አንድ አርሶአደር በፍትህ እጦት ምክንያት ራሳቸውን አጠፉ

 

መጋቢት ፳፱ (ሃይ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-በደቡብ ክልል በሲዳማ ዞን በጩኮ ወረዳ ማንጉዶ ቀበሌ በግብርና ስራ ይተዳዳሩ የነበሩት አቶ ካሚሶ ካያሞ የቀበሌው ሊቀመንበር የይዞታ መሬታቸውን ስለቀማቸው ለተለያዩ የመንግስት አካላት አቤቱታ ቢያቀርቡም የሚሰማቸው ባለማግኘታቸው ነው ራሳቸውን አጠፉት።

 

አርሶ አደሩ ራሳቸውን ከማጥፋታቸው በፊት መጋቢት 20 ቀን 2004ዓም ” ልጆቼና ቤተሰቤ በችጋር ሲያልቁ አላይም፣ ፍትህ የለም በግፍ መሬቴን ስለተነጠኩ ህይወቴን ለማጥፋት ተገድጃለሁ” የሚል ደብዳቤ ጽፈው እንደነበር ለማወቅ ተችሎአል።

ደብዳቤ መጻፋቸውን የተረዱት ቤተሰቦቻቸው ጥበቃ ሲያደርጉ ቢቆዩም፣ ቤተሰባቸውን ገረጋጉ በሁዋላ በጡዋት ወደ ሊቀመንበሩ መኖሪያ ግቢ በመሄድ ራሳቸውን ሰቅለው መሞታቸውን ቀብራቸውም በማግስቱ መጋቤት 21 መፈጸሙን የደረሰን ዜና ያመለክታል።

 

በኢትዮጵያ በፍትህ እጦትና በችጋር የተነሳ ራሳቸውን የሚያጠፉ ሰዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱ ይነገራል።

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide