Author Archives: Central

በሃረር ልጃቸው በእስር ቤት ውስጥ የተገደለባቸው አባት ፍትህ እንደላገኙ ገለጹ

ሚያዚያ ፲፬ (አስራ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፈው መጋቢት ወር በሃረር የተነሳውን የእሳት ቃጠሎ ተከትሎ እቃ ሰርቀሃል በሚል የ21 ዓመቱ ወጣት ዳንኤል ጎሳ በእስር ቤት ውስጥ ለብቻው እንዲታሰር ተደርጎ ከፍተኛ ደብደባ ተፈጽሞበት መሞቱን ኢሳት የእስር ቤት ምንጮችን ዋቢ አድርጎ ከዘገበ በሁዋላ ወላጅ አባቱ  አቶ ጎሳ አበበ ፣ የልጃቸውን አሟሟት ትክክለኛ መንስኤ ለማጣራት ጥረት ቢያደርጉም እስካሁን እንዳልተሳካለቸው ገልጸዋል። አቶ ጎሳ ...

Read More »

ከ800 ሚሊዮን ብር በላይ ያልተወራረደ ገንዘብ መኖሩን የመንግስት ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት አስታወቀ

ሚያዚያ ፲፬ (አስራ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፌድራልዋናኦዲተርለተወካዮች ምክር ቤት የ2005 በጀት አመት ሪፖርትን ባቀረረበት ወቅት በ77 የመንግስት መስሪያ ቤቶች ውስጥ 8 መቶ 87 ሚሊዮን 45 ሺ 264 ብር  ከ60 ሳንቲምያልተወራረደ ገንዘብ መኖሩን ይፋ አድርጓል። የገንዘብ አያያዝን በተመለከተ በአምስትመስሪያቤቶች ውስጥ በተደረገ የናሙና ጥናት ከ1 ሚሊዮን ብር በላይ ገንዘብ ጉድለት መገኘቱም ተገልጿል። አምና መከላከያን ጨምሮ በተደረገው ምርመራ ከ3 ቢሊዮን ብር ...

Read More »

በደቡብ ምእራብ ሃገረ ስብከት ከ35 በላይ ካህናት ተባረሩ

ሚያዚያ ፲፬ (አስራ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አንዳንድ የሃይማኖት አባቶች ለኢሳት እንደገለጹት አዲሱን ጳጳስ አቡነ ማቲያስን እንዲሁም የሀገረ ሰብከቱን ዋና አስተዳዳሪ አቡነ ሳዊሮስን አትደግፉም የተባሉ ከ35 በላይ ካህናት ከሃላፊነት የተነሱ ሲሆን፣ ይህን ተከትሎም የሆሳእና በአል እለት በወሊሶ ረብሻ ተነስቶ ነበር። ምእመናኑ የተባረሩት የሃይማኖት አባቶች እንዲመለሱ እንዲሁም አዳዲስ ሹሞች እንዲወርዱ ጠይቀዋል። የፌደራል ፖሊስ ጣልቃ ገብቶ ለማረጋጋት ሞክሯል። አቡነ ሳዊሮስ ለጸሎት ...

Read More »

የሼህ አላሙዲን አጎት ባለቤት በድጋሜ ታስረው ተፈቱ  

ሚያዚያ ፲፬ (አስራ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የሼህ ሙሃመድ አላሙዲን አጎት ባለቤት የሆኑት ወ/ሮ ኬርያ  አህመድ  አደም በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ለሁለተኘ ግዜ ለሶስት ቀናት ታስረው ተፈትተዋል። አቶ መርዱፍ የሳውዲይ ዜግነት ያላቸው ሲሆኑ  የሼክ አላሙዲን  ንብረት የሆነው  የማምኮም ፋብረካ ስራስኪያጅ ናቸው:: ወ/ሮ ኬርያ አህመድ አደም  ኬር ፊትነስ ሴንተር የሚባል የንግድ ድርጅት አዲስ አበባ  ቺቺንያ እየተባለ በሚጠራው አካባቢና በወሎ ሰፈር ሲኖራቸው በካዛንችስ አካባቢ በሚገኘው በኢሲኤ  ሁለት ...

Read More »

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በደቡብ ሱዳን በበንቲው ግዛት የተካሄደውን የዘር ማጽዳት ዘመቻን በጥብቅ አወገዘ

ሚያዚያ ፲፬ (አስራ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የሰብአዊ እርዳታ ተጠሪ ቶቢ ላንዘር: በደቡብ ሱዳን የተካሄደው ዘግናኝ ግድያ በጣም እንዳሳዘናቸው በመግለጽ ድርጊቱን የፈጸሙት ሰዎች ባስቸኳይ ለፍርድ እንዲቀርቡ ጠይቀዋል:: ቶቢይ ላንዘር  አንዳንድ ግለሰቦች የራዲዮ ጣብያን በመጠቀም ላደረጉት የጥላቻ ቅስቀሳ ተጠያቂ መሆናቸውንም ተናