የአፋር ሽማግሌዎች ከመሬታችን የሚለየን ሞት ብቻ ነው ይላሉ

መጋቢት ፳፰ (ሃይ ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-ሰሞኑን ኢሳት በአፋር አካባቢ የሚገኙ ሰፋፊ ቦታዎችን መንግስት ለሸንኮራ አገዳ እርሻ ልማት እንደሚፈልገው ማስታወቁን ተከትሎ የአካባቢው ህዝብ ተቃውሞ ማሰማቱን መዘገቡ ይታወሳል። የህዝቡ ተቃውሞ ያሰጋው መንግስት በአካባቢው የእርሻ ስራ እየሰሩ ያሉት ዶዘሮች በልዩ ሀይል እንዲጠበቁ በማድረግ የእርሻውን ስራ በጉልበት ለማካሄድ ወስኗል። የመንግስትን እርምጃ የተቃወሙ አፋሮች ተደብድበዋል ብዙዎችም ታስረዋል። ቤታችን አናፈርስም ብለው በመቃወማቸው ከታሰሩት መካከል 8 ሴቶች ከእነዚህም ውስጥ ሁለቱ አራሶች የሆኑ ይገኙበታል።

ጉዳዩን በማስመልከት መንግስት ይፋ መግለጫ ባይሰጥም የአፋር ሽማግሌዎች ግን የመንግስትን እርምጃ እስከ ሞት ድረስ እንደሚቃወሙት ለኢሳት ተናግረዋል። ሁለት የጎሳ ተጠሪዎች እንደተናገሩት መጥፎ እየተባለ የሚታወቀው ደርግ ያልፈጸመውን ድርጊት የመለስ መንግስት እየፈጸመው ይገኛል ። አንደኛው የጎሳ መሪ እንደተናገሩት ከአካባቢያቸው የሚያፈናቅላቸው ሞት ብቻ ነው

የጎሳ መሪው  መንግስት ከሽማግሌዎች ጋር ያደረገውን ስምምነት ማፍረሱንም ገልጠዋል መሪው ከእንግዲህ ወዲያ እስር ቤት እንደማይገቡ የሚመጣውን ለመከላከል የሚችሉትን ሁሉ ጥረት እንደሚያደርጉ አክለዋል ሌላ የጎሳ መሪም እንዲሁ መላው አለም ከጎናቸው እንዲቆም ጠይቀዋል

በኢትዮጵያ ውስጥ ህዝብ በየቦታው እየተፈናቀለ መገኘቱ በተደጋጋሚ መዘገቡ ይታወቃል።

________________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide