ጥር ፳፮ (ሃያ ስድት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከውስጥ አዋቂ ምንጮች ለማዎቅ እንደተቻለው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የሚታየውን የመኖሪያ ቤቶች ችግር በዘላቂነት ለማቃለል በሚል ከዚህ በፊት ከነበረው የ 20/80 የጋራ መኖሪያ ቤት ልማት ፕሮግራም በተጨማሪ በአማራጭ የ 10/90 አነስተኛ ገቢ ላላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች እና ለመለስተኛና መካከለኛ ገቢ ላላቸው በ40/60 የቁጠባ ቤት ፕሮግራም መቅረጹን ተከትሎ እስከ ...
Read More »Author Archives: Central
ብኢኮ ለሙስና የተጋለጠ ድርጅት መሆኑን የጸረ ሙስና ኮሚሽን አስታወቀ
ጥር ፳፮ (ሃያ ስድት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በጀኔራል ክንፈ ዳኛው ስራ አስኪያጅነት የሚመራው በስሩ ከ13 በላይ ኩባንያዎችን ዬያዘውና በብዙ ቢሊዮን ብር ካፒታል የተቋቋመው የመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ወይም ብኢኮ አሰራር ግለጽነት የጎደለው መሆኑን የጸረ ሙስና ኮሚሽን ባወጣው የ6 ወራት ሪፖርት ገልጿል። ብኢኮ ከተቋቋመበት ከ1995 ዓም ጀምሮ አሰራሩ ለሙስና በር የሚከፍት መሆኑ በተደጋጋሚ በኢሳት ሲዘገብ ቆይቷል። በጥቂት የህወሃት ጄኔራሎች በሚመራው ...
Read More »የባለስልጣናት ጣልቃ ገብነት የጋዜጠኞችንና የሚዲያ ነፃነትን ገፏል ሲሉ ጋዜጠኞች ተናገሩ
ጥር ፳፮ (ሃያ ስድት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሚኒስትሮች በሚመራው የጋዜጠኞች ስልጠና ላይ የኢህአዴግ ባለስልጣናት ጣልቃ ገብነት የጋዜጠኞችን እና የሚዲያውን ነፃነት የገፈፈ መሆኑን የስልጠናው ተሳታፊ የሆኑ ጋዜጠኞች ተናገሩ፡፡ ባህርዳር ከተማ በማካሄድ ላይ ባለው በዚህ የጋዜጠኞች ስልጠና ላይ ” የፕሬስ ነፃነት በሀገሪቱ ሊኖር ባለመቻሉ የመንግስት መገናኛ ብዙሀን ድርጅት ጋዜጠኞች ሳይቀር ተሸማቀው እንዲሰሩ እየተደረገ ያለው የአስራር ስርዓት እስከ መቼ ፍፃሜ ያገኛል?” ...
Read More »ኔልሰን ማንዴላ 4 ሚሊዮን ዶላር የሚገመት ንብረት እንደነበራቸው ተዘገበ
ጥር ፳፮ (ሃያ ስድት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቢቢሲ ባወጣው ዘገባ እውቁ የነጻነት ታጋይና በቅርቡ ከዚህ አለም የተለዩት ኔልሰን ማንዴላ ሀብቱን ያፈሩት በጆሀንስበርግ እና በኬፕ ታውን ከነበራቸው ቤት ሽያጭ እንዲሁም ከመጽሃፋቸው ከተገኘ ገቢ ነው። ማንዴላ ከእርሳቸው ጋር ሲሰሩ ለነበሩት ለእያንዳንዳቸው 50 ሺ የደቡብ አፍሪካ ገንዘብ እንዲሁም እርሳቸው የተማሩባቸው ትምህርት ቤቶች 100 ሺ ራንድ እንዲሰጣቸው ተናዘዋል። ለአራት የትምህርት ተቋማትም ለእያንዳንዳቸው ...
Read More »የአማራው ክልል መሪ በአማራው ህዝብ ላይ ተሳለቁ
ጥር ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአማራ ክልል ም/ ፕሬዚዳንት እና የብአዴን ጽ/ቤት ሃላፊ የሆኑት አቶ አለምነው መኮንን “የአማራው ህዝብ ሰንፋጭ የሆነ ትምክተኝነት የተጠናወተው በመሆኑ በቤንሻንጉልና በሌሎችም ቦታዎች ለመሰደዱ ምክንያት ሆኖታል” በማለት፣ ለብአዴን ነባርና አዳዲስ ካድሬዎች ተናግረዋል። ካድሬዎቹ “የአማራው ህዝብ ለምን ይሰደዳል? ለምን በእየክልሉ ጥቃት ይደርስበታል? አማራውን ከጥቃት ለመከላከል ለምን ሙከራ አይደረግም በማለት ጥያቄ ያቀረቡ ሲሆን፣ ም/ል ...
