Author Archives: Central

የፌደራል ገቢዎች ባለስልጣን የፍትህ ጋዜጣን አሳታሚ ንግድ ፍቃድ አላድስም አለ

ጥቅምት ፳፱ (ሀያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የፌደራል ገቢዎች ባለስልጣን መስሪያ ቤት የንግድ ፈቃድ ፈቃድ ለማደስ የሄዱትን የማስተዋል የህትመት ማስታወቂያ ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ስራ አስኪያጅ እና ስራ አስፈጻሚ አባላት የንግድ ፈቃድ አላድስም በማለት እንደመለሳቸው ምንጮቻችን አስታውቀዋል። ላለፉት 4 አመታት በሀገሪቱ ላይ ያለውን ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ተግዳሮቶች ተቃውሞ ፍትህ ጋዜጣን በማሳተም ለንባብ ሲያበቃ የነበረው ድርጅት ፍቃዱን እንዳያድስ ከበላይ ...

Read More »

ለግራዚያኒ የተሰራው መታሰቢያ እንዲፈርስ ተጠየቀ

ጥቅምት ፳፰ (ሀያ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በኢጣሊያ ሮም አፍሌ ከተማ ለፋሽስቱ አዶልፍ ግራዚያኒ የተሰራውን መካነ መቃብርና መናፈሻ የተቃወመና እንዲፈርስ የጠየቀ ሰላማዊ ሰልፍ እዚህ ዋሽንግተን ዲሲ ተካሄደ። ከትላንት በስቲያ በዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው የጣሊያን ኤምባሲ የተደረገው የተቃውሞ ሰልፍ በሶስት ቀን የአውሮፖላን ድብደባና በመርዝ ጋዝ ከሰላሳ ሺህ በላይ ኢትዮጵያን ላስጨፈጨፈው ፋሽስቱ አዶልፍ ግራዚያኒ በታሰቢያ መሰራቱን በጽኑ አውግዞል። አለም አቀፈ ትብብር ለፍትህ (ገሎባል አሊያንስ ፎር ...

Read More »

አንድ የሲቪል ሰርቪስ ባለስልጣን ሃገር ከዱ

ጥቅምት ፳፰ (ሀያ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአቶ መለስን ሕመምና ሕልፈት ተከትሎ ስርአቱን እየከዱ የሚሸሹ ባለስልጣናት በተለይም የሕውሐት አባላት ቁጥር እየጨመረ መሆኑን ከኢትዮጲያ ለኢሳት የሚደርሱ መረጃዎች እያመላከቱ መጥተዋል። በዚህ መሰረት የፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር እና የሕዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ ሕውሐት አባል አቶ አታክልቲ ሐጎስ ከነቤተሰባቸው ከሃገር መሰደዳቸው ታውቋል። የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት አቶ አታክልቲ ሐጎስ ከነቤተሰባቸው ካናዳ መግባታቸው የተረጋገጠ ሲሆን ...

Read More »

የመከላከያ ሰራዊት አዲሱን መንግስት እንዲቀበሉ ለማሳመን የሚደረገው ግምገማ ቀጥሎአል

ጥቅምት ፳፰ (ሀያ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢሳት የመከላከያ ሰራዊት ምንጮች እንደገለጡት  የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ  ካረፉ እና አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ ከተሾሙ በሁዋላ በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ የሚካሄደው ግምገማ ተጠናክሮ ቀጥሎአል። ከፍተኛ የጦር አዛዦች ግምገማ መጠናቀቁን የጠቆሙት ምንጮች፣ ግምገማው ወደ መካከለኛና ተራ ወታደሮች እየወረደ ነው። በምስራቅ እዝ የሚገኙ እስከ ኮሎኔልነት ማእረግ ያላቸው መኮንኖች ሀረር ውስጥ ...

Read More »

በቃሊቲ ግንቦት 7 እየተባሉ በሚጠሩ እስረኞች ላይ ጥቃት እየተፈጸመ መሆኑ ታወቀ

ጥቅምት ፳፰ (ሀያ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢሳት የቃሊቲ ምንጮቻችን  እንደገለጡት በተለምዶ የአማራ ተወላጅ የሆኑትንና ከፖለቲካ ጋር  በተያያዘ የታሰሩትን  በሙሉ  የማረሚያ ቤቱ ሀላፊዎች ግንቦት7 እያሉ እንደሚጠሩዋቸው ገልጸው፣ በእስረኞች ላይ ኢሰብአዊ ድርጊቶች እየተፈጸመ መሆኑንም ገልጸዋል። ከዚህ ቀደም  በእነ ጀኔራል ተፈራ ማሞ መዝገብ በመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ተከሰው በእስር ላይ በሚገኙት ወታደራዊ መኮንኖች ላይ እጅግ ኢሰብዓዊ የሆነ አሰቃቂ ድብደባ ( ቶርች) የተፈጸመባቸው ...

