ሰኔ ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በደርግ ዘመን በአየር ድብደባ የሞቱ የሀውዜን ነዋሪዎች እና ታጋዮች ለ5ኛ ጊዜ በመቀሌ ከተማ ታስበው ውለዋል። የመንግስት የመገናኛ ብዙሀን እንደዘገቡት በሀውዜን በደረሰው ጭፍጨፋ ከ2500 በላይ ሰዎች ተገድለዋል፤ በትጥቅ ትግሉም ወቅት 40 ሺ በላይ የህወሀት ታጋዮች ተገድለዋል። የክልሉ ፕሬዚዳንት አባይ ወልዱ ወጣቱ ትውልድ የሰማእታቱን አላማ ከግብ ለማድረስ እንዲረባረብ አሳሰበዋል። በሀውዜን ለደረሰው ጭፍጨፋ ...
Read More »Author Archives: Central
የሱዳኑ ፕሬዚዳንት የአባይ ግድብ ግንባታን እንደሚደግፉ አስታወቁ
ሰኔ ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሱዳን ትሪቢውን እንደዘገበው ፕሬዚዳንት በሽር የግድቡ ግንባታ ለኤሌክትሪክ ሀይል ፍጆታ የሚውል በመሆኑ በግብጽም ሆነ በሱዳን የውሀ ፍጆታ ላይ የሚኖረው ተጽኖ አይኖርም ብለዋል። ግድቡን ለመሙላት በሚያስፈልግበት ወቅት እንኳ በግብጽም ሆነ በሱዳን የውሀ ድርሻ ላይ ተጽኖ አያመጣም ብለዋል። ፕሬዚዳንቱ ኢትዮጵያ የግድቡን ግንባታ እንድትቀጥልም ጠይቀዋል። ፕሬዚዳንት በሽር የሰጡት መልስ ግብጽና ሱዳን ቀድሞ የነበራቸው ጥብቅ ...
Read More »ሙስሊም ኢትዮጵያውያን በወልድያ ጠንካራ ተቃውሞ አሰሙ
ሰኔ ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ተቃውሞው ከአመት በላይ የዘለቀው የድምጻችን ይሰማ ተቃውሞ አንዱ አካል ቢሆንም ፣ የዛሬው የተቃውሞ መነሻ ግን የፌደራል ፖሊሶች ሐሙስ ጧት ከ35 አመታት በላይ ሲያገለግል የነበረውን የወልድያ እርዳታ ማህበር ቢሮ ማሸጋቸውን ተከትሎ የመጣ መሆኑን የአካባቢው ተወላጆች ለኢሳት ገልጸዋል። ሰላም መስጊድ በሚባለው በተደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ድምጻችን ይሰማ ፣ መሐይም አይመራንም” የሚሉና ሌሎች መፈክሮችም ተደምጠዋል። ...
Read More »መድረክ የግብጽን ጥቃት በመከላከያ ብቻ እንመለክታለን ማለት ጊዜው ያለፈበት ስትራቴጂ ነው አለ
ሰኔ ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ስብስብ የሆነው መድረክ በአባይ ወንዝ መጠቀም ተፈጥሮአዊና ህጋዊ መብታችን ነው በሚል ርእስ ባወጣው መግለጫ ፣ አባይንና ሌሎችን ወንዞቻችን ፍትሀዊ በሆነ መንገድ በጋራ መጠቀም ብቸኛውና ዘላቂ መፍትሄ ቢሆንም በግብጽ በኩል ዝግጅትነት ባለመኖሩ፣ ችግሩን በብቃትና በአስተማማኝ መንገድ ለመመከት መፍትሄው አገራዊ መግባባት ነው ብሎአል። ከውጭ የሚቃጣብንን ጥቃት በመድፍ በታንክና በሌሎች የጦር መሳሪያዎች ...
Read More »ከቀደምት የላሊበላ አብያተ ክርስትያናት መካከል አንዱ የሆነው ይምርሃነ ክርስቶስ በመፈራረስ አደጋ ላይ ነው፡፡
ሰኔ ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በመካከለኛው ክፍለ ዘመን ከ1 ሺ 076 እስከ 1 ሺ 116 ዓ.ም በቅዱስ ይምርሃነ ክርስቶስ የተገነቡት እነኚህ ህንፃዎች በዓለምና በኢትዮጽያ ለጎብኝዎች ፣ ለትምህርትና ለጥናት የሚውሉ ቁምነገሮች የሞሉባቸው በመሆኑ ከአደጋ ለማውጣት አፋጣኝ ምላሽ ሊሰጠው ይገባል ሲሉ የቤተክርሲቲያኑ አባቶች ተማጽኖ አቅርበዋል፡፡ ተደጋጋሚ ጥያቄዎችን ለመንግስት ቢያቀርቡም ምላሽ ማጣታቸውን የሚናገሩት አባቶች ፣ ሃዘናቸው ቅርሶችን ለመጠበቅ ሃላፊነቱን በአግባቡ ...
