Author Archives: Central

ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ተቃውሞአቸውን አሰሙ

ግንቦት ፴ (ሰላሳ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ግንቦት 30 በአዲስ አበባና  በበርካታ የክልል ከተሞች “የሀይል እርምጃ ለህዝብ መልስ አይሆንም” በሚል ርዕስ  የተጠራው የሙስሊሞች ተቃውሞ በደማቅና  በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁ ታውቋል። በአዲስ አበባና በበበርካታ የክልል ከተሞች ተቃውሞ  ያሰሙት ሙስሊሞች ካስተጋቧቸው መፈክሮች መካከል፦”  መብታችንን ለማስከበር የምናደርገው ትግል በሀይል እርምጃ አይጨናገፍም!፣ ለህዝብ የመብት  ጥያቄ ሀይል መልስ  አይሆንም! የታሰሩት መሪዎቻችን ያለምንም ቅድመ-ሁኔታ ይፈቱ! መንግስት ከሀይማኖታችን ...

Read More »

የባለራእይ ወጣቶች የህዝብ ግንኙት ሀላፊ ከእስር ተለቀቀ

ግንቦት ፴ (ሰላሳ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ግንቦት14፣ 2005 ዓም በደህንነቶች ታፍኖ ከተወሰደ በሁዋላ በማእከላዊ እስር ቤት ያለ ፍርድ ሲሰቃይ የነበረው የባለራእይ ወጣቶች ማህበር የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ የሆነው ወጣት ብርሀኑ ተክለያሬድ በ5 ሺ ብር ዋስ ከእስር መፈታቱ ታውቋል። ወጣት ብርሀኑ ግንቦት27 ለ3ኛ ጊዜ ሜክሲኮ በሚገኘው የአዲስ አበባ ፍርድ ቤት ቢቀርብም ፖሊስ ክስ ለመመስረት ባለመቻሉ ቀጠሮ ተጠይቆበት እንደገና ወደ እስር እንዲመለስ ...

Read More »

በከረዩና አርጎባ ብሄረሰቦች መካከል የተፈጠረው ችግር ተባብሶ ቀጥሎአል

ግንቦት ፴ (ሰላሳ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በሰሜን ሸዋ ዞን ውስጥ በሚገኙት በከረዩ ኦሮሞዎች እና አርጎባ ብሄረሰቦች መካከል በተፈጠረ ግጭት አርጎቦቹ   ከ200 በላይ የከረዩ ብሄረሰብ ከብቶችን በመዝረፍ ወስደዋል።  ባለፈው ማክሰኞ ግንቦት 27 ፣ 2005 ዓም ደግሞ ከረዩዎች ከ120 በላይ የአርጎቦችን ፍየል በመውሰዳቸው ግጭቱ ተባብሶ መቀጠሉ ታውቋል። የፌደራል ፖሊስ አባላት ግጭቱን  እቆታጠራሉ በማለት ጣልቃ ቢገባም በአርጎቦቹ በኩል ተቀባይነት በለማግኘቱ ግጭቱ ሊበርድ ...

Read More »

ሰማያዊ ፓርቲ መንግስት ለቀረቡት ጥያቄዎች በ3 ወራት ውስጥ መልስ እንዲሰጥ አሳሳበ

ግንቦት ፳፱ (ሀያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ፓርቲው ግንቦት29 ቀን 2005 ዓም ባወጣው መግለጫ መንግስት በፓርቲው ላይ መሰረተቢስ ውንጀላ ከማቅረብ ይልቅ ለቀረቡለት ጥያቄዎች መልስ እንዲሰጥ ጠይቋል። የገዥው ፓርቲ ተወካይ ሰልፉን አስመልክቶ “የሐይማኖት አክራሪነት አጀንዳው አድርጎ ሲንቀሳቀስ የነበረው ሰማያዊ ፓርቲ ዛሬ በጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ድብቅ አጀንዳው ገሃድ ወጣ” በማለት የሰጡት አስተያየት መሰረተ ቢስ ፍረጃ መሆኑን የጠቀሰው ፓርቲው ፣ የገዥው ቡድን ...

Read More »

የተለያዩ የግል ተቋማት የህክምና ተማሪዎች የትምህርት ማቆም አድማቸውን ቀጥለዋል

ግንቦት ፳፱ (ሀያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከ14 የግል ኮሌጆች የተሰባሰቡ ከ5 ሺ በላይ የሚጠጉ የህክማን ተማሪዎች  ሰኔ 27፣ 2005 ዓም የጀመሩትን የትምህርት ማቆም አድማ የቀጠሉ ሲሆን መንግስት ለችግራቸው መፍትሄ የማይሰጥ ከሆነ በአድማው ለመግፋት መወሰናቸውን ተናግረዋል። የትምህርት ሚ/ር ባለስልጣናት ተማሪዎቹ በተወካዮቻቸው አማካኝነት ጥያቄያቸውን እንዲያቀርቡ መጠየቃቸውን ፣ የተማሪዎች ተወካይም እስከትናንት ድረስ ከመንግስት ባለስልጣናት ጋር ሲነጋገር ከቆየ በሁዋላ ተማሪዎች ሊያገኙት አለመቻሉን ...

