.የኢሳት አማርኛ ዜና

የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት በአርማጭሆ ወታደራዊ ጥቃት መፈፀሙን አስታወቀ

ነሀሴ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ኢሕአግ በሰሜን ጎንደር አርማጭሆ ልዩ ስሙ አዋሳ በተሰኘ አካባቢ ከመንግስት ልዩ ሃይል ታጣቂ ጋር ሐምሌ 28-2004 ዓ∙ም ባካሄደው ውጊያ 11 የመንግስት ቡድን ቅጥረኞችን በመግደልና 19 በማቁሰል አንፀባራቂ ድል ማግኘቱን ለኢሳት በላከው መግለጫ አመልክቷል። በእለቱ የግንባሩ  ሰራዊት የተለመደውን ታሪካዊ ጀብድ ሲያከናውን የአካባቢው ማህበረሰብ ከፍተኛ ድጋፍና አቀባበልም እንዳደረገለት ገልጧል። ማህበረሰቡ የአርበኛ ግንባር ደጋፊ ነህ በሚል ...

Read More »

በማሌዥያ ጫት ይዛ የተገኘችው ኢትዮጵያዊ ተከሰሰች

ነሀሴ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የተከለከለ ዕጽ  በማዘዋወር የተጠረጠረችው ኢትዮጵያዊቷ የቤት እመቤት ጫት ይዛ በመገኘቷ ትናንትና በፍርድ ቤት ክስ እንደተመሰረተባት የተለያዩ የማሌዥያ የዜና አውታሮች ዘገቡ። የ36 ዓመቷ ሙና መሃመድ ኢብራሂም፣ እ.ኤ.አ ሃሙስ ኦገስት 2/ 2012 የማሌዥያው  ኬ.ኤል ዓለም አቀፍ አይሮፕላን ማረፊያ ውስጥ  90 ኪሎግራም የሚመዝን ካቲኖን የተሰኘ እፅ ወይንም ጫት ይዛ በመገኘቷ በቁጥጥር ስር እንደዋለች ታውቋል። ነዋሪነቷ ካናዳ እንደሆነ የተገለፀው ወ/ሮ ...

Read More »

በለንድን ኦሎምፒክ የሴቶች 5000 ሺህ ሜትር የፍፃሜ ውድድር ኢትዮጵያውያኑ የበላይነታቸውን አሳዩ

ነሀሴ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ጠያይሞቹ ንግስቶች ለንደን ላይ  አክሊላቸውን ደፉ።አረንጓዴው ጎርፍ በለንደን ኦሎምፒክ ስታዲየም ፈሰሰ። በሴቶች 5ሺህ ሜትር የ ኦሎምፒክ ውድድር ድንቅ  ታሪክ ተሠራ። 1 ኛ ኢትዮጵያ 3ኛ ኢትዮጵያ 5 ኛ ኢትዮጵያ። የ2004 የ ኦሎምፒክ ሻምፒዮን የሆነችው ጀግናዋ መሰረት ደፋር እንደ ልማዷ በመጨረሻው መቶ ሜትር ላይ ፍጥነቷን በመጨመር እና የኢትዮጵያውያን ተቀናቃኝ የሆነችውን- ኬንያዊቷን የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮን ቪቪያን ...

Read More »

የአቶ መለስ መሰወር የስልጣን ሽኩቻና ፍርሀትን ጋርጧል ተባለ

የአቶ መለስ ለረጅም ግዜ ከስልጣን መሰወር፤ በኢትዮጵያ ውስጥ ድብቅ የስልጣን ሽኩቻ፤ በአፍሪካው ቀንድ ደግሞ፤ ፍርሀትን እንደፈጠረ ፋይናንሳል ታይምስ የተሰኘው ጋዜጣ ዘገበ። መንግስት አቶ መለስ ከሕመማቸው እያገገሙ እንደሆነ ቢናገርም፤ የአቶ መለስ ዜናዊ መሰወር ግን የጎሳ ፖለቲካን አደጋዎች እንዲያገጡ በሚያደርግና፤ ስርአቱን ለአደጋ በሚያጋልጥበት መለኩ ድብቅ የስልጣን ሽኩቻን ጭሯል ሲል ፋይናንሻል ታይምስ ዘግቧል። “ስለአቶ መለስ ጤና ሁኔታ ምንም አይነት መረጃ የለንም” ያለው፤ የኬንያው ...

Read More »

ሲፒጄ አዲሱ የኢትዮጵያ አመራር ሰብአዊ መብት ጥበቃ እንደሚያሻሽል እምነቱን ገለጸ

የአለምአቀፉ ጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት፤ በእንግሊዘኛ ምህጻረ ቃል፤ ሲ.ፒ.ጄ፤ ጠ/ሚ/ር መለስን የሚተካው መሪ በሀገሪቱ ላይ የሰፈነውን የጭቆናና ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ገፈፋ እንደሚያሻሽል እምነቱን ገለጸ። የሲፒጄ የአፍሪካ አድቮኬሲ ሀላፊ የሆኑት ሙሀመድ ኬይታ፤ በተለይ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፤ አምባገነናዊ ስርአት ግዜው ያለፈበት ሁዋላቀርነት መሆኑን አስገንዝበው፤ አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር፤ በአቶ መለስ ዜናዊ አመራር መንግስት የሁዋሊዮሽ የሄደውን የሰብአዊ መብት አያያዝ፤ ወደለየለት ፈላጭ ቆራጭነት ...