Read More »

በኢትዮጵያ የአደገኛ አደንዛዥ ዕፅ ምርት እየጨመረ ነው ተባለ

ጥቅምት ፳፰ (ሀያ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የህወሀት ንብረት የሆነው ፋና ራዲዮ ”  ካናቢስ የተባለው የአደንዛዥ ዕፅ ምርት በአዲስ አበባ ፥ ለመልሶ ማልማት የታጠሩ አካባቢዎችን ጨምሮ በደቡብ ክልል ፣ በኦሮሚያ ፣ አርሲና ምስራቅ ሃረርጌ ፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እና በአባይ በረሃ በስፋት እንደሚታይ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን መናገሩን” በመግለጽ ዘግቧል። ባለፈው ዓመት ብቻ መጠኑ ከ400 ኪሎ ግራም በላይ እንዲሁም ያልተመዘነ ...

Read More »

ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ለሁለተኛ ጊዜ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ሆነው ተመረጡ

ጥቅምት ፳፰ (ሀያ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-”ይህች አገር ከማናቸውም የዓለማችን አገሮች በላይ ንብረት አላት። እኛን ሀብታም ያደረገን ግን ያ አይደለም። በታሪክ በጣም  ግዙፍ የሆነ ወታደራዊ ሀይል አለን።ጠንካሮች ያደረገን ግን ያ አይደለም።ዩኒቨርሲቲያችን፣ባህላችን ሁሉ  በዓለማችን ምርጦች የሚባሉ ናቸው።ዓለምን ወደኛ ዳርቻ ያመጡት ግን እነሱ አይደሉም። አሜሪካን  የተለየ ያደረጋት ፤ የምድራችንን የተለያዩ ህዝቦች፤ በህብረት ያስተሳሰረችበት  ሰንሰለት ነው” ለሁለተኛ ጊዜ የተመረጡት 44ኛው  የአሜሪካ ...

Read More »

አዲስ የእስልምና ም/ቤት ተቋቋመ

የ ኢትዮ ጵያ ሙስሊሞችን የመብት ጥያቄ ሲያስተባብሩ በነበሩት የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ላይ ያሸባሪነት ክስ በተመሰረተ ማግስት አዲስ ያእስልምና ም/ቤት መቐቐሙን መንግስታዊ ሚዲያዎች ይፋ አድርገዋል። በቅርቡ የተካሄደውን ምርጫ ተከትሎ የተመረጡት ያእስልምና ም/ቤት አባላት ከሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች የተወከሉ መሆናቸውን ከወጣው ዝርዝር መረዳት ተችሎዋል ። በሳዑዲ አረቢያ የ ኢትዮጵያ ኤምባሲ በዋና ፀሐፊነት እና በቢሮ ሀላፊነት ሲያገለግሉ የቆዩት ሼክ ኪያር መሀመድ አማን በሊቀመንበርነት ...

Read More »

አምነስቲ እስረኞች እንዲፈቱ ጠየቀ

ጥቅምት ፳፯ (ሀያ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የ ኢትዮጵያ መንግስት የሰብአዊ መብታቸው እንዲከበር በመጠየቃቸው አ ፍሶ ያ ሰራቸውን ኢትዮጵያውያን በ አስቸክዋይ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈታ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ለመንግስት ጥሪ አቀረበ ። መንግስት በ አሸባሪነትና የተለያዩ የወንጀል ምክንያት እየፈጠረ ያሰራቸው ሰዎች ያደረጉት ነገር ወይም የጠየቁት ጥያቄ እራሱ ባወጣው በሀገሪቱ ህገመንግስትና በ አለም አቀፍ ህግ ተቀባይነት ያለውና ህጋዊ በመሆኑ ሊታሰሩም ሊከሰሱም ...

Read More »

የኦህዴድ ክፍፍል ወደ ዞን ባለስልጣናትም ወረደ

ጥቅምት ፳፯ (ሀያ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኦህዴድ ክፍፍል ወደ ዞኖች ወርዷል፣ ይህን መንግስት ተቀብለን እንቀጥላለን ወይም አንቀጥልም የሚሉ ሁለት ቡድኖች መፈጠራቸውን አባላቱ ገለጡ ስማቸው እንዳይገለጥ ያስጠነቀቁ የኦህዴድ ባለስልጣናት ለኢሳት እንደገለጡት በኦህዴድ ከፍተኛ አመራሮች የተፈጠረው መከፋፈል ወደ ዞኖች ወርዶ በድርጅቱ ውስጥ ሁለት ቡድኖች እንዲፈጠሩ አድርጓል።   ከፍተኛ ክፍፍል በሚታይበት በሀረሪ ክልል ፣  በአንድ በኩል ይህንን ስርአት ደግፈን መጓዝ አለብን ...

Read More »