አቶ በረከት “አቶ መለስ ዜናዊ ለኢትዮጵያ አዲስ አመት ይመለሳሉ” አሉ

ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በቀናት ውስጥ ወደ ስራ ገበታቸው ይመለሳሉ በማለት የተናገሩት አቶ በረከት ስምኦን፤ የአቶ መለስን ወደስራ ገበታ መመለሻ ግዜ በሳምንታት አሳድገው፤ ወደኢትዮጵያ አዲስ አመት በማስጠጋት መግለጫ ሰጥተዋል።
አቶ በረከት ስምኦን፤ በዛሬው እለት አውስትራሊያ ለሚገኘው SBS ሬድዮ በሰጡት ቃለ ምልልስ፤ አቶ መለስን ለምን አታሳዩም በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ፤ “ህዝቡ ያምነናል፤” የሚል ምላሽ ሰትተዋል።
የስልጣን ትግል በፓርቲያቸው ውስት ስለመካሄዱ ለተነሳባቸው ጥያቄም፤ የመተካካቱን ስራ በጉባኤ ስለጨረስን የስልጣን ትግል የለም ሲሉ አስተባብለዋ።