Read More »

የኦሎምፒክ ቡድናችን ጥሮ ተፎካካሪ ሆኖ ቀጥሏል

ነሀሴ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአሜሪካ የኦሎምፒክስ ቡድን በ90 ሜዳሊያ ብዛት እየመራ በሚገኝበት የለንደኑ ኦሎምፒክስ ላይ፤ ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ብርቱ ፉክክር ማድረጋቸውን ቀጥለዋል:: በትላንትናው እለት በተካሔደው የ800 ሜትር ውድድር ተሳታፊ የነበረው ኢትዮጵያዊው መሐመድ አማን 6ኛ ደራጃ ያገኘ ሲሆን፤ በዚህ ውድድር ላይ ኬኒያዊው ዴቭድ ሩዲሺያ አዲስ የለም ክብረ ወሰን በማስመዝገብ አሸናፊ ሆኗል:: ኢትዮጵያዊው አትሌት መሐመድ አማን የሜዳሊያ ሰንጠረጅ ውስጥ ይገባል ...

Read More »

አቶ በረከት “አቶ መለስ ዜናዊ ለኢትዮጵያ አዲስ አመት ይመለሳሉ” አሉ

ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በቀናት ውስጥ ወደ ስራ ገበታቸው ይመለሳሉ በማለት የተናገሩት አቶ በረከት ስምኦን፤ የአቶ መለስን ወደስራ ገበታ መመለሻ ግዜ በሳምንታት አሳድገው፤ ወደኢትዮጵያ አዲስ አመት በማስጠጋት መግለጫ ሰጥተዋል። አቶ በረከት ስምኦን፤ በዛሬው እለት አውስትራሊያ ለሚገኘው SBS ሬድዮ በሰጡት ቃለ ምልልስ፤ አቶ መለስን ለምን አታሳዩም በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ፤ “ህዝቡ ያምነናል፤” የሚል ምላሽ ሰትተዋል። የስልጣን ትግል በፓርቲያቸው ውስት ስለመካሄዱ ለተነሳባቸው ጥያቄም፤ ...

Read More »

በደሴ ከተማ ሙስሊሞች ከፌደራል ፖሊስ ጋር ተጋጩ

ነሀሴ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የጁመኣን ሶላት ጸሎት ለማድረስ ዛሬ በደሴ አረብገንዳ የተሰባሰቡ ሙስሊሞች ከፖሊስ ጋር ሲጋጩ ውለዋል። በደሴና አካባቢዋ የሚገኙ ሙስሊሞች አረብገንዳ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ በሚገኘው መስጊድ ለመስገድ በሚሰባሰቡበት ወቅት፣ በስፍራው ሲጠባበቁ የነበሩ የፌደራል ፖሊስ አባላት በመስጊዱ ጸሎት ማድረስ አይቻልም በማለት መከልከላቸውን ተከትሎ ነው ችግሩ የተፈጠረው። ፖሊሶቹ ” ሁላችሁም በአካባቢያችሁ በሚገኙ መስጊዶች መስገድ ትችላላችሁ፣ ወደ ዚህ ቦታ ...

Read More »

ገዢው ፓርቲ ህዝብን ያረጋጋሉ የተባሉ ካድሬዎችን ወደ ገጠር አሰማራ

ነሀሴ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአቶ መለስ ዜናዊ የጤና ሁኔታ ከፍተኛ የህዝብ የመነጋገሪያ አጀንዳ እንደሆነ በቀጠለበት በዚህ ወቅት፣ ገዢው ፓርቲ ህዝብን ለማሳመን ይችላሉ ብሎ የሚያስባቸውን ካድሬዎች ወደ ገጠር መላኩ ታውቓል። የብአዴን ካድሬዎች በአማራ ክልል በሚገኙ ወረዳዎች ህዝቡን እንዲያረጋጉ እንዲሁም የህዝቡን ስሜት እንዲያጠኑና ወደ ማእከል ሪፖርት እንዲያደርጉ ተልከዋል። ካድሬዎቹ ህዝቡን ለማሳመን ምን ማለት እንዳለባቸው በትክክል እንደማያውቁ፣ ይልቁንም ራሳቸው ካድሬዎቹ ...

Read More »

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ተከሰሰ

ነሀሴ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በማስተዋል የህትመትና ማስታወቂያ ሥራ ድርጅት አማካይነት በየሳምንቱ ዓርብ ዕለት እየታተመ ለንባብ የሚበቃው የፍትህ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ተመስገን ደሳለኝና ድርጅቱ ሶስት ክሶች ዛሬ ተመሰረቱባቸው፡፡ የፌዴራሉ አቃቤ ህግ በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 16ኛ የወንጀል ችሎት ክስ የመሰረተባቸው በፍትህ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ተመስገን ደሳለኝ እና በማስተዋል የህትመት እና ማስታወቂያ ስራ ድርጅት ላይ ነው። አቃቤ ህግ በጋዜጠኛ ...

Read More »