ሰኔ ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአዋሳ ከተማን እጣ ፋንታ እና የሲዳማ ዞንን የክልል ጥያቄ ተከትሎ በሲዳማ ዞን ተወላጅ የምክር ቤት አባላት በአንድ ጎን እና የፌደራሉና የሌሎች የምክር ቤት አባላት በሌላ ጎን ሆነው የጀመሩት ውዝግብ እየተካረረ መምጣቱን ተከትሎ በአዋሳ የሚታየው ከፍተኛ ውጥረት አለመቀነሱን ዘጋቢያችን ገልጧል። በዛሬው እለት ወጣቶች ሰላማዊ ሰልፍ ያደርጋሉ በሚል ስጋት የፌደራል ልዩ ሀይል አድማ በታኝ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
ወደ ዓረብ አገራት የሚሄዱ ኢትዮጵያዊያን ቁጥር ከሶስት እጥፍ በላይ አሻቀበ
ሰኔ ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በመጠናቀቅ ላይ በሚገኘው በ2004 በጀት አመት 10 ወራት ውስጥ ብቻ 140 ሺ ዜጎች ሥራ ፍለጋ ወደ ተለያዩ የአረብ ሀገራት መጓዛቸውን ይህ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ329 በመቶ ማሻቀቡን አንድ ጥናት አመለከተ፡፡ በትላንትናው ዕለት በጠ/ሚኒስትሩ ቢሮ ይፋ የሆነው ይህው ጥናት እንደሚያመለክተው በህገወጥ መንገድ ከአገር የሚወጡት ዜጎች ቁጥር በአስደንጋጭ መልኩ ማሻቀቡን የጠቆመ ...
Read More »በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሠራተኛው ላይ የ 7 አመት ከ 8 ወራት እስራት ተበየነ
ሰኔ ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ፍርድ ቤቱ አብዱራሂም ሺሁ ሀሰን በተሰኘው የመንግስታቱ ድርጅት የሴኩሪቲ ኦፊሰር ላይ ይህን ውሳኔ ያሳለፈው፦ “ለኦጋዴ ብሄራዊ ነፃነት ግንባር መረጃዎችን አስተላልፏል” በማለት በ ፌዴራል አቃቤ ህግ በተመሰረተበት ክስ ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ እንደሆነ ገልጿል። አብዱራሂም የሽብርተኝነት ክስ ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ፤ ዓለማቀፍ የሰብዓዊ መብት ተቋማት፦ የኢትዮጵያ መንግስት ተዓማኒነት የሌለውን ክሱን ውድቅ በማድረግ የመንግስታቱ ድርጅት የደህንነት ...
Read More »አቶ ሽመልስ ”መንግስት የስካይፒ ጥሪን እንዲሁም የጎግል እና የ “ያሁ” አገልግሎቶችን በህግ አላገደም” አሉ
ሰኔ ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ሚኒስትር ዴኤታው ይህን ያሉት ትናንት በጽህፈት ቤታቸው በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ነው። አቶ ሽመልስ በትናንቱ መግለጫቸው ትኩረት ያደረጉባቸው ሁለት ነጥቦች፦ በኦሞ ወንዝ አካባቢ እየተሰራ ያለውን የስኳር ፕሮጀክት አስመልክቶ ከሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች እየተሰማ ያለውን ተቃውሞ እና መንግስት በ”ስካይፒ “፣ በ”ጎግል ቶክ” እና በ”ያሁ መሴንጄር” አማካይነት የሚደረጉ ጥሪዎችን ...
Read More »የጸጥታ ሀይሎች በሱዳን መንግስት ተቃዋሚዎች ላይ እርምጃ እየወሰዱ ነው
ሰኔ ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የጸጥታ ሀይሎቹ እርምጃውን የወሰዱት የአልበሽር መንግስት የመንግስትን ወጪን ለመቀነስ የወሰደውን እርምጃ ለመቃወም በወጡ ሰልፈኞች ላይ ነው። ትናንት ከጁመአ ጸሎት በሁዋላ ተቃዋሚዎቹ ህዝቡ መንግስት እንዲለወጥ ይፈልጋል የሚል መፈክሮችን አሰምተዋል። ተመሳሳይ ተቃውሞ በባህሪ አካባቢ ተነስቶ ፖሊሶች ተቆጣጥረውታል። የሱዳን የዩኒቨርሰቲ ተማሪዎች ያነሱት ተቃውሞ በአገሪቱ የሚታየውን የኢኮኖሚ ችግር ይበልጥ ያባብሰዋል ተብሎ ተሰግቷል። ደቡብ ሱዳን ራሱን ከሰሜኑ ...
