.የኢሳት አማርኛ ዜና

የህዝብ ትምህርት ቤቶች ሊወረሱ ነው

ሚያዚያ ፴ (ሰላሳ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም   ኢሳት ዜና:-የኢህአዴግ መንግሥት በአዲስ አበባ እና በዋና ዋና የክልል ከተሞች የሚገኙ ነፃ የሕዝብ ትምህርት ቤቶችን ወደ መንግሥት ትምህርት ቤትነት ለማዘዋወር ወይም ለመውረስ እንቅስቃሴ ጀምሯል። በአዲስ አበባ የሚገኙ የሕዝብ ትምህርት ቤት መምህራኖችንና ሠራተኞችን  ረቡ እና ሀሙስ ማለትም ሚያዚያ 24 እና 25 ሙሉ ቀን ፣ የተማሪዎችን ወላጆችን ደግሞ ቅዳሜ እና እሁድ ለግማሽ ቀን ለይስሙላ አወያይቶ ...

Read More »

እጅግ ሰፊ ክልል የሚሸፍነው የሊማሊሞ ደን በቃጠሎ ወደመ

ሚያዚያ ፴ (ሰላሳ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም   ኢሳት ዜና:-በሰሜን ኢትዮጵያ ከውድመት ከተረፉት ጥቂት የደን ክልሎች  መካከል በሊማሊሞ አካባቢ የሚገኘው ጥቅጥቅ ደን በእሳት መጋየቱን የኢሳት ምንጮች አስታወቁ። እሳቱ የተነሳው ከአምስት ቀን በፊት ሲሆን እስካ ዛሬ ድረስ አለመጥፋቱን ከ10 ሺ ሄክታር በላይ የሚሸፍን ደንም ሙሉ ሙሉ ማውደሙን የአካባቢው ሰዎች ይናገራሉ።  እሳቱ አንድን አካባቢ ለማራቆት ሆን ተብሎ በመንግስት ሀይሎች የተለኮሰ  ነው  በማለት ቁጣቸውን ...

Read More »

የአሳታሚዎችና የብርሃንና ሠላም ማተሚያ ቤት ውዝግብ እንደቀጠለ ነው

ሚያዚያ ፴ (ሰላሳ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም   ኢሳት ዜና:-የብርሃንና ሠላም ማተሚያ ድርጅት ማኔጅመንትና አሳታሚዎች ውይይት ያለውጤት ተበትኗል፡፡ሁለቱ ወገኖች በድጋሚ ለመወያየት ለግንቦት 10 ቀን 2004 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮም ይዘዋል፡፡ በትላንትናው ዕለት አሳታሚዎችን የወከሉ አባላት ከብርሃንና ሠላም ማተሚያ ድርጅት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር በመገኛኘት “የሕትመት ስታንዳርድ ውል” በሚል እንዲፈርሙ የቀረበላቸው ረቂቅ ውል ሕገመንግሥቱን ጭምር የሚጥስ ቅድመ ምርመራ መሆኑን በመጥቀስ ውሉን ለመፈረም እንደሚቸገሩ ...

Read More »

በኢትዮጵያ አየር መንገድ ላይ ያልተጠበቀ አደጋ ሊደርስ እንደሚችል ሰራተኞች አስጠነቀቁ

ሚያዚያ ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም   ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባለፉት ሳምንታት ሸኚዎች ወደ ውስጥ ገብተው ዘመዶቻቸውን እንዳይሸኙ ክልከላ መጣሉን በተደጋጋሚ ስንዘግብ ቆይተናል። የአየር  መንገድ ሰራተኞች እንደሚሉት መንግስት እግዱን የጣለው የሽብር ጥቃት እንደሚፈጸም መረጃው ስለደረሰው ነው። ይሁን እንጅ አንዳንድ ወገኖች መንግስት ወደ ሳውዳ አረብያ  የሚጎርፉትን ወጣት ሴቶች ህዝቡ እንዳያያቸው የተጠቀመበት ስልት ነው ሲሉ በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ወጣት ሴቶች ...

Read More »

በደብረማርቆስ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ባስነሱት ተቃውሞ በርካቶች ታስረዋል

ሚያዚያ ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም   ኢሳት ዜና:-ተቃውሞው ምግብን ሰበብ አድርጎ እንደተፈጠረ ቢነገርም፣ የተማሪዎች ግን ከዚህ የዘለለ ነው ተብሎአል። ትናንት ከሰአት በሁዋላ የተነሳው ተቃውሞ ዛሬም ቀጥሎ የዋለ ሲሆን ተቃውሞው ከዞኑ ፖሊስ አቅም በላይ በመሆኑ የፌደራል ፖሊስ ጣልቃ ገብቷል። ተማሪዎች በፖሊሶች ላይ የሚያወርዱት ድንጋይ  መምህራኑ ከግቢያቸው እንዳይወጡ አድርጓቸው እንደነበር የደረሰን መረጃ ያመለክታል። የፌደራል ፖሊስ ግቢውን ለመቆጣጠር መሳሪያዎችን መተኮሱን አድማ ...