Read More »በብራዚል እየተጠናከረ የመጣውን ተቃውሞ ተከትሎ የአገሪቱ ካቢኔ ለአስቸኳይ ጉባኤ ተጠራ
ሰኔ ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- የህዝብ ማመላለሻ ትራንስፖርት ዋጋ መጨመርን ተከትሎ የተነሳው የህዝብ ተቃውሞ እየተስፋፋ በመሄዱ የአገሪቱ ካቢኔ ለአስቸኳይ ስብሰባ ተጠርቷል። ተቃዋሚዎቹ በመጀመሪያ ያነሱት ጥያቄ ከመንግስት በኩል ምላሽ ቢያገኝም፣ ህዝቡ ግን ሙስናን ለመዋጋት በቂ እርምጃ አልተወሰደም እንዲሁም ለሚቀጥለው አመት ለአለም ዋንጫ ዝግጅት የሚመጣው ወጪ በዝቷል በሚል ተቃውሞውን እንደቀጠለ ነው። በ100 የአገሪቱ ከተሞች ከአንድ ሚሊዮን በላይ ህዝብ ...
Read More »የአሜሪካ ኮንግረስ አባላት በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ዙሪያ ውይይት አደረገ
ሰኔ ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- የአፍሪካ ጉዳዮች ሃላፊ ዶናልድ ያማማቶ፣ በአፍሪካ የዩሴ አይ ዲ ዳይሬክተር ኤሪል ጋስት፣ በአፍሪካ ጉዳዮች ተመራማሪ ዶ/ር ፒተር ፓሀም፣ የግንቦት7 ሊቀመንበር ዶ.ር ብርሀኑ ነጋ ፣ ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶና የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የአሜሪካ ተወካይ ሚስተር አዶቲ አኪዌ እና ሌሎችም ታዋቂ ምሁራን ፖለቲከኞች የተሳተፉበት ውይይት የተካሄደ ሲሆን፣ አምባሳደር ያማማቶ እና ...
Read More »አንድነት ፓርቲ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን አሳትፎ በ3 ወራት ውስጥ ህዝባዊ ንቅናቄ ሊጀምር መሆኑን አስታወቀ
ሰኔ ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ የሆነው ወጣት ዳንኤል ተፈራ ለኢሳት እንደገለጸው ፓርቲው በሚቀጥሉት ሶስት ወራት እና ከዛም በሁዋላ በኢትዮጵያ ውስጥ እየተሸራረፉ ያሉ ሰብአዊ እና ዲሞክራሲያዊ መብቶች እንዲከበሩ ለማድረግ ይሰራል። የጸረ ሽብር ህጉ እንዲሰረዝ፣ የህዝብ ማፈናቀል እንዲቆም፣ የኑሮ ውድነቱ እና የስራ አጥነት ችግር እንዲቀረፍ፣ የንግዱ ማህበረሰብ ፍትሀዊ በሆነ መንገድ እንዲነግድ ሁኔታዎች እንዲመቻቹ እንደሚጠይቅ ...
Read More »መሬታቸው የተወሰደባቸው ከ50-60 የሚጠጉ የመተማ አርሶአደሮች ጫካ መግባታቸውን ሲያስታውቁ ከ30 ያላነሱት ደግሞ ታስረዋል
ሰኔ ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- በመተማ ዮሐንስ እና በኮኪት ቀበሌዎች የሚኖሩ አርሶአደሮች መሬታችን አድሎአዊ በሆነ መልኩ ለባለሀብቶች እየተሰጠብን ነው” በማለት ተቃውሞአቸውን ማሰማታቸውን ተከትሎ ጸረ ሽምቅ እና ልዩ ሀይል የሚባሉ የመንግስት ታጣቂዎች ከ30 ያላነሱትን የአካባቢውን ሰዎች ሲያስሩ፣ በታጣቂዎች ከሚፈለጉት መካከል ደግሞ ከ50- 60 የሚሆኑት አርሶደሮች ጫካ መግባታቸውን አስታውቀዋል። ባለፉት ሳምንታት አቤቱታቸውን አዲስ አበባ ተገኝተው ለም/ል ጠቅላይ ሚኒስትር ...
Read More »ኤጀንሲው በአማራ ህዝብ ቁጥር መቀነስ ዙሪያ ፍተሻ ማድረጉን አስታወቀ
ሰኔ ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- በማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ የሕዝብ ቆጠራ ኮምሽን በ1999/2000 ዓ.ም የሶስተኛው የሕዝብና ቤት ቆጠራ ውጤት ይፋ በተደረገበት ወቅት በተለይ የአማራ ክልል ሕዝብ ብዛት ከሌሎች ክልሎች በተለየ ሁኔታ ከትንበያው ዝቅ ብሎ ተገኝቷል በሚል በቀድሞ የፓርላማ አባላት በቀረበው ቅሬታ ላይ ኮምሽኑ ፍተሻዎችን ማድረጉንና ምንም ዓይነት ስህተት አለማግኘቱን አስታውቋል፡፡ የቤቶች ቆጠራ ኮምሽን ዛሬ ለፓርላማው ያቀረበው ሪፖርት ...
Read More »