Read More »በሀረማያ ዩኒቨርስቲ በርካታ ተማሪዎች በፖሊሶች ተደበደቡ
ጥር ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፈው ማክሰኞ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ ትናንት የዩኒቨርስቲ ግቢውን ለቀው በመውጣት ላይ በነበሩ ተማሪዎች ላይ የፌደራል ፖሊስ በወሰደው እርምጃ የአንዲት ተማሪ ጆሮ መቆረጡንና በርካታ ተማሪዎች እጆቻቸውና እግሮቻቸው መሰበሩን ተማሪዎችና የዩኒቨርስቲው መምህራን ለኢሳት ገልጸዋል። ችግሩ የተፈጠረው የውሃ ኢንጂነሪንግር ተማሪዎች የትምህርት ዘርፍ ለውጥ እንዲደረግ መጠየቃቸውን ተከትሎ ነው። ዩኒቨርስቲው የትምህርት-ዘርፍ ለውጥ እንደማያደርግ እና መማር የማይፈልጉ ...
Read More »ኢህአዴግ ሚኒስትሮቹን የግንባሩን ስራ እንዲያከናውኑ መደበ
ጥር ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢህአዴግ ፓርቲውን እንዲመሩ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን እና ሌሎች ሁለት ሚኒስትር ዴኤታዎችን ባለፉት ወራት መሾሙን ውስጥ አዋቂ ምንጮች ጠቆሙ፡፡ ኢህአዴግ የመንግስት መዋቅርን ከፓርቲው መዋቅር ጋር አደበላልቆ በመስራት ላይ እንደሚገኝ ተደጋጋሚ ወቀሳዎችና ትችቶች እየቀረቡበት የቆየ ሲሆን በዚህ መልኩ ግልጽ የሆነ አደረጃጀት በመያዝ የመንግስት ከፍተኛ አመራሮችን ሲመድብ ከአቶ መለስ ሞት በሃላ ...
Read More »የመንግስት ባለስልጣናት የ7 ሚሊዮን ብር መኪና መግዛት ማቆም አለባቸው ሲሉ አፈ ጉባኤው ተናገሩ
ጥር ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አባ ዱላ ገመዳ ይህን የተናገሩት በዛሬ የፓርላማ ውሎ ላይ ነው። የመንግስት መስሪያ ቤቶች በአገር ውስጥ የተመረቱ ምርቶችን መጠቀምና በ7 ሚሊዮን ብር የሚገዙ መኪኖችን መጠቀም ማቆም አለባቸው ብለዋል። ኢሳት አዲስ አበባ መስተዳድር ሰሞኑን እጅግ ዘመናዊ መኪኖቹን በብዙ ሚሊዮን ዶላር ለባለስልጣነቱ ገዝቶ ማከፋፈሉን መዘገቡ ይታወሳል።
Read More »የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ጎንደር ላይ ታሰሩ
ጥር ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከድንበር ጋር በተያያዘ በኢትዮጵያ እና በሱዳን መንግስታት መካከል ያለው ንግግር ለህዝብ ግልጽ እንዲሆን ለመጠየቅ በመጪው እሁድ በጎንደር ከተማ ለማካሄድ የታቀደውን ሰልፍ ለማስተባበር ወደ ጎንደር ያቀኑት የሰማያዊ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ፣ ሌሊት ከተማዋ ደርሰው በማግስቱ የቅስቀሳ ስራ ሲጀምሩ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለዋል። አመራሮቹ ሲታሰሩ የተመለከተ አንድ ታዛቢ ከኢሳት ጋር ባደረገው አጭር ቆይታ ...
Read More »ኢህአዴግ ልማቱን ለመጨረስ ከ40 እስከ 45 አመት ያስፈልገዋል ሲሉ አቶ በረከት ተናገሩ
ጥር ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የጠ/ሚንስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ አማካሪ የሆኑት አቶ በረከት ስምዖን ይህን የተናገሩት ለኢህአዴግ ከፍተኛ ካድሬዎች ነው። ለማንኛውም የመገናኛ ብዙሃን ዝግ በሆነው የካድሬዎች ስብሰባ ላይ ጥናታዊ ወረቀታቸውን ያቀረቡት አቶ በረከት፣ ኢህአዴግ የህዝቡን የነፍሰ ወከፍ ገቢ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ለማድረስ ቢያንስ ከ40 እስከ 50 ዓመታት እንደሚያስፈልገው ገልጸዋል። አቶ በረከት የወደፊቱ የህዳሴ መንገድ በሚል ባቀረቡት ጽሁፍ ...
Read More »