Read More »

አንድነት ፓርቲ በትናንትናው እለት በአርባ ምንጭ የተሳካ ስብሰባ አካሄደ

ሚያዚያ ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም   ኢሳት ዜና:-አንድነት ለዲሞክራሲ እና ለፍትህ ፓርቲ ባለፈው ቅዳሜ በወላይታ ሶዶ የተሳካ ስብሰባ ከካሄደ በሁዋላ በማግስቱ ደግሞ በአርባ ምንጭ  በርካታ ህዝብ በተገኘበት የተሳካ ስብሰባ አካሂዷል። የከተማው መስተዳደር ለፓርቲው ስብሰባ ማካሄጃ ሲቀላ በሚባለው አካባቢ በሚገኝ የፖሊስ አዳራሽ ቢፈቅድም፣ አዳራሹ ለተሰብሳቢው በማይመች መልኩ ማዘጋጀቱን ለማወቅ ተችሎአል። በስብሰባው ላይ በርካታ ህዝብ እንደሚገኝ እየታወቀ ሲመጣ፣ የወረዳው ባለስልጣናት ...

Read More »

ሁለት የመካከለኛው ምሥራቅ ዜጎች በ24 ሰዓት ውስጥ ከአገር እንዲወጡ መወሰኑ ውሸት ነው ተባለ

ሚያዚያ ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም   ኢሳት ዜና:-በታላቁ የአንዋር መስጊድ  ለፀሎት በተሰበሰቡ ምዕመናን መካከል በመግባት ህገ-ወጥ  ቅስቀሳ ሲያደርጉ እና  በህገ -ወጥ መንገድ ወረቀት ሲበትኑ የተገኙ ሁለት የመካከለኛው ምሥራቅ ዜጎች በ 24  ሰ ዓት ውስጥ ከ አገር እንዲወጡ ተወሰነ በማለት የ ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ትናንት ያስተላለፈውን ዘገባ የ አዲስ አበባ ነዋሪዎች ፦”የተለመደ ነጭ ውሸት” ሲሉ አጣጣሉት። በጉዳዩ ዙሪያ የ ኢሳት ...

Read More »

ሰማያዊ ፓርቲ በምርጫ ቦርድ እየተጉላላ ነው

ሚያዚያ ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም   ኢሳት ዜና:-በወጣቶች እና በምሁራን  የተቋቋመው እና በአጭር ጊዜ ውስጥ እጅግ በርካታ አባላትን ምፍራቱ የሚነገርለት ሰማያዊ ፓርቲ ፤ከምርጫ ቦርድ ህጋዊ ፈቃድ ማግኘት እንዳልቻለ ገለጸ። ሰማያዊ ፓርቲ  የተቋቋመው የዛሬ አምስት ወር አካባቢ ቢሆንም፤ አባላት ከማፍራት ጀምሮ በ አጭር ጊዜ ውስጥ እያደረጋቸው ያሉት እንቅስቃሴዎች  በመንግስት ዘንድ  ስጋት ማሳደር ሳይጀምሩ እንዳልቀሩ አንድ የፓርቲው ከፍተኛ አመራር ጠቁመዋል። ...

Read More »

በወላይታ ሶዶ አንድነት ፓርቲ በወከባ ውስጥ ሆኖ ስብሰባውን አካሄደ

ሚያዚያ ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም   ኢሳት ዜና:-አንድነት ፓርቲ ዛሬ ሚያዚያ 26፣ 2004 ዓም በወላይታ ሶዶ ከተማ ህዝባዊ ስብሰባ መጥራቱን ተከትሎ  የገዢው ፓርቲ ካድሬዎች በሰብሳቢዎቹና በተሰብሳቢዎቹ ላይ ከፍተኛ ወከባ አድርሰዋል። በስብሰባው ላይ ለመገኘት ከአዲስ አበባ ወደ ወላይታ ያመሩት ኢ/ር ዘለቀ ረዲ፣ ዶ/ር ሀይሉ አርአያና አቶ ዳንኤል ሺበሺ ወደ ከተማዋ ሲገቡ መኪናቸው ጉዳት እንደደረሰባት፣ እንዲሁም ደጋፊዎቻቸውና የከተማዋ ነዋሪዎች ወደ ...

Read More »

በደሴ ከተማ ከጁምአ ጸሎት በሁዋላ የተቃውሞ ሰልፍ ተካሄደ

ሚያዚያ ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም   ኢሳት ዜና:-በደሴ ከተማ  በፉርቃን መስጊድ ለአምስተኛ ጊዜ የተካሄደው ይህ የተቃውሞ ሰልፍ  በድምቀቱም ሆነ  በህዝብ ብዛት  ባለፉት አራት ሳምንታት ከተካሄዱት ሰልፎች የበለጠ  ሆኖ ታይቷል። የሰልፉ አስተባባሪዎች መንግስት  በብዙሀን ሙስሊሞች ላይ ያነጣጠረ የማስጠንቀቂያ መልዕክት ባስተላለፈበት ጊዜ  የተካሄደው ሰልፍ  ይበልጥ ጠንካራ እና ደማቅ የሆነው፤ ህዝበ-ሙስሊሙ  መንግስት  የቀረበለትን የመብት ጥያቄ  በሀይል ለመፍታት በያዘው መንገድ   ላይ  ይበልጥ ...

Read More »