የኦሎምፒክ ቡድናችን ጥሮ ተፎካካሪ ሆኖ ቀጥሏል

ነሀሴ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-የአሜሪካ የኦሎምፒክስ ቡድን በ90 ሜዳሊያ ብዛት እየመራ በሚገኝበት የለንደኑ ኦሎምፒክስ ላይ፤ ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ብርቱ ፉክክር ማድረጋቸውን ቀጥለዋል::

በትላንትናው እለት በተካሔደው የ800 ሜትር ውድድር ተሳታፊ የነበረው ኢትዮጵያዊው መሐመድ አማን 6ኛ ደራጃ ያገኘ ሲሆን፤ በዚህ ውድድር ላይ ኬኒያዊው ዴቭድ ሩዲሺያ አዲስ የለም ክብረ ወሰን በማስመዝገብ አሸናፊ ሆኗል::

ኢትዮጵያዊው አትሌት መሐመድ አማን የሜዳሊያ ሰንጠረጅ ውስጥ ይገባል የሚል ግምት ተሰጥት የነበረ ቢሆንም፤ በተለምዶ ይጠቀምበት ከነበረው የአሯሯጥ ዘዴ ወጣ ብሎ፤ ከመጀመሪያው ዙር ጀምሮ ዴቭድ ሩዲሺያን ተከትሎ በመውጣቱ፤ በውድድሩ ፍጻሜ ላይ ፍጥነቱን መጠበቅ ሳይችል ሊቀደም ችሏል::

ይህ በእንዲህ እንዳለ በዛሬው እለት በሚካሄደው የ5000 እና 1500 ሜትር የሴቶች የፍጻሜ ውድድር ላይ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች መሰረት ደፋር ወርቅ እንዲሁም ጥሩነሽ ዲባባ ነሃስ ሜዳሊያ አሸንፈዋል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ተፋላሚዎቿን ጥላ በመውጣት፤ በዳይመንድ ሊጎች ላይ እያሸነፈች ያለችው አትሌት አበባ አረጋዊ፤ የወርቅ ሜዳሊያ ታገኛለች የሚለው ግምት ጨምሯል::

ከዚህ በተጨማሪ ሐምሌ 27 በተካሔደው የአስር ሺህ ሜትር ውድድር ለአገሯ የወርቅ ሜዳሊያ ያስገኘችውና የአለምን ቀልብ ያሳበችው ጥሩነሽ ዲባባ ዛሬ በሚካሔደው የ5000 ሜትር ውድድር ትሳተፋለች::

በዚሁ ውድድር በአቴንሱ ኦሎምፒክስ፤ የ5000 ሜትር የወርቅ ሜዳሊያ ባለድል የነበረችውና፤ በዚሁ ርቀት ከፍተኛ እውቀት ያላት መሰረት ደፋር፤ እንዲሁም ዲያጉ/ደቡብ ኮሪያ በተደረገው የአለም ሻምፒዮን ላይ አሸናፊ የነበረችው፤ ኬንያዊቷ ቼሪዮትም ብርቱ ተፎካካሪ እንደሚሆኑ ይጠበቃል::

እኛም አትሌቶቻችን ውድድሮቻቸውን በድል እንዲወጡ እንመኛለን::

____________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide