይዞት በወጣው ዘገባ ተፈናቃዮች በግዳጅ ወደ መጡበት እየተመለሱ መሆኑን ፣ የአማራ ...
Read More »