Author Archives: Central

ጠ/ሚኒስትር ኃ/ማርያም ደሳለኝ በኢትዮጵያ ውስጥ አክራሪነት የለም የሚሉ የተቃዋሚ ድርጅቶች አጥፊዎች፣ከሃዲዎች ናቸው አሉ

ጳግሜ ፬(አራት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ጠ/ሚኒስትሩ ትላንትና እና ዛሬ ለሕትመት በበቃው ከመንግስታዊው አዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ላይ እንደተናገሩት “የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች በርግጥም ለኢትዮጽያ ሕዝብ ዴሞክራሲ፣መልካም አስተዳደር ልማትና ሠላምን ለማምጣት አጀንዳ አድርገው የሚንቀሳቀሱ ከሆነ አክራሪነትንና ሽብርተኝነትን ከመንግስት ጎን ተሰልፈው ሊያወግዙ ይገባል ብለዋል፡፡ ” በኢትዮጽያ አክራሪነትና ሽብርተኝነት የለም ብለው የሚያስቡ ከሆነ እነዚህ ሰዎች በኢትዮጵያ ውስጥ የሉም ማለት ነው፡፡ በኢትዮጵያ ...

Read More »

የጠ/ሚ ባለቤት በቤተመንግስት ኑሮ መሰላቸታቸውን ገለጹ

ጳግሜ ፬(አራት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቀዳማዊት እመቤት ሮማን ተስፋዬ የቤተመንግስት ኑሮ የሚመች አለመሆኑንና የቀድሞ ጠ/ሚኒስትርንም አኗኗር በማየት ያዝኑ እንደነበር ተናግረዋል። ቀዳማዊት እመቤቷ ትላንት ከወጣው መንግስታዊው ዘመን መጽሔት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ የቤተመንግስት ሕይወት አስደሳች አይደለም ብለዋል፡፡ “ የቤተመንግስትን ሕይወት ለማንም ተመኝቼው አላውቅም፡፡ የሴቶች ጉዳይን ስናቋቁም ስምንት ወር ተመላልሼበታለሁ፡፡ ዛሬ እናንተ ተፈትሻችሁ እንደገባችሁት እኛም ተፈትሸን ነበር የምንገባው፡፡ እዚህ ግቢ ስገባ ወደጠ/ሚኒስትሩ ...

Read More »

አትሌት ሀይሌ ገብረስላሴ በቢሮክራሲው መማረሩን ገለጸ

ጳግሜ ፬(አራት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ታዋቂው አትሌት ሻለቃ ሀይሌ ገብረስላሴ፣ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚታየው ቢሮክራሲ የኢንቨስትምንት ስራ  ለመስራት ዋነኛው እንቅፋት መሆኑን ከሪፖርተር ጋር ባደረገው ቃለምልልስ ገልጿል። የመብራትና ውሀና መንገድ ችግሮችን በጋራ መቋቋም ይቻላል ያለው ሀይሌ ፣ ቢሮክራሲው ከፍተኛ ችግር መሆኑን ገለጿል። ሀይሌ እንደሚለው የቢሮክራሲው ዋና ምክንያት በራሳቸው የሚወስኑ ባለስልጣናት መጥፋታቸው ነው። በተለያዩ ሀላፊነት ላይ ያሉ ባለስልጣናት በራሳቸው እንዲወስኑ እስካልተደረገ ድረስ ...

Read More »

የአላሳድ መንግስት የኬሚካል መሳሪያ አለመጠቀሙን አስታወቀ

ጳግሜ ፬(አራት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፕሬዚዳንቱ በህዝቤ ላይ የኬሚካል የጦር መሳሪያ የምጠቀምበት ምንም ምክንያት ለም በማለት ለአንድ የአሜሪካ የቴሌቪዥን ጣቢያ ተናግረዋል። አሜሪካ ሶሪያን ብትደበድብ አንዳንድ ደጋፊ አገሮች አጸፋዊ መልስ ለመስጠት መዘጋጀታቸውንም አላሳድ አክለው ገልጸዋል። ይሁን እንጅ እነዚህን አገሮች  በስም ከመግለጽ ተቆጥበዋል። አለም በሶሪያ ላይ ስለሚወደው የሀይል እርምጃ ተከፋፍሎአል። ፕሬዚዳንት ኦባማ በሶሪያ ላይ እርምጃ ካልተወሰደ ሌሎች አምባገነን መንግስታት ህዝባቸውን በተመሳሳይ ...

Read More »

የጎንደር ህዝብ በአስተዳደሩ መማረሩን ገለጸ

ጳጉሜ ፩(አንድ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከሳምንት በፊት የቀድሞው የኮምኒኬሽን ሚ/ርና የአሁኑ ጠ/ሚ ሀይለማርያም ደሳለኝ አማካሪ አቶ በረከት ስምኦን በመሩት ስብሰባ ላይ ህዝቡ በአስተዳደሩ መማሩን ገልጿል። 50 በመቶ የጎንደር ከተማ ነዋሪ መኖሪያ ቤት የለውም፣ ያሉት አንድ ተናጋሪ ህዝቡ በችግር እየተጠበሰ ስለልማት ቢያወሩት አይገባውም ብለዋል። ህዝቡ መብቱን ሲጠይቅ ተቃዋሚ ነህ እየተባለ እንደሚዘመትበት እኝሁ ግለሰብ አክለው ተናግረዋል። አንድ ሌላ ተናጋሪ ደግሞ አመራሮች ...

