የሱዳኑ ፕሬዚዳንት የአባይ ግድብ ግንባታን እንደሚደግፉ አስታወቁ

ሰኔ ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና :-ሱዳን ትሪቢውን እንደዘገበው ፕሬዚዳንት በሽር የግድቡ ግንባታ ለኤሌክትሪክ ሀይል ፍጆታ የሚውል በመሆኑ በግብጽም ሆነ በሱዳን የውሀ ፍጆታ ላይ የሚኖረው ተጽኖ አይኖርም ብለዋል።

ግድቡን ለመሙላት በሚያስፈልግበት ወቅት እንኳ በግብጽም ሆነ በሱዳን የውሀ ድርሻ ላይ ተጽኖ አያመጣም ብለዋል።

ፕሬዚዳንቱ ኢትዮጵያ የግድቡን ግንባታ እንድትቀጥልም ጠይቀዋል።

ፕሬዚዳንት በሽር የሰጡት መልስ ግብጽና ሱዳን ቀድሞ የነበራቸው ጥብቅ ትስስር እየላላ መምጣቱን የሚያሳይ መሆኑን አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ።