.የኢሳት አማርኛ ዜና

“የመለስ አምልኮ” የሚል ርእስ ያለው መጽሀፍ ነገ በገበያ ላይ ይውላል

ሚያዚያ ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የፍትህ ጋዜጣ መሥራችና ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በጋዜጣ ላይ ያወጣቸውን ፖለቲካዊ፣ ኤኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ ፊቸር- ጽሑፎች፣ አርቲክሎች እና ሀገራዊ ኮሜንተሪ- ሂሶች “የመለስ አምልኮ” በሚል ርዕስ የተመረጡ ስብስብ ሥራዎቹን በመድብል መልክ ያዘጋጀ ሲሆን መጽሐፉ በነገው ዕለት በኢትዮጵያ ዋና- ዋና ከተሞች በገበያ ላይ ይውላል፡፡ “የመለስ አምልኮ” መጽሐፍ 255 ገፆችን አካቶ በመጸሐፉ ጀርባ ላይ የቀድሞው ...

Read More »

ኢህአዴግ በ አማራ ተወላጆች ላይ እየፈጸመ ያለውን የማፈናቀል ተግባር ቀጥሎበታል

ሚያዚያ ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም   ኢሳት ዜና:-እንደ ጋዜጣው ዘገባ፤በደቡብ ክልል በጉራ ፈርዳ ወረዳ ይኖሩ የነበሩ አማሮች ፦”ወደ አገራችሁ ሂዱ” ተብለው መባረራቸው ህዝባዊ ተቃውሞ ባስነሳበት በሁኑ ጊዜ፤ በቤንሻንጉክ ጉሙዝ ክልል ይኖሩ የነበሩ የ አማራ ተወላጆችም ተመሣሳይ ዕጣ ገጥሟቸዋል። እንዲሁም  በሰሜን ጎንደር ዞን ሱዳን ድንበር አቅራቢያ በሚገኘው አርማጭሆ ወረዳ ውስጥ በኢብርሀጂራ  አካባቢ በእርሻ ሥራ  ተሰማርተው ይኖሩ የነበሩ የአማራ ተወላጅ ...

Read More »

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የ2012ትን የፔን ሽልማት ተቀበለ

ሚያዚያ ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም   ኢሳት ዜና:-በእስር ላይ የሚገኘው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የፔን አለማቀፍ ሽልማትን  የተቀበለው፧ በባለቤቱ በሰርካለም ፋሲል በኩል ነው። በአሜሪካ ሙዚየም ኦፍ ናቹራል ሂስተሪ ውስጥ በተደረገው የሽልማት ስነስርአት 500 የሚጠጉ የፔን ኢንተርናሽናል ደጋፊዎችና አባላት ተገኝተዋል። “እስክንድር ነጋ እጅግ የተደነቀና ደፋር ጋዜጠኛ ነው። እራሱን ለአደጋ እንደሚዳርገው እያወቀ; ብእሩን ከማንሳት ወደ ሁዋላ አላለም።” ሲሉ የፔን አሜሪካን ማእከል ...

Read More »

ለኢህአዴግ በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ የለገሰው ግለሰብ፧ በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ አጭበርብሯል የሚል ክስ ቀረበበት

ሚያዚያ ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም   ኢሳት ዜና:-ዮሐንስ ሲሳይ የተባለው የ40 አመት ጎልማሳ ኢህአዴግ አገሪቱን ከተቆጣጠረ በሁዋላ በአጭር ጊዜ ቢሊየነር ለመሆን የበቃ የዘመኑ ባለሀብት ነው። የሱ እና ሸበል የሚባሉ ኩባንያዎችን የመሰረተው ዮሐንስ ፣ ኢህአዴግ ለምርጫ በሚወዳደርበት ጊዜ በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ለፓርቲው ለግሷል። የትኛውም የአገር ውስጥ ባለሀብት ባላደረገው መልኩም፧ ከ30 ሚሊዮን ብር በላይ በማውጣት ለአባይ ግድብ ማሰሪያ ቦንድ ገዝቷል። ...

Read More »

ከ70 በላይ የፓኪስታን ዜጎች ጋምቤላን ለቀው ወጡ

ሚያዚያ ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም   ኢሳት ዜና:-ባለፈው ቅዳሜ በጋምቤላ በፓኪስታንና በኢትዮጵያውያን ላይ በተፈጸመው ጥቃት አራት ኢትዮጵያውያን እና አንድ ፓኪስታናዊ መገደላቸውን እንዲሁም አራት ፓኪስታናውያንና 5 ኢትዮጵያውያን መቁሰላቸውን ተከትሎ፣ በሼክ ሙሀመድ ሁሴን አል አሙዲን ሳውዲ ስታር ኩባንያ ውስጥ በከፍተኛ አመራርነት ይሰሩ የነበሩ ከ70 በላይ የፓኪስታን ዜጎች አካባቢውን ለቀው ዛሬ ወደ አዲስ አበባ ተጉዘዋል።  ፓኪስታናውያኑ አካባቢውን የለቀቁት የፓኪስታን ኢምባሲ ባለስልጣናት ...

