Author Archives: Central

የህወሀቱ መስራች አቶ ስብሀት ነጋ፦”የኢትዮጵያ ሕዝብ ለዲሞክራሲ ብቁ አይደለም” አሉ

ጥቅምት ፲፫ (አስራ ሶስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አቶ ስብሀት ይህን ያሉት   <የኢትዮጵያ የውጪ ጉዳይ ፖሊሲ ከ አቶ መለስ ሞት በሁዋላ ምን ለውጥ ይኖረዋል?>በሚል ርዕስ ከጀርመን  ምክር ቤት አባላት ጋር ባደረጉት ውይይት ነው። በበርሊን በተደረገውና ኢትዮጵያ፤ኬንያ እና ማላዊ ላይ ባነጣጠረው በዚሁ ስብሰባ ኢትዮጵያን ወክለው የተገኙት አቶ ስብሀት ነጋ አቶ መለስ ቢሞቱም ፖሊሲን በተመለከተ ምንም ዓይነት ለውጥ እንደማይኖር ተናግረዋል። <<መለስ አንድ ...

Read More »

የትግራይ ተወላጆች፤ ዘርና ሀይማኖት ላይ ባነጣጠረው የአቶ ስብሀት ንግግር ማዘናቸውን ገለጹ

ጥቅምት ፲፫ (አስራ ሶስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-“አቦይ ስብሃት ፤’ሥልጣን ከአማራውና ከኦርቶዶክሱ በመራቁ ደስ ብሎናል’ሲሉ መናገራቸው አገር ወዳዶቹን የትግራይ ልጆች  አሳዝኖናል ሲሉ በሲያትልና አካባቢው የሚኖሩ ተወላጆች ገለጹ። የትግራይ ተወላጆቹ የ አቶ ስብሀት ነጋን ወደ በርሊን መምጣት በማስመልከት ባወጡት መግለጫ፤ አቶ ስብሀት   ገዛ ተጋሩ በተባለው ፓልቶክ ክፍል ቀርበው ሥልጣን- ከአማራውና ከ ኦርቶዶክሱ በመራቁ ደስ ብሎናል በማለት በመናገራቸው  ምስጢሩ ያልገባቸው አንዳንድ ...

Read More »

ለፓትርያርክ መርቆሬዎስ እና ለአቃቤ መንበረ-ፓትሪያርክ ለአቡነ ናትናኤል የተማጽኖ ደብዳቤ ተጻፈ

ጥቅምት ፲፫ (አስራ ሶስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ  ተዋህዶ ቤ/ክርስቲያን ምዕምናን ዓለም አቀፍ ማህበር፤ ለፓርትያርክ አቡነ መርቆሪዎስና፤ ለአቃቤ መንበር አቡነ ናትናኤል የተማተፅኖ ደብዳቤ ፃፈ። የቤ/ክርስቲያኒቱ አንድነት እንዲጠበቅ ሁለቱም ወገኖች ያስተላለፉትን ውግዘት ያለቅድመ ሁኔታ እንዲያነሱም ጠይቋል። ዋና መቀመጫወን በአሜሪካ ያደረገው የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክርስቲያን መዕመናን ዓለም አቀፍ ማሕበር፤ በቦርድ ሰብሳቢው በአቶ ይስሐቅ ክፍሌ ስም ባወጣው መግለጫ፤ አቡነ ጳውሎስ በሕይወት ...

Read More »

የቀድሞው የኢቴቪ ጋዜጠኛ ሰለሞን መንግስቴ ተናገረ

ጥቅምት ፲፫ (አስራ ሶስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ውስጥ የሚዲያ ነጻነት አስከፊ ደረጃ ላይ በመድረሱ በወር ሶስት አራት ጋዜጠኞ ስራቸውን እንደሚለቁ፤ የቀድሞ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የእንግሊዘኛው ፕሮግራም ባልደረባ ሰለሞን መንግስቴ ለኢሳት ገለጸ። ጋዜጠኛ ሰለሞን መንግስቴ ለኢሳት እንደገለጸው፤ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንና ሬድዮ ጋዜጠኞች፤ እንጀራ ሆኖባቸው በምርጫ ማጣት ይስሩ እንጂ፤ ምንም አይነት የጋዜጠኝነትም ይሁን የኤዲቶሪያል ነጻነት እንደሌላቸው ገልጿል። የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የተቋቋመበት ሕግ ...

Read More »

በአረብ አገራት ለሚሰቃዩ ሴቶች በዋሽንግተን ዲሲ ሰልፍ ተደረገ

ጥቅምት ፲፫ (አስራ ሶስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአራብ አገራት የሚገኙ ሴቶች ኢትዮጵያዊያን ላይ የሚደርስባቸውን ጭቆናና በደል እንዲቆም የሚጠይቅ የእግር ጉዞ ባለፈው ቅዳሜ ጥቅምት 10 ቀን በዋሽንግተን ዲሲ ተካሄደ። መቀመጫው በሲልቨር ስፕሪንግ፤ ሜሪላንድ የሆነው የኢትዮጵያ ሴቶች መብት ማእከል ያዘጋጀው የእግር የተካሄደው ከመሀል ዋሽንግተን ዲሲ ከሚገኘው የነጻነት ታዛ የአሜሪካው ሕግ አውጪ አካል (ኮንግረስ) ከሚገኝበት ካፒቶል ድረስ ሲሆን፤ በሰልፉ ላይ ኢትዮጵያዊያን ሴቶች፤ ...

Read More »

እስክንድር ነጋ ጥቅምት 27 ጠቅላይ ፍ/ቤት ይቀርባል

ጥቅምት ፲፫ (አስራ ሶስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የ18 አመት ጽኑ እስራት የተፈረደበትና ላለፉት 13 ወራት በቃሊቲ እስር ቤት የሚገኘው፤ ታዋቂው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፤ በመጭው ጥቅምት 27 በጠቅላይ ፍርድ ቤት ቀርቦ ይግባኙ እንደሚደመጥ ኢትዮጽያን ሪፖርተር ዘገበ:: በ2001 አም በወጣውና አፋኝ እንደሆነ የሚተቸውን ጸረ ሽብር ህጉን በመጣስ የተከሰሰው እስክንድር ነጋ፤ የከፍተኛው ፍርድ ቤት ውሳኔ ያለበትን የህግ ስህተቶችና የማስረጃ ድክመት ጠቅሶ በመሰረተው ...

Read More »

በገርባ የፌደራል ፖሊስ አባላት 2 ሰዎችን ረሸኑ፣ የሟቾች ቁጥር 4 ደርሷል

ጥቅምት ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በገርባ የፌደራል ፖሊስ አባላት 2 ሰዎችን ረሸኑ፣ የሟቾች ቁጥር 4 ደርሷል :: የአካባቢው ነዋሪዎች ግን የማቾች ቁጥር ሊጨምር ይችላል ይላሉ በአማራ ክልል በደቡብ ወሎ ዞን በገርባ ቀበሌ በትናንትናው እለት የወረዳው ፖሊስ አባላት ሆን ብለው በጫሩት ግጭት 4 ሰዎች ሲገደሉ 2ቱ በልዩ ሀይሎች ተወስደው መረሸናቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል። የኢሳት ዘጋቢ የተለያዩ የአካባቢው ነዋሪዎችን ...

Read More »

አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ፣ ባለሀብቶችን ሊያረጋጉ ነው

ጥቅምት ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከአቶ መለስ ዜናዊ ዜና እረፍት ጋር ተያያዞ በባለሀብቶች በኩል በታየው አለመረጋጋት የተነሳ የዶላር እጥረት መከሰቱ፣ አጠቃላይ የንግድ እንቅስቃሴው መዳከሙንና በአንጻሩም የአገሪቱ ኢኮኖሚ አደጋ ውስጥ መግባቱ ያሳሰበው የአቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ መንግስት የፊታችን ረቡዕ ጥቅምት 14 ቀን 2005 ዓም ከባላሀብቶች ጋር እንደሚወያዩ ታውቋል። አቶ ሀይለማርያም ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር መካሄዱን በመግለጽ እስካሁን ድረስ ያልተረጋጉትን ባለሀብቶች ...

Read More »

የ “መለስ አንደበት” የተሰኘው አዲስ መጽሀፍ በገበያ ቦታዎች ሳይቀር እየተዋወቀ ነው

ጥቅምት ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አዲሱ  የ “መለስ አንደበት” የተሰኘው መጽሀፍ በተለያዩ ከተሞች በገበያ ቦታዎች ላይ ሳይቀር እየተዋወቀ ነው። የአቶ መለስን ፎቶ የለጠፉ መኪኖች በተለያዩ የአገሪቱ ክልሎች እየተዘዋወሩ ህዝቡ መጽሀፉን እንዲገዛ እያግባቡት ነው። መጽሀፉ አቶ መለስ ስልጣን ከያዙበት ከ1983 ዓም ጀምሮ ያደረጉዋቸውን ንግግሮች የሚተነትን ነው። ” መለስና ውጤታማ ጉዞዋቸው” በሚለው ክፍሉ ውስጥ አቶ መለስ የማርክሲዝም ሌኒኒስት ንድፈ ...

Read More »

በሀረር ከፍተኛ የሆነ የውሀ እጥረት ተከስቷል

ጥቅምት ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከአካባቢው ህዝብ የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው የከተማውን የውሀ ችግር ይቀርፋል ተብሎ ከሶስት ወራት በፊት አዲስ የውሀ ፕሮጀክት ቢመረቅም የከተማው የውሀ ችግር አሁንም ተባብሶ ቀጥሎአል። ነዋሪዎች እንደሚሉት 20 ሊትር ውሀ ከአምስት እስከ 10 ብር እየተሸጠ ነው።2 ሊትር የሚይዙ የውሀ ላስቲኮች በ14 ብር እየተሸጡ  ነው።  ውሀው ከሩቅ ቦታ የሚመጣ በመሆኑም ህዝቡ በፈለገው ጊዜ ለማግኘት አልቻለም። ...

Read More »