Author Archives: Central

የፌደራል ፖሊስ የግዥ አፈፃፀም ሥርዓት ለሙስና የተጋለጠ መሆኑን የጸረ ሙስና ኮምሽን በጥናት አረጋገጠ

ሐምሌ ፰( ስምንት )ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፌዴራል የሥነምግባርና የጸረ ሙስና ኮምሽን በቅርቡ ባካሄደው የአሰራር ሥርዓት ጥናት በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የግዥ አፈፃፀም ለሙስና እና ብልሹ አሠራር የተጋለጠ ነው ብሎአል፡፡ በፖሊስ ኮምሽኑ የተጠና የጠቀሜታ ዝርዝር /ስፔስፊኬሽን/ አዘገጃጀት አሰራር አለመኖር፣ ግዥዎችን በዕቅድና በፕሮግራም አለመፈፀም፣ በጀት መኖሩ ሳይረጋገጥ የግዥ ሂደቶችንማከናወን፣ በግዥ መመሪያው ከተቀመጠው የገንዘብ መጠን በላይ ግዥ መፈፀም እና የጨረታ ኮሚቴው ከግዥ ...

Read More »

በሮመዳን ጾም ጅማሮ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ጠንካራ ተቃውሞ አሰሙ

  ሐምሌ ፭( አምት )ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአዲስ አበባ በአንዋር መስጊድ ከፍተኛ ህዝብ በተገኘበት ተቃውሞ ተካሂዷል። መንግስት የለም ወይ፣ የሼክ ኑር ኢማም ግድያ ድራማ ነው፣ ድራማው ይብቃ፣      መሪዎቻችን ይፈቱ፣ መሀይም አይመራንም፣ በፍትህ እጦት ድፍን አንድ አመት መንግስት ራሱ ገዳይ ራሱ ከሳሽ፣ ። አሸባሪው  መንግስት ነው፣  ፍትሕ ማዳን። ፍትህ እያሉ ቃሊቲ ገቡ ገደሉት ብለው ድራማ ሰሩ። የመንግስት ...

Read More »

በአዊ ዞን የእንጅባራ ከተማ ነዋሪዎች ምሬታቸውን ገለጹ

ሐምሌ ፭( አምት )ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰሞኑን በሁለቱ ከተሞች በተካሄዱት ስብሰባዎች ህዝቡ በመልካም አስተዳደር ችግሮች እየተሰቃየ እንደሚገኝ በድፍረት ለመንግስት ተወካዮች ሲገልጽ ተሰምቷል። በእንጅባራ አንድ ነጋዴ ሲናገሩ የመንግስት ባለስልጣናት የሚያቀረቡዋቸው ሪፖርቶች ለራሳቸው የሚጠቅሙ እንጅ ህዝቡ የሚያያቸው አይደሉም በማለት በማስረጃ አስደግፈው አቅርበዋል። ነጋዴው እንዳሉት እቃዎች ሳይገዙ እንደተገዙ ተደርጎ ይወራረዳሉ፣ ጥራት ያላቸው እቃዎች አይገዙም፣ የመንግስት መጋዘኖችም በባለስልጣናት ይዘረፋሉ። የከተማዋ ባለስልጣናት ከሙስና ...

Read More »

በ1976 ዓ.ም የተቋቋመው አንጋፋው የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ማኔጅመንት ከሠራተኛው ጋር እሰጣ አገባ ውስጥ ገባ

ሐምሌ ፭( አምት )ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ በሀላፊነት ላይ የሚገኙ የድርጅቱ  ሠራተኛ እንደተናገሩት በምክትል ጠ/ሚኒስትር ማዕረግ የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትር የሆኑት አቶ ሙክታር ከድር በቦርድ ሰብሳቢነት ወደመድን ድርጅት ከመጡ ካለፉት ሁለት ዓመታት ወዲህ ዘረኝነትና ግልጽ የሆነ ዘረፋ በድርጅቱ ውስጥ በመንሰራፋቱ  በርካታ ባለሙያዎች ድርጅቱን ለመልቀቅ እየተገደዱ ነው። ችግሩን ቦርዱ ተመልክቶ ሠራተኛውን እንዲያወያይ በተደጋጋሚ ጥያቄ ቢቀርብለትም እነአቶ ሙክታር ፈቃደኛ ...

Read More »

ታዋቂው አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረስላሴ የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ሆኖ በገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ ሊመረጥ እንደሚችል ተጠቆመ

ሐምሌ ፭( አምት )ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሻለቃ ኃይሌ ፕሬዚዳንት የመሆን ፍላጎት እንዳለው ለዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን መግለጹን ተከትሎ ኢህአዴግ መራሹ ራዲዮ ፋና ባልተለመደ መልክ ዜናውን ደጋግሞ እንዳራገበው አንድ የፖለቲካ ተንታኝ ጠቅሰው ፣ ሀይሌ የሰጠውም መግለጫ ሆነ የሬዲዮ  ፋና ዘገባ በድንገት የሆነ ሳይሆን ታቅዶበት የተደረገእንደሚሆን ግምታቸውን አስቀምጠል፡፡ በአሁኑ ወቅት በስልጣን ላይ የሚገኙት መቶ አለቃ ግርማ ወ/ጊዮርጊስ ሁለተኛውን የሥልጣን ዘመናቸውን ...