Read More »

መንግስት ድምጻችን ይሰማ የሚሉ ወጣቶችን ማሰር ጀመረ

ሚያዚያ ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም   ኢሳት ዜና:-ከወራት በፊት በአወልያ የተነሳው የእምነት ነጻነት ይከበር ጥያቄ እየተስፋፋ ሄዶ መላው አገሪቱን እያዳረሰ ባለበት ሰአት መንግስት በአንዳንድ አካባቢዎች የሀይል እርምጃ መውሰድ ጀምሮአል። በምእራብ አርሲ ዞን አሳሳ ወረዳ 4 የእስልምና እምነት ተከታዮች በፌደራል ፖሊስ አባላት ከተገደሉ በሁዋላ ፣ ጥያቄውን አነሱ ሙስሊሞችን ማዋከብና ማሰሩ ቀጥሎአል። በአወልያ በተነሳው ተቃውሞ ወቅት የተመረጡ የሙስሊሙ አመራሮች፣ ከአቶ ...

Read More »

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ተቀጣ

ሚያዚያ ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም   ኢሳት ዜና:-በእነ አንዷለም አራጌ የክስ መዝገብ በፌዴራል አቃቤ- ሕግ አቤቱታ የቀረበበት የፍትህ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የሁለት ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት ትናንት ከሰዓት በኋላ በከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ሦስተኛ ወንጀል ችሎት ተፈረደበት፡፡   ፍርድ ቤቱ በቃሊቲ ማረሚያ ቤት በእስር ላይ የሚገኘውን 5ተኛ ተከሳሽ ክንፈሚካኤል ደበበ (አበበ ቀስቶ) ከማረሚያ ቤት ...

Read More »

የመለስ ዜናዊ መንግስት በንጹህ ዜጎች ላይ የሚፈጽመውን ግድያን ቀጥሎበታል ሲል ግንቦት7 አስታወቀ

  ሚያዚያ ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም   ኢሳት ዜና:-ግንቦት7 ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው የመለስ ዜናዊ መንግስት ለረጅም ጊዜ ይዞት የቆየውን የትግራይን የበላይነትን የማስጠበቅ አላማውን ከግብ ለማድረስ አማራዎችን ከደቡብ ከማፈናቀል ጀምሮ በጋምቤላ ፣ በአፋር እና በአርሲ አካባቢዎች በንጹህ ዜጎች ላይ ጭካኔ የተሞላበት እርምጃ ወስዷል።  ኢትዮጵያ  የአለም ታላላቅ ሀይማኖቶች የሆኑት እስልምናና ክርስትና ለዘመናት ተቻችለው የኖሩባት አገር ብትሆንም፣ በቅርቡ እየታዩ ያሉት ምልክቶች ...

Read More »

በጋምቤላው በደረሰው ጥቃት የሞቱት የሳውዲ ስታር ሰራተኞች ተሸኙ

ሚያዚያ ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም   ኢሳት ዜና:-ከጋምቤላ በምስል ተደግፎ ለኢሳት የተላከው ዘገባ እንዳመለከተው ባለፈው ቅዳሜ በአበቦ ወረዳ በሳውዲ ስታርና በሳውዲ ስታር ሰብ ኮንትራክተር በሆነው CRBC ኩባንያ ሰራተኞች ላይ ቅዳሜ እለት በተፈጸመው ጥቃት የሞቱት ዛሬ በአንድ የመከላከያ ሰራዊት ሄሊኮፕተር እና በአንድ አውሮፕላን ተጭነው ወደ አዲስ አበባ ተሸኝተዋል። ድርጊቱ የተፈጸመው ሰራተኞቹ ከአሌሮ ግድብ የሚወጣውን ውሀ ለሩዝ እርሻው ለማቅረብ የቧንቧ ...

Read More »

በሺዎች የሚቆጠሩ የሰሜን ጎንደር ነዋሪዎች ወደ ዋልድባ ተመሙ፣ ሁለት ነጮች ተገድለዋል ሌሎች ሰራተኞች አካባቢውን ለቀው ወጥተዋል

ሚያዚያ ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም   ኢሳት ዜና:-በሺዎች የሚቆጠሩ የሰሜን ጎንደር ነዋሪዎች ወደ ዋልድባ ተመሙ፣  ሁለት ነጮች ተገድለዋል ሌሎች ሰራተኞች አካባቢውን ለቀው ወጥተዋል የገዳሙ አባቶች ለሰሜን ጎንደር ነዋሪዎች ባቀረቡት ጥሪ መሰረት እስከ 200 ኪሎሜትር ርቀት የሚገኙ የሰሜን ጎንደር ነዋሪዎች ወደ አካባቢው መትመማቸውን ተከትሎ ሁለት ነጮች መሞታቸውን፣ ሌሎች ሰራተኞች ደግሞ እኛ ከህዝብ ጋር አንጣላም በማለት አካባቢውን ለቀው ወጥተዋል። የሟቾቹ ...

Read More »