Read More »

የ6ኛ ክፍል ተማሪው የመጀመሪያው ታዳጊ የኢሳት አስተያየት ሰጪ ሆነ

ግንቦት ፳፱ (ሀያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአገራቸው ጉዳይ ላይ ላለፉት 3 አመታት ለኢሳት ስልክ በመደወል አስተያየታቸውን ሲሰጡ የቆዩ በርካታ ኢትዮጵያውያን ቢኖሩም የ12 አመቱ የስድስተኛ ክፍሉ የወንድይራድ ተማሪ ፣ ለኢትዮጵያ ህዝብ መልእክት በማስተላለፍ በኢሳት ታሪክ የመጀመሪያው ታዳጊ አስተየየት ሰጪ ሆኖ ተመዝግቧል። ታዳጊው ግንቦት25 ፣ 2005 ሰማያዊ ፓርቲ በጠራው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ ተገኝቶ  የተመለከተውን ተናግሯል። በጣፋጭ ለዛና በአስደናቂ የቋንቋ አጠቃቀም ...

Read More »

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሚሊኒየሙ የልማት ግብ ሲጠናቀቅ በህገወጥ የገንዝብ ዝውውር ላይ እንደሚዘምት አስታወቀ

ግንቦት ፳፱ (ሀያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አለማቀፍ እውቅና ያላቸውን ሰዎች ያካተተው የተመድ ከፍተኛ ፓናል ፣ የሚሊኒየም የልማት ግቦች መርሀግብር ከሁለት አመት በሁዋላ ሲጠናቀቀር ፣ በህገወጥ መንገድ ከደሀ አገሮች እየተዘረፈ በውጭ ባንኮች  በሚቀመጠው ገንዘብ ላይ ፊቱን እንደሚያዞር  አስታውቋል። ግሎባል ፋይናንሻል ኢንተግሪቲ ከላከው ዜና ለመረዳት እንደተቻለው ፣ በአለፉት 30 አመታት ከአፍሪካ 1 ትሪሊዮን 300 ቢሊዮን ዶላር ተዘርፎ በውጭ ባንኮች ተቀምጧል። ...

Read More »

በትጥቅ ትግል ከሚንቀሳቀሱት ሀይሎች ጋር ግንኙነት አላችሁ የተባሉ የታች አርማጭሆ አንድነት ሰብሳቢ እና ሌሎች 15 ሰዎች ቶርቸር ተፈጸመባቸው

ግንቦት ፳፰ (ሀያ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በሰሜን ጎንደር የታች አርማጭሆ ሰብሳቢ የሆኑት   ሚያዚያ 17 ፣ 2005 ዓም በቁጥጥር ስር በዋሉበት እለት ከፍተኛ ድብደባ እንደተፈጸመባቸው ቤተሰባቸው ለኢሳት ገልጸዋል። እህታቸው ወ/ሮ የንጉሴ ሲሳይ  ወንድማቸው ተዘቅዝቆ ለረጅም ሰአታት እንዲቆይ መደረጉን፣ በእጆቹ ጣቶች  መካከል ብረት እንዲገባ በመደረጉ ጣቶቹ ሽባ መሆናቸውን እንዲሁም እግሮቹ በድበዳ መመለጣቸውን  እያለቀሱ ተናግረዋል። አቶ ተገኝ በድብደባ ብዛት ለመሞት ሲቃረቡ ...

Read More »

በባህርዳር ከ17 ሰዎች ሞት ጋር በተያያዘ ከታሰሩት 22 ፖሊሶች መካከል 4ቱ ተፈቱ

ግንቦት ፳፰ (ሀያ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በቅርቡ በባህርዳር ከተማ 17 ንጹሀን ዜጎችን በግፍ ከገደለው የፌደራል ፖሊስ አባሉ ፈቃዱ ናሻ ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር ከዋሉት የፌደራል ፖሊስ አባላት መካከል 4ቱ ዛሬ ሲለቀቁ፣ 5ቱ ደግሞ ከስራ ተባረዋል። ከዚህ ሌላ  2ቱ ፖሊሶች በከፍተኛ ቁጥጥር ስር እንዲውሉ ሲደረግ፣ 9ኙ ደግሞ በህዳር 11 ፖሊስ ጣቢያ ምርመራ እየተካሄደባቸው ነው። ሥለ ጉዲዩ  ምስክርነት የሰጠችው የፖሊስ ...

Read More »

የተለያዩ የግል ተቋማት የህክምና ተማሪዎች የትምህርት ማቆም አድማ እና የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ

ግንቦት ፳፰ (ሀያ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከ14 የግል ኮሌጆች የተሰባሰቡ 5 ሺ የሚጠጉ ተማሪዎች ትናንት ሰኔ 27፣ 2005 ዓም የትምህርት ማቆም አድማ በማድረግ ወደ ትምህርት ሚኒስቴር አምርተዋል። የትምህርት ሚ/ር ባለስልጣናትም ተማሪዎቹ በተወካዮቻቸው አማካኝነት ጥያቄያቸውን እንዲያቀርቡ ጠይቀው ፣ ተማሪዎቹ የትምህርት ሚኒስቴርን ግቢ ለቀው ካልወጡ በፖሊስ ተገደው እንደሚወጡ ሲነገራቸው ተወካዮችን ወክለው መሄዳቸው ታውቋል። የትምህርት ሚኒስቴር ባለስልጣናትም ተማሪዎች ላቀረቡት ጥያቄ ለዛሬ ...

Read More »