Read More »

የዜጎች መፍለስ ለተቃዋሚዎች እየበጀ መሆኑን ኢህአዴግ ገለጸ

ጳጉሜ ፩(አንድ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የግንባሩ ልሳን የሆነው  አዲስ ራእይ እንደገለጸው በህገወጥ መንገድ የሚፈልሱ ሰዎች የመንግስትን ፕሮግራሞች የማይደግፉ ሀይሎችን በመቀላቀል፣ ከጸረ ህዝቦች ጎን እንዲሰለፉ እየተደረጉ በመሆኑ አደጋ ደንቅረዋል። ልሳኑ ” የዜጎች በህገወጥ መንገድ መፍለስ ለፖለቲካ ፍጆታ በር እንደሚከፍት መታሰብ ያለበት ጉዳይ ነው” ካለ በሁዋላ ” በአሁኑ ወቅት በአገራችን እየተገነባ ያለው የዲሞክራሲ ስርአት ግንባታ መልካም አስተዳደርና ከድህነት ለመውጣት እያደረግን አለነው ...

Read More »

አሜሪካና ሩሲያ በሶሪያ ጉዳይ ሳይግባቡ ቀሩ

ጳጉሜ ፩(አንድ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሩሲያ በተካሄደው የቡድን 20 አገራት ስብሰባ ላይ የተገኙት የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ፣ ከሩሲያው አቻቸው ጋር በሶሪያ ላይ ስለሚወሰደው እርምጃ ቢመክሩን ስምምነት ላይ ሳይደርሱ መቅረታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል። ፕሬዚዳንት ፑቲን በሶሪያ  የኬሚካል የጦር መሳሪያ ጥቅም ላይ መዋሉን አገራቸው ብትቀበልም ድርጊቱን የፈጸሙት ተቃዋሚዎች እንጅ የባሽር አላሳድ መንግስት አለመሆኑን ገልጸዋል። ተቃዋሚዎች የአለማቀፉ ማህበረሰብ ጣልቃ እንዲገባ በማሰብ ድርጊቱን ...

Read More »

ሰማያዊ ፓርቲ የተቃውሞ ሰልፉን አራዘመ

ነሃሴ ፴(ሠላሳ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፓርቲው የህግ ክፍልና የተቃውሞ ሰልፍ አስተባባሪ የሆኑት አቶ ይድነቃቸው  ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ የመስተዳድሩ ባለስልጣናት ቀኑ የበአል ዋዜማ በመሆኑ እና  የንግድ ድርጅቶችም እንቅስቃሴ የሚያደርጉበት በመሆኑ ሰልፉን ለማስተናገድ እንደማይችሉ በመግለጻቸው ለማራዘም እንደወሰኑ ገልጸዋል። አንድነት ፓርቲ መስከረም 5፣ 2006 ዓ/ም  የጠራው የተቃውሞ ሰልፍ በመኖሩ በሳምንቱ ሰልፉን ለማካሄድ መወሰናቸውን አስተባባሪው ገልጸዋል። በሌላ በኩል ደግሞ አንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ...

Read More »

በኢትዮጵያ ከሚሊዮን በላይ በልመና የሚተዳደሩ ሰዎች አሉ ተባለ

ነሃሴ ፴(ሠላሳ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የማህበራዊ ኑሮ ጠንቆች ሲል ባስጠናው እና በዓመቱ መጠናቀቂያ በወርሐ ጳጉሜ ይፋ በሚያደርገው መረጃ እዳመለከተው የልመና ተዳዳሪነት በሐገሪቱ ላይ ጥቁር ጥላውን እያጠላበት ሲሆን ከጊዜ ወደ ጊዜ የቱሪስቶች የደህንነት ስጋት ከመሆን ባለፈ ለዜጎችም መትረፋቸውን ገልጿል። በመገባደድ ላይ ባለው በ2005 ዓ.ም ብቻ በአማራ ክልል ከሶስት መቶ ሺ ፣ በትግራይ ከሁለት መቶ ሺ ...

Read More »

የአርበኞች ግንባር አባላት ናቸው የተባሉ ሰዎች ፍርድ ቤት ቀረቡ

ነሃሴ ፴(ሠላሳ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሰሜን ጎንደር ዞን ነዋሪ የሆኑት ጸጋው አለሙ፤ ዋስይሁን ንጉሱ፤ ጎዳዳው ፈረደ፤ ማማይ ታከለ እና ተገኝ ሲሳይ የተባሉት ሰዎች በኤርትራ ስልጠና ካገኙ በሁዋላ ወደ ኢትዮጵያ ሲመለሱ በትግራይ ክልል ማካይዳ ከተማ መያዛቸውን ፋና ዘግቧል። ተከሳሾች  ኤርትራ እና አውሮፓ ከሚገኙ የአሸባሪው ድርጅት የተለያዩ አመራሮች ጋር ግንኙነት በመፍጠር አባላትን እየመለመሉ ወደ ኤርትራ መላካቸውን ገልጾ ፣ የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድቤት ...

Read More »