በግብጽ ሙስሊም ወንድማማቾች ፓርቲ የተቃውሞ ሰልፍ ጠራ

ሰኔ ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-ፓርቲው ሰልፍ ለመጥራት የተገደደው የአገሪቱ መከላከያ ሰራዊት ዋና ዋና የሚባሉትን ስልጣኖች በእጁ በማስገባቱ ነው

የመከላከያ ጀኔራሎች በሳምንቱ መጨረሻ የእስላማዊ ወንድማማቾች የተቆጣጠሩትን ፓርላማ በማፍረስ ህግ የማውጣቱን ስልጣን ለራሳቸው ሰጥተዋል።

በሳምንቱ መጨረሻ በተደረገው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ የሙስሊም ወንድማማቾች ፓርቲ ምርጫውን ማሸነፉን አስታውቋል። የአገሪቱ የምርጫ አስፈጻሚዎች የምርጫውን ውጤት የፊታችን ሀሙስ ይፋ እንደሚያደርጉ ገልጠዋል።

ቢቢሲ እንደዘገበው የመከላከያ ሰራዊት ጄኔራሎች የሙስሊም ወንድማማቾች ምርጫውን ያሸንፋል በሚል እምነት ዋና ዋና የሚሉዋቸውን ስልጣኖች ወደ ራሳቸው በመውሰድ የፕሬዚዳንቱን ስልጣን ለመገደብ ሞክረዋል።

የሙስሊም ወንድማማቾች በሚቀጥለው ማክሰኞ አዲሱን አዋጅ በመቃመው 1 ሚሊዮን ህዝብ የሚገኝበት የተቃውሞ ሰልፍ ለማዘጋጀት አቅደዋል። የመከላከያ ሰራዊት አመራሮች ከ10 ቀናት በሁዋላ ስልጣናቸውን ለአዲሱ ፕሬዚዳንት እንደሚያስረክቡ እየገለጡ ነው።

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide