6 August 2012 [ESAT] የኢትዮጵያ ህዝቦች በአገር ውስጥና በውጭ ሃገር በመደራጀት እየታገሉ መሆናቸውን ተገንዝቤያለው ያለው ነጻ የኢትዮጵያ ሰራዊት ንቅናቄ ከዚህ የህዝብ አብራክ የወጣ የመከላከያ ሰራዊትም በህቡዕ ተደራጅቶ የትግል አካል ለመሆን መዘጋጀቱን በመግለጫው አስታውቋል:: የንቅናቄው ቃል አቀባይ ሻምበል ኤፍሬም ተካ ከኢሳት ሬድዮ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንደገለጹት የኢትዮጵያ መከላከያ የፖሊስና የደህንነት ኃይል በህቡዕ ሲደራጅ መቆየቱን አመልክተው ለትግል ለተዘጋጀው የኢትዮጵያ ህዝብ መከታ ሆኖ ከጎኑ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
የአቶ መለስ ዜናዊ መጨረሻ አሁንም የኢትዮጵያውያን ያልተመለሰ ጥያቄ ሆኗል
ሐምሌ ፳፰ (ሀያ ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-እጅግ ውስብስብ የሆኑ ሚስጢሮችን በማውጣት የሚታወቁት አለማቀፍ የመገናኛ ብዙሀን የአቶ መለስን የደህንነት ሁኔታ ለማወቅ አለመቻላቸው ብዙዎችን አነጋግሯል። አንዳንድ ወገኖች የምእራባዊያን የመገናኛ ብዙሀን ከአሜሪካ ወይም ከአውሮፓ መንግስታት የ”ይለፍ መብራት” ካልበራላቸው፣ ዜናዎችን ለማውጣት ፈቃደኛ አይሆኑም በማለት ሲናገሩ ሌሎች ደግሞ ኢትዮጵያ የምእራባዊያን የመገናኛ ብዙሀን የምትስብ አገር ባለመሆኑዋ የመገናኛ ብዙሀኑ ትኩረት እንደነፈጉዋት ይገልጣሉ። በመሀሉ በርካታ ኢትዮጵያውያን ...
Read More »በደቡብ ክልል በፕሬዚዳንቱና በአፈ ጉባኤዋ መካከል በተፈጠረው ውዝግብ ምክር ቤቱ ለሁለት ተከፈለ
ሐምሌ ፳፰ (ሀያ ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ባለፈው ማክሰኞ የክልሉ ፕሬዚዳንት የሆኑት አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ከሲዳማ ዞን የተለያዩ ወረዳዎች የተውጣጡ የአገር ሽማግሌዎችን ሰብስበው “የሲዳማ ጥያቄ ፣ ወቅታዊ አለመሆኑንና አብዛኛውን ህዝብ የማይወክል መሆኑን” ተናገሩ በማለት ለማግባባት ሞክረው እንደከሸፈባቸው መዘገባችን ይታወሳል። ከኢትዮጵያ ቴሌቪዥንና ከሌሎች የመገናኛ ብዙሀን የተወከሉ ጋዜጠኞች በስፍራው ተገኝተው “የሲዳማ ጥያቄ የጸረ ሰላም ሀይሎች ጥያቄ ነው” በማለት ይዘግባሉ ተብሎ ሲጠበቅ፣ ...
Read More »ሚኒስትሩ አቶ ጁነዲን ሳዶ ይቅርታ አልጠይቅም አሉ
ሐምሌ ፳፰ (ሀያ ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ባለቤታቸው የታሰሩባቸው የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትሩ አቶ ጁነዲን ሳዶ፦”ይቅርታ ጠይቁ” በመባላቸውን በመጥቀስ፦” የሠራሁት ስህተት ስለሌለ የምጠይቀው ይቅርታ የለም” አሉ። ባለቤቴ ከህፃናት ልጆች ተነጥላ ትክክለኛ ባልሆነ ማስረጃ ታስራብኛለች ሲሉም አቤት አሉ። ሚኒስትር ጁነዲን ሳዶ የባለቤታቸውን መታሰር አስመልክቶ በኢትዮ ቻነል እና በሰንደቅ ጋዜጦች ለወጡት ዜናዎች መልስ በሰጡበትና በዛሬው የ ኢትዮ ቻነል ጋዜጣ ላይ በታተመው ጽሁፋቸው ...
Read More »ኢትዮጵያዊቷ የቤት ሰራተኛ በኩዌት ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ እራሷን አጠፋች
ሐምሌ ፳፰ (ሀያ ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አረብ ታይምስ ትናንት ባወጣው ዘገባ እንደገለፀው ከሆነ፣ ኢትዮጵያዊቷ ትሰራበት የነበረው ቤት ውስጥ ራሷን የመግደል ሙከራ ስታደርግ ተይዛ ወደ ሆስፒታል ተወስዳ ስነልቦና ሕክምና እንድትወስድ ተደርጋ ነበር። ሆኖም ከሆስፒታሉ ስትወጣ “ጃሃራ” በሚባል ስፍራ ወደሚገኘው “አል-ነኢም” ፖሊስ ጣቢያ ተወስዳ በመታሰር በምርመራ ላይ ሳለች፤ የእስር ቤቱ መታጠቢያ ቤት ውስጥ አድርጋው በነበረው ሂጃብ የራሷን ሕይወት አጥፍታ ተረኛው ...
Read More »በለንደን እየተካሄ ባለው 17ኛው ኦሎምፒክ ውድድር አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ በ 10፣000 ሜትር በማሸነፍ የወርቅ ሜዳሊያ አጠለቀች
ሐምሌ ፳፰ (ሀያ ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ውድድሩ ከመካሄዱ በፊት ኬንያውያን ወርቁ የእነሱ እንደሆነ ደምድመው ለተለያዩ ሚዲያዎች ብዙ ብለዋል። በተለይ በዳጉ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በ 5 000 እና በ 10 000 የድርብ ወርቅ ሜዳል ባለቤት የሆነችውና በትናንት ምሽቱ የ 10000 ሜትር ውድድር ሦስተኛ የወጣችው ቪቪያን ቸሩዮት ወድድሩ ከመካሄዱ በፊት፤ ወርቁ የእሷ እንደሆነ በእርግጠኝነት በማወጅ፦”ኬንያውያን ከአሁን ጀምረው መጨፈር ይችላሉ” ነበር ...
Read More »ሙስሊም ኢትዮጵያውያን በአንዋር መስጊድ ሰላማዊ ተቃውሞዎችን ቀጥለው ዋሉ
ሐምሌ ፳፯ (ሀያ ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአዲስ አበባ እና በአዲስ አበባ ዙሪያ ባሉ ከተሞች የሚኖሩ ሙስሊም ማህበረሰብ ዛሬ ከቀኑ 5 ሰአት ተኩል ጀምሮ በአንዋር መስጊድ በመሰባሰብ የአርብ ስገደት ካደረጉ በሁዋላ ፣ ሰላማዊ ተቃውሞዎችን ቀጥለው ውለዋል። ቁጥራቸው ከ5 መቶ ሺ በላይ ሙስሊሞች ፣ የሚወርደው ዶፍ ዝናብ ሳይበግራቸው ፣ ከጸሎት በሁዋላ ለደቂቃዎች ነጭ ማህረብ ጨርቅ ፣ ነጭ ሶፍት ወረቀት በማውለብለብ፣ ...
Read More »የሱዳን የደህነት አባላት የቤንሻንጉል ነጻ አውጭ ድርጅትን መሪ ልጅ አሰሩ
ሐምሌ ፳፯ (ሀያ ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-መንግስት ሰሞኑን ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ነጻ አውጭ ድርጅት ሰራዊት አባላት ጋር ድርድር በማድረግ ስምምነት ላይ መድረሱን አስታውቆ ነበር። ሱዳን አገር የሚገኙ አንዳንድ የድርጅቱ አባላት የድርጅቱ ሊቀመንበር ባልተገኙበት ሁኔታ በኢትዮጵያ ኢምባሲ በኩል ከመንግስት ጋር ድርድር አድርገዋል። መንግስት የድርጅቱ ሊቀመንበር የሆኑት አምባሳደር ዩሱፍ ሀሚድ ወደ አገር ከገቡ ከፍተኛ ገንዘብ እንደሚሰጣቸው ቃል መግባቱን ፣ ይሁን እንጅ ...
Read More »የጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ እስር ወደ አምስት ዓመት ዝቅ አለ
ሐምሌ ፳፯ (ሀያ ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በጋዜጠኛ ርእዮት አለሙ ላይ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ሶስተኛ ወንጀል ችሎት የሰጠውን የ14 አመት ጽኑ እስራት እና የ33 ሺ ብር የቅጣት ውሳኔ፣ እስካሁን የታሰረችው አንድ አመት ከአንድ ወር ታሳቢ ተደርጎ ወደ 5 አመት ዝቅ እንዲል ወስኗል። የጋዜጠኛ ርእዮት አለሙ የኢህአዴግ ቀይ እስክርቢቶ የተሰኘ መጽሀፍ ነገ ሀምሌ 28 ...
Read More »የኢትዮ ቻነል እና የሳምሶን ማስታወቂያ ድርጅት ባለቤት የሆነው ሳምሶን ማሞ ከነ ባለቤቱ ታሰረ
ሐምሌ ፳፯ (ሀያ ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮ-ቻናል ጋዜጣ ማኔጂንግ ዳይሬክተርና የሳምሶን አድቨርታይዚንግ ዋና ስራ አስኪያጅ ጋዜጠኛ ሳምሶን ማሞ እና የኢትዮ-ቻናል ጋዜጣ አሳታሚ የዜድ ፕሬስ ዋና ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ዘውድነሽ ታደሰ ባለፈው ሐሙስ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለዋል ወደ 6 የሚሆኑ መለዮ የለበሱና ሲቪል የላንቻ ፖሊስ ጣቢያ አባላት ጋዜጠኛ ሳምሶን ማሞን አስገድደው የያዙት ሐሙስ ማለዳ ወደ ቢሮው በሚገባበት ወቅት ነበር፡፡ ...
Read More »