Read More »

ገዢው ፓርቲ በደሴና ጎንደር የሚካሄዱትን ሰላማዊ ሰልፎች ለማደናቀፍ እየሞከረ ነው የፓርቲው ሰዎች በአቋማቸው ጸንተዋል

ሐምሌ ፬( አራት )ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሀምሌ 7፣ 2005 ዓ/ም በደሴና ጎንደር ከተሞች አንድነት ፓርቲ የጠራቸው የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፎች በታቀደላቸው ጊዜ እንደሚካሄዱ ከመንግስት እውቅና የተሰጣቸው ቢሆንም፣ የገዢው ፓርቲ ካድሬዎችና ባለስልጣናት የቅስቀሳ ወረቀቶችን የሚበትኑትን ሰዎች ከማሰር እና ከማስፈራራት አልፈው ፣ ከአዲስ አበባ የሄዱ የፓርቲው አመራሮች አልጋ እንዳያገኙ የሆቴል ባለንብረቶችን እስከ ማስፈራራት መድረሳቸውን የፓርቲው አመራሮች ለኢሳት ገልጸዋል። የአንድነት ፓርቲ የብሄራዊ ...

Read More »

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ የሰላማዊ ሰልፍለማድረግ ያቀረበው ጥያቄ በአዲስ አበባ መስተዳድር ጽህፈት ቤት ተቀባይነት ሳያገኝ ቀረ።

ሐምሌ ፬( አራት )ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መስተዳድሩ-ለፓርቲው በጻፈው ደብዳቤ- መድረክ ለእሁድ ሐምሌ 7 ቀን 2005 ዓመተ ምህረት ከጧቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 6 ፡00 ሰዓት የሚቆይና ከስድስት ኪሎ ተነስቶ በአራት ኪሎ፣ በፒያሳና በቸርችል ጎዳና በማድረግ  መዳረሻው ድላችን ሐውልት የሚያደርግ ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ ያቀረበውን ጥያቄ እንደተመለከተው በመጥቀስ፤ሰላማዊ ሰልፉ የሚደረግበት የጉዞ መስመር  በአሁኑ ጊዜ እየተዘረጋ ባለው የባቡር መስመር የትራፊክ መስመር እየተጨናነቀ ...

Read More »

ትንታጉ የደቡብ አፍሪካ ፖለቲከኛ ጁሊየስ ማሌማ ፓርቲ መሰረተ

ሐምሌ ፬( አራት )ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ብሄራዊ ኮንግረስ የወጣቶች ሊግ ሊቀመንበር ጁሊየስ ማሌማ ኢኮኖሚክ ፍሪደም ፋይተር የተሰኘ ፓርቲ መስርቷል። ወጣቱ ፖለቲከኛ በነጮች የተያዙት የአገሪቱ መሬት ለህዝቡ እንዲከፋፈል እና  ዋና ዋና የማእድን ፋብሪካዎች በመንግስት ቁጥጥር ስር እንዲውሉ እንደሚታገል አስታውቋል። ማሌማ ፓርቲው ጸረ ካፒታሊዝም መሆኑም ገልጿል። “እኛ ጥቁሮች በዚህ አገር ስንኖር የምናሳያው ነገር የለንም፣ ልናሳየው የሚገባ  ነገር ...

Read More »

አንድነት ፓርቲ በደሴና በጎንደር በመጪው እሁድ ለሚያደርገው የተቃውሞ ሰልፍ ቅስቀሳውን ቀጥሎአል

ሐምሌ ፫( ሦስት )ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኢትዮጵያ ያለውን የሰብአዊ መብቶች ጥሰት፣ የኑሮ ውድነት እና የፍትህ እጦት ለመቃወም ፓርቲው በጎንደርና በደሴ የጀመረውን ቅስቀሳ ወረቀቶችን በመበተን፣ እና በመኪና ላይ በመሆን በየሰፈሩ በመዘዋወር በድምጽ ማጉያ የትግል ጥሪ እያስተላለፈ ነው። በደሴ ከተማ በማስተባበር ላይ የሚገኙት የአንድነት ፓርቲ ብሄራዊ ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ዘካርያስ የማነብርሃንና የፍኖት ነጻነት ጋዜጠኛ የሆነዉ አቶ ወንደወሰን ክንፈ ታግተው ...

Read More »

የኮንዶሚኒየም ተመዝጋቢዎች ገንዘባቸውን ከንግድ ባንክ ውጭ ባሉ የግል ባንኮችም ማስቀመጥ ይችላሉ ተባለ

ሐምሌ ፫( ሦስት )ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መንግስት በ10/ 90 ወይም በ20 / 80 የቁጠባ ስርአት የኮንዶሚኒየም ቤት ለመስራት የሚፈልጉ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ገንዘባቸውን የመንግስት ንብረት በሆነው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ እንዲያስቀምጡ ትእዛዝ ማስተላለፉ የግል ባንኮችን የሚያዳክም ነው የሚል ትችት ሲቀርብ ሰንብቷል። ገንዘባቸውን በግል ባንኮች ያስቀምጡ የነበሩ ደንበኞች ደንበኝነታቸውን  እየሰረዙ በንግድ ባንክ ማስቀመጥ ከጀመሩ ባንኮች በደንበኛ እጥረት ከገበያ ውጭ ...

Read More »