Author Archives: Central

በኢትዮጵያ የሚታየውን የኢኮኖሚ ችግር ለመቅረፍ ህዝቡን ማሳተፍ ግድ ይላል ሲሉ አንድ ታዋቂ ኢኮሚስት ተናገሩ

ሚያዚያ ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በሙረይ ስቴት ዩኒቨርስቲ የኢኮኖሚክስ መምህር የሆኑት ፕሮፌሰር ሰኢድ ሀሰን ለኢሳት እንደገለጹት በኢትዮጵያ ውስጥ የሚታየውን የኑሮ ውድነት ለመግታትም ሆነ የአገሪቱን የኢኮኖሚ ችግር ለመቅረፍ መንግስት ህዝቡን ያሳተፈ ስርአት መመስረት አለበት ብለዋል።   መንግስት ኢኮኖሚውን በበላይነት መቆጣጠሩና ከመንግስት ጋር ተለጥፈው የሚገኙት የመንግስት እና የገዢው ፓርቲ ኩባንያዎች ኢኮኖሚውን እስከ ተቆጣጠሩት ድረስ በኢትዮጵያ የሚታየውን የኢኮኖሚ ችግር መፍታት ...

Read More »

የወንዶ ገነት ኮሌጅ ዲን እና የኮሌጁ የፖሊስ ክፍል አዛዥ ታሰሩ

ሚያዚያ ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአዋሳ ዩኒቨርስቲ ስር የሚገኘው የወንዶገነት የደንና የተፈጥሮ ሀብት ኮሌጅ ዲን የሆኑት ዶ/ር ጸጋየ በቀለ እና የኮሌጁ የፖሊስ ክፍል አዛዥ  ሻምበል አለማየሁ ወረታ የታሰሩት የመንግስት ባለስልጣናት የኮሌጁን መሬት በመቁረጥ ለአካባቢው ተወላጅ ባለሀብት ለመስጠት የሚደረገውን እንቅስቃሴ በመቃወማቸው ነው።   አንድ ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ ዩኒቨርስቲው ባለስልጣን ለኢሳት እንደገለጹት ሁለቱም ግለሰቦች የታሰሩት የአካባቢው ባለስልጣናትየኮሌጁን መሬት በመውሰድ ...

Read More »

የዐረና ለትግራይን ልሳን ያደሉ ሰዎች ታሰሩ

ሚያዚያ ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በትግራይ ክልል ማይፀብሪ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የ አረና ለትግራይ ፓርቲን ልሳን ያደሉ ሰዎች መታሰራቸው ተገለጸ። ለ ኢሳት የደረሰው መረጃ እንደ ያመለክተው  ተሾመ ገብረመድህን እና ሰለሞን አባይ የተባሉ ሰዎች   ሚያዝያ13, 2005 ዓመተ ምህረት  አረና    ፓርቲ በምርጫው ለምን እንዳልተሳተፈ የሚያብራራ ጽሁፍ  በማይፀብሪ አካባቢ ሲያድሉ በፖሊስ ተይዘው ታስረዋል። የፓርቲውን ልሳን ለህዝብ በማደላቸው ሳቢያ ወንጀል እንደፈፀሙ ...

Read More »

የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ከእስር ተፈተው አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ ታዘዙ

ሚያዚያ ፲፪ (አስራ  ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በቤንሻንጉል ጉሙዝ በአማራ ተወላጆች ላይ የደረሰውን መፈናቀል ለማጣራት ወደ መተከል ዞን አቅንተው የነበሩት የሰማያዊ ፓርቲ  ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት፣ የፓርቲው ም/ል ሊቀመንበር አቶ ስለሺ ፈይሳና የምስራቅ ጎጃም ዞን አስተባባሪ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ በቃሉ አዳነ በቡለን ወረዳ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ኢሳት በሰበር ዜናው ካቀረበ በሁዋላ ፣ ሶስቱም አመራሮች ማምሻውን ተለቀዋል። አመራሮቹ የታሰሩት ከፌደራል ...

Read More »

በኖርዌይ ለአባይ ግድብ ገንዘብ ለማሰባሰብ የተጠራ ስብሰባ ተበተነ

  ሚያዚያ ፲፪ (አስራ  ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከኦስሎ ወደ 700 ኪሎ ሜትር ርቆ በሚገኘው ስታቫንጋር ከተማ ለአባይ ግድብ ገንዘብ ለማሰባሰብ የተጠራው ስብሰባ በአገሪቱ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን  ከፍተኛ ተቃውሞ እንዲቋረጥ ከመደረጉም በላይ ኢትዮጵያኑ መንግስት የተከራየውን አዳራሽ በመረከብ የራሳቸውን ስብሰባ አካሂደዋል። ኢትዮጵያውኑ ኢህአዴግ ስልጣን ከያዘበት ጊዜ ጀምሮ በአገሪቱ የተፈጸሙ ወንጀሎች ዘርዝረው ለባለስልጣናት አቅርበዋል። በጉዳዩ ዙሪያ በስፍራው የሚገኘውን ወጣት ጌዲዮን ደሳለኝን አነጋግረነዋል።

Read More »

መንግስት ትችቶችን ወደ ሁዋላ በማለት ተጨማሪ መሬቶችን ለውጭ ባለሀብቶች ለመስጠት ማቀዱ ታወቀ

ሚያዚያ ፲፪ (አስራ  ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ኢትዮጵያዊያን ገበሬዎችን በማፈናቀል ለሃገር ውስጥና ለውጪ ባለሃብቶች ሰፋፊ መሬቶችን በማቅረቡ ከፍተኛ ተቃውሞ እየቀረበበት ያለው የኢትዮጽያ መንግስት ይህንኑ ተግባሩን በማጠናከር ሰፋፊ የእርሻ መሬቶች የያዘ ዞን ከማቋቋም በተጨማሪም የግብርና ኢንቨስትመንትን ብቻውን የሚመራ ራሱን የቻለ ተቋም ለመመስረት ማቀዱን ከግብርና ሚኒስቴር የተገኘ ሪፖርት አመለከተ፡፡ የግብርና ኢንቨስትመንትን በፍጥነት እና በተቀናጀ ሁኔታ ለማስፋፋትና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳውን ለማጎልበት እንዲቻል የግብርና ...

Read More »

መኢአድ በአማራ እና በአፋር ህዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለውን የዘር ማጥፋት ወንጀል እንዲቆም ጠየቀ

ሚያዚያ  ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የመላው አንድነት ድርጅት ዛሬ በሊቀመንበሩ በኢንጂነር ሀይሉ አማካኝነት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ህገመንግስቱ በአንቀጽ 25 ሁሉም ሰዎች በህግ ፊት እኩል ናቸው ቢልም የአማራ ህዝብ ሀገርና ትውልድን ለመታደግ በተደረጉ ጸረ ቅኝ ግዛት ትግሎች ሁሉ ከመላው ኢትዮጵያውያን ጋር በመሆን ደሙን አፍስሶ አጥንቱን ከስክሶ እንዳልኖረ ዛሬ በየደረሰበት ቦታ እንደ ውሻ ውጣውጣ እየተባለ ለአመታት ደክሞ ያፈራውን ንብረቱን ...

Read More »

የአውሮፓ ህብረት ባለስልጣናት በኢትዮጵያ የህዝቡ ነጻነት እንዲከበር ጠየቁ

ሚያዚያ  ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአውሮፓ ህብረት የፓርላማ መሪ ማርቲን ሹልትዝ ፣ የኮሚሺኑ ፕሬዚዳንት ሚስተር ጆሴ ማኑኤል  የጎበኙት ጠ/ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ ባሮሶ እና የካውንስሉ ፕሬዚዳንት ሚ/ር ቫን ሩምፒ፣ ኢትዮጵያ በእሰር ላይ የሚገኙትን ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋንና ርእዮት አለሙን ጨምሮ ሌሎች የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ፣ በአገሪቱ ውስጥ የሀዝቡ ነጻነት እንዲከበር፣ የጸረ ሽብር ህጉ እንዲሻሻል፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን ለመቆጣጠር የወጣው ህግ ...

Read More »

መንግስት አዲሱን የፕሬስ ካውንስል በበላይነት ለመምራት እየሰራ ነው

ሚያዚያ  ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የመንግስት ኮምኒኬሽን ጽ/ቤት የመንግስትና የግል መገናኛ ብዙሃንን በተመለከተ እያካሄደ ካለው ሪፎርም ስራ ጋር በተያያዘ ለመወያየት ስብሰባ ቢጠራም፣ መንግስት በቀጥታ በማይመለከተው የፕሬስ ካውንስል ምስረታ አጀንዳ ላይ ሲመክር ውሎአል። ባለፈው ዕረቡ በሒልተን ሆቴል በተጠራው ስብሰባ ላይ የኢትዮጽያ መገናኛ ብዙሃን ም/ቤት በሚል የሚታወቀውን የፕሬስ ካውንሰል በሚመሰረትበት ጉዳይ ላይ የመንግስትና የግል የሚዲያ ባለቤቶችና ከፍተኛ ኃላፊዎች በተገኙበትና ...

Read More »

መኢአድ በአማራ እና በአፋር ህዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለውን የዘር ማጥፋት ወንጀል እንዲቆም ጠየቀ

ሚያዚያ  ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የመላው አንድነት ድርጅት ዛሬ በሊቀመንበሩ በኢንጂነር ሀይሉ አማካኝነት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ህገመንግስቱ በአንቀጽ 25 ሁሉም ሰዎች በህግ ፊት እኩል ናቸው ቢልም የአማራ ህዝብ ሀገርና ትውልድን ለመታደግ በተደረጉ ጸረ ቅኝ ግዛት ትግሎች ሁሉ ከመላው ኢትዮጵያውያን ጋር በመሆን ደሙን አፍስሶ አጥንቱን ከስክሶ እንዳልኖረ ዛሬ በየደረሰበት ቦታ እንደ ውሻ ውጣውጣ እየተባለ ለአመታት ደክሞ ያፈራውን ንብረቱን ...

Read More »