በአረብ አገራት ለሚሰቃዩ ሴቶች በዋሽንግተን ዲሲ ሰልፍ ተደረገ

ጥቅምት ፲፫ (አስራ ሶስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-በአራብ አገራት የሚገኙ ሴቶች ኢትዮጵያዊያን ላይ የሚደርስባቸውን ጭቆናና በደል እንዲቆም የሚጠይቅ የእግር ጉዞ ባለፈው ቅዳሜ ጥቅምት 10 ቀን በዋሽንግተን ዲሲ ተካሄደ።

መቀመጫው በሲልቨር ስፕሪንግ፤ ሜሪላንድ የሆነው የኢትዮጵያ ሴቶች መብት ማእከል ያዘጋጀው የእግር የተካሄደው ከመሀል ዋሽንግተን ዲሲ ከሚገኘው የነጻነት ታዛ የአሜሪካው ሕግ አውጪ አካል (ኮንግረስ) ከሚገኝበት ካፒቶል ድረስ ሲሆን፤ በሰልፉ ላይ ኢትዮጵያዊያን ሴቶች፤ ወንዶችና ህጻናት ተሳትፈዋል።

የሰልፉ አስተባባሪ፤ ወ/ሮ አያንቱ አበበ ስለሰልፉ ዓላማ አብራርታ እህቶቻችን በአረብ አገራት የሚደርስባቸው ኢሰብአዊ በደል ትኩረት ስላልተሰጠው፤ በተለይ በተሻለ የነጻነት አገራት የምንገኝ ኢትዮጵያዊያን፤ ለእህቶቻችን ልንቆምላቸው ይገባል ብላለች።