.የኢሳት አማርኛ ዜና

የሱዳን የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የተቃውሞ ሰልፍ እያደረጉ ነው።

ሰኔ አስራ ሦስት ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ተማሪዎቹ ተቃውሞውን ያነሱት መንግስት በአገሪቱ የሚታየውን የዋጋ ንረት ለመቆጣጠር የሚወስደውን እርምጃ ተከትሎ ነው። የአገሪቱ ተቃዋሚዎች ህዝቡ በፕሬዚዳንት አልበሽር መንግስት ላይ እንዲነሳ ጥሪ እያቀረቡ ነው። የበሽር መንግስት በተማሪዎች ላይ የሚወስደውን እርምጃ የአሜሪካ መንግስት አውግዟል። አመጹ በካርቱም ብቻ ሳይሆን ከካርቱም ውጭ ባሉ ዋና ዋና ከተሞችም ተሸጋግሯል። ተቃውሞውን ለመዘገብ ወደ ዩኒቨርስቲዎች የተጓዙ የውጭ አገር ጋዜጠኞችም በጸጥታ ...

Read More »

ከማዳበሪያ እዳ ጋር በተያያዘ በአንድ ቀበሌ ከ200 በላይ አርሶአደሮች ታሰሩ

ኢሳት ዜና:-በአማራ ክልል በአለፋ ጣቁሳ ወረዳ በማዳበሪያ እዳ የተያዙ ከ200 በላይ አርሶአደሮች መታሰራቸውን ዘጋቢያችን ገልጧል። ገዢው ፓርቲ ለገቢ ማሰባሰቢያ በሚል በግዴታና በውዴታ ማዳበሪያ በእዳ ሲያከፋፍል ከቆየ በሁዋላ ካለፉት 2 ወራት ጀምሮ አርሶአደሮቹ በአስቸኳይ እንዲከፍሉ ትእዛዝ ወርዶባቸዋል። እዳቸውን ለመክፈል አቅሙ ያጠራቸው አርሶአደሮች በገፍ እየተያዙ በእስር ላይ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሎአል። አንድ ስሙ እንዳይገለጥ የጠየቀ ሰው ለኢሳት እንደገለጠው በእስር ላይ ከሚገኙት አርሶአደሮች መካከል ...

Read More »

ሚስተር ቤን ራውለስን ዜጎች ያለፍላጎታቸው እንዲፈናቀሉ መደረጉ አለማቀፍ ህግንና ህገመንግስቱን መጣስ አሉ

ሰኔ ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ዜጎች ያለፍላጎታቸው እንዲፈናቀሉ መደረጉ አለማቀፍ ህግንና ህገመንግስቱን መጣስ ነው ሲሉ ሂውማን ራይትስ ወች የአፍሪካ ከፍተኛ ተመራማሪ ተናገሩ ሚስተር ቤን ራውለስን ለኢሳት እንደገለጡት በታችኛው የኦሞ ሸለቆ አካባቢ ለስኳር ልማት በሚል ዜጎች እንዲፈናቀሉ የሚደረጉት ያለፍላጎታቸው ነው። አለማቀፍ ህግም ሆነ የኢትዮጵያ ህገመንግስት አርብቶአደሮች ያለፍለጎታቸው እንዲፈናቀሉ አይፈቅድም በማለት የተናገሩት ራውለንስ ሂውማን ራይትስ ወች የኢትዮጵያ መንግስትም ለህጎቹ ...

Read More »

እስረኞች ግፍና በደል እየተፈጸመባቸው እንደሆነ አንድነት ፓርቲ አስታወቀ

ሰኔ ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ቅዱስ ሃብት በላቸው ከአውስትራሊያ እንደዘገበው  “በቃሊቲ እሥር ቤት ውስጥ የሚገኙ የህሊና እስረኞች ደህንነታቸውን አደጋ ላይ የሚጥሉ በርካታ በደሎች እየተፈጸሙባቸው ነው፡፡” ሲል የአንድነት ለፍትህና ለዴሞክራሲ ፓርቲ ባለፈው እሁድ አዲስ አበባ ላይ ያወጣውን መግለጫ በመጥቀስ ዘግቧል   በእሥር ቤቱ ፖሊሶችና ኃላፊዎች ሳይቀር ሰብዓዊ ክብርን የሚነኩ ዘለፋዎችና አሰቃቂ ድብደባዎች እንደሚፈፀምባቸው የገለፀው  አንድነት በመግለጫው ላይ በዝርዝር ...

