ሲፒጄ አዲሱ የኢትዮጵያ አመራር ሰብአዊ መብት ጥበቃ እንደሚያሻሽል እምነቱን ገለጸ

የአለምአቀፉ ጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት፤ በእንግሊዘኛ ምህጻረ ቃል፤ ሲ.ፒ.ጄ፤ ጠ/ሚ/ር መለስን የሚተካው መሪ በሀገሪቱ ላይ የሰፈነውን የጭቆናና ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ገፈፋ እንደሚያሻሽል እምነቱን ገለጸ።
የሲፒጄ የአፍሪካ አድቮኬሲ ሀላፊ የሆኑት ሙሀመድ ኬይታ፤ በተለይ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፤ አምባገነናዊ ስርአት ግዜው ያለፈበት ሁዋላቀርነት መሆኑን አስገንዝበው፤ አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር፤ በአቶ መለስ ዜናዊ አመራር መንግስት የሁዋሊዮሽ የሄደውን የሰብአዊ መብት አያያዝ፤ ወደለየለት ፈላጭ ቆራጭነት እንዳያመራ እንደሚአስቆሙ ተስፋቸውን ገልጠዋል።
ሚስተር ኬትታ፤ በመንግሰቱ ሀይለማሪያምና በመለስ አገዛዞች መካከል ያለው ልዩነት፤ በስልጣን ላይ ያለው መንግስት ዜጎችን የሚጨቁነውና የሚረግጠው፤ ህግን ያለአግባብ በመጠቀም መሆኑን አስረድተዋል።