Read More »በሲዳማ ዞን እየተነሳ ባለው ተቃውሞ የመንግስት እጅ አለበት ተባለ
ሰኔ ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአዋሳ ነዋሪዎች ለኢሳት እንደገለጡት ለዘመናት ተቻችለው የኖሩ ህዝቦች እንዲጋጩ ለማድረግ የመንግስት ባለስልጣናት ሆን ብለው እየሰሩ ነው። ህዝቡ በኑሮ ውድነቱ፣ በመብት አፈናው እና በተለያዩ አስተዳደራዊ ችግሮች እየተማረረ፣ ከዛሬ ነገ ለውጥ ይመጣል እያለ በሚናፍቅበት በዚህ አስቸጋሪና አስፈሪ ወቅት፣ መንግስት የዋሳ ከተማን አስተዳደር እንደገና የህዝብ አጀንዳ አድርጎ በማቅረብ ግጭት እንዲነሳ መጣሩ ነዋሪዎችን አስቆጥቷል። የዞኑ ባለስልጣናት ...
Read More »ሸብርተኝነትን ይዋጋል የተባለ መታወቂያ በብሔራዊ ደረጃ ሊዘጋጅ ነው
ሰኔ ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ሸብርና ወንጀልን ለመከላከል ይረዳል የተባለ በአገር አቀፍ ደረጃ ብሔራዊ የመታወቂያ ካርድ ለመስጠት የሚያስችል ረቂቅ አዋጅ ትናንት ለፓርላማ ቀረበ፡፡ በፍትህ ሚኒስቴር ተዘጋጅቶ በሚኒስትሮች ም/ቤት ጸድቆ ለፓርላማ የቀረበው ረቂቅ ሕግ በአገር አቀፍ ደረጃ አንድ ወጥ የሆነ፣የራሱ ሚሲጢራዊ ኮድ ያለው መታወቂያ በብሔራዊ ደረጃ ማዘጋጀት ያስፈለገው ሸብርና ወንጀልን ለመከላከልና ለምርመራ ተግባራት፣ለብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ለግብር አከፋፈል፣ለፋይናንስ ...
Read More »የፌደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የጋዜጠኛና መምህርት ርእዮት አለሙን አቤቱታ አደመጠ
ሰኔ ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ዛሬ ረፋዱ ላይ የመሀል ዳኛው አቶ ዳኘ መላኩ፣ የቀኝ ዳኛው በላቸው አንሺሾና ስማቸው ያልተገለጠው ግራ ዳኛው በመሩት ችሎት ላይ የርእዮት ጠበቃ የሆኑት አቶ ሞላ ዘገየ እና አቃቢ ህጉ አቶ ብርሀኑ ወንድማገኝ ተከራክረዋል። የርእዮት አባት የሆኑት አቶ አለሙ ገበቦ በረዳት ጠበቃነት ተሳትፈዋል። ጠበቃ ሞላ ዘገየ ደንበኛቸው ርእዮት አለሙ በህገመንግስቱ አንቀጽ 29 በተሰጣት መብት ...
Read More »ለእስር ቤቶች ግንባታ የሚመደበው በጀት በየዓመቱ ከፍተኛ ጭማሪ እያሳየ ነው
ሰኔ ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ መንግስት ለእስር ቤቶች ግንባታ በየዓመቱ የሚመድበው ባጀት በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ መምጣቱን መረጃዎች ጠቆሙ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር ከ2003 እስከ 2005 ዓ.ም ባሉት ጊዜያት መንግስት ለፌዴራል እስር ቤቶች ግንባታ ብቻ በድምሩ 415 ሚሊየን 153 ሺ100 ብር መድቧል፡፡ በ2003 በጀት ዓመት 13 ሚሊየን ለግንባታ( ካፒታል ወጪ) የመደበ ሲሆን ይህ ቁጥር በ2004 ዓ.ም ወደ 193 ...
Read More »የፖለቲካ ግብ ያለውን ማስታወቂያ የሚከለክለው ረቂቅ አዋጅ ለፓርላማ ቀረበ
ሰኔ ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የፖለቲካ ፓርቲዎች ( ድርጅቶች ) የፖለቲካ ግብ ያለው ማስታወቂያ እንዳያሰራጩ የሚከለክለው ረቂቅ አዋጅ በብሮድካስት ባለሥልጣን አርቃቂነት በሚኒስትሮች ም/ቤት ጸድቆ ትናንት ለፓርላማ ቀረበ፡፡ ረቂቅ አዋጁ የፖለቲካ ድርጅቶች የሚያደርጉትን የአድራሻ ለውጥ፣የስብሰባ ጥሪ እና መሰል ማስታወቂያ እንደተጠበቀ ሆኖ የፖለቲካ ግብ ያለው ማስታወቂያን በመገናኛ ብዙሃን እንዳይተላለፍ ይከለክላል፡፡ አዲሱ ህግ የፖለቲካ ድርጅቶችና የሃይማኖት ተቋማት የመገናኛ ብዙሃንን ማስታወቂያዎች ...
Read More »