Read More »

ኢትዮጵያ አደጋ ውስጥ ከገቡ አገሮች ተርታ ተመደበች

ሰኔ ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ፎሬን ፖሊሲ መጋዚን ባወጣው የፌልድ ሰቴትስ ኢንዴክስ ኢትዮጵያን ከአለም አገሮች በ17ኛ ደረጃ በማስቀመጥ፣ለአደጋ የተጋለጠች አገር ሲል ፈርጇታል።  ለኢትዮጵያ ህልውና አስጊ ሆነው ከቀረቡ ችግሮች መካከል የህዝብ ቁጥር መጨመር፣ የስደተኞች መብዛት፣ የህዝብ ብሶቶች መጨመር፣  ዜጎች አገራቸውን ጥለው መሰደድ፣ የፖለቲካ መሪዎች ልዩነት እና የጸጥታ ሀይሎች ጣልቃ ገብነት የሚሉት ይገኙበታል። ከሁለት አመት በፊት ኢትዮጵያ እንደ ዘንድሮው ...

Read More »

በግብጽ ሙስሊም ወንድማማቾች ፓርቲ የተቃውሞ ሰልፍ ጠራ

ሰኔ ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ፓርቲው ሰልፍ ለመጥራት የተገደደው የአገሪቱ መከላከያ ሰራዊት ዋና ዋና የሚባሉትን ስልጣኖች በእጁ በማስገባቱ ነው የመከላከያ ጀኔራሎች በሳምንቱ መጨረሻ የእስላማዊ ወንድማማቾች የተቆጣጠሩትን ፓርላማ በማፍረስ ህግ የማውጣቱን ስልጣን ለራሳቸው ሰጥተዋል። በሳምንቱ መጨረሻ በተደረገው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ የሙስሊም ወንድማማቾች ፓርቲ ምርጫውን ማሸነፉን አስታውቋል። የአገሪቱ የምርጫ አስፈጻሚዎች የምርጫውን ውጤት የፊታችን ሀሙስ ይፋ እንደሚያደርጉ ገልጠዋል። ቢቢሲ እንደዘገበው የመከላከያ ...

Read More »

ኢትዮጵያ፡ ለስኳር ልማት ሲባል አርብቶ አደሮች መሬታቸውን በግዳጅ እንዲለቁ እየተደረገ ነው

ሰኔ ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በቂ ምክክር ሳያደርግ ወይም ተገቢውን የካሣ ክፍያ ሳይፈጽም በመንግስት የሚካሄድ የስኳር ልማትን ለማስፋፋት የኢትዮጵያ መንግስት በኢትዮጵያ የታችኛው የኦሞ ሸለቆ ነዋሪ የሆኑ አርብቶ አደሮችን በግዳጅ እያፈናቀለ ነው ሲል ሂዩማን ራይትስ ዎች ዛሬ ባወጣው ሪፖርት ገለጸ።  ሪፖርቱ ከዚህ በፊት ያልታተሙ እና የመስኖ መስመሮችን፣ የስኳር ማምረቻ ፋብሪካዎችን እንዲሁም ሌሎች ለንግድ የሚውሉ ሰብሎችን ለማማረት የሚውል 100,000 ...

Read More »

አይ. ኤም.ኤፍ የኢትዮጵያን መንግስት የኢኮኖሚ ዕድገት ትንበያ እንደማይቀበል አስታወቀ

ሰኔ ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ መንግስት በዘንድሮው ዓመት ከ 11 በመቶ በላይ የኢኮኖሚ ዕድገት እንዳስሚያስመዘግብ በተደጋጋሚ ሲገልጽ መቆየቱ ይታወሳል። የዓለማቀፉ የገንዘብ ተቋም የአፍሪካ ዲፓርትመንት ምክትል ዳይሬክተር በሆኑት በሚስተር ማይክል አቲንጅ የተመራውና ከግንቦት 26 እስከ ሰኔ 7 ቀን 2004 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ቆይታ ያደረገው የ አይ. ኤም ኤፍ  ልዑክ ግን ፣ ይህን የኢትዮጵያ መንግሥት  የኢኮኖሚ ዕድገት ትንበያ እንደማይቀበለው ...

Read More »

በመከላከያ ሰራዊት ፊት ኢሳዎች በአፋሮች ላይየሚፈጽሙት ግፍ ልኩን አልፏል ሲል የአፋር ፎረም አስታወቀ

ሰኔ ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ፎረሙ ለኢሳት በላከው መግለጫ ካለፈው ወር ጀምሮ በሶማሊ ክልል መንግስት የሚደገፉ ታጣቂ ሚሊሻዎች በአፋር ተወላጆች ላይ ግድያ እየፈጸሙ ነው። የመከላከያ ሰራዊት አባላት ቆመው እየተመለከቱ በርካታ አፍር ወጣቶች መገደላቸውን ፎረሙ ጠቅሷል። ፎረሙ የጅቡቲ መንግስት ለኢሳ ታጣቂዎች ድጋፍ እየሰጠ ነው በሚልም ክስ አቅርቧል። በሶማሊያ ክልል የሚደገፉት ኢሳዎች የመሬትና የኢኮኖሚ ጥያቄ አለን እንደሚሉ የጠቀሰው ፎረሙ፣ ...

Read More »