አዲስ የእስልምና ም/ቤት ተቋቋመ

የ ኢትዮ ጵያ ሙስሊሞችን የመብት ጥያቄ ሲያስተባብሩ በነበሩት የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ላይ ያሸባሪነት ክስ በተመሰረተ ማግስት አዲስ ያእስልምና ም/ቤት መቐቐሙን መንግስታዊ ሚዲያዎች ይፋ አድርገዋል።

በቅርቡ የተካሄደውን ምርጫ ተከትሎ የተመረጡት ያእስልምና ም/ቤት አባላት ከሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች የተወከሉ መሆናቸውን ከወጣው ዝርዝር መረዳት ተችሎዋል ።

በሳዑዲ አረቢያ የ ኢትዮጵያ ኤምባሲ በዋና ፀሐፊነት እና በቢሮ ሀላፊነት ሲያገለግሉ የቆዩት ሼክ ኪያር መሀመድ አማን በሊቀመንበርነት ተሰይመዋል የተወከሉት ከኦሮሚያ ክልል መሆኑም ተመልክቶዋል። ሼክ ኪያር መሀመድ አማን በ ኦህዲድ በሚመራው ያኦሮሚያ ልማት ማህበር በጂዳ ሪያድ የማህበሩ ሊቀመንበር ሆነው ማገልገላቸውንም የህይወት ታሪካቸው ያስረዳል።

ዶክተር ሼክ መሀመድ ከማል ከአማራ ክልል ፣ ሼክ አባስ ያሲን ከደቡብ ክልል ፣ ሐጂ መሀመድ አደም ከሶማሌ ክልል ፣ ሼክ መሀመድ ድሬሳ ሙሳ ከአፋር ክልል ፣ አብዲል ሀሚድ አቡበክር ከሀረሪ ክልል አብዱል መጂድ ከሊፋ ከቤንሻንጉል ክልል ሼክ ከድር መሐመድ ከትግራይ ክልል አቶ ይስሐቅ አደም ከጋምቤላ ክልል አቶ መሀመድ አሊ ከ አዲስ አበባ ፣ ሼክ አብዱል አዚዝ አሊ ከድሬደዋ ፣ መመረጣቸው ተዘርዝሯል። ከወጣው ዝርዝር መረዳት እንደተቻለው ከትግራይ ክልል የተወከሉት ሼክ ከድር መሀመድ የፌድራል ጉዳዮች የሀይመኖት አማካሪ ናቸው።

የተካሄደውን የ እስልምና ም/ቤት ምርጫ በመቃወም የሚደረገው ተቃውሞ መቀጠሉም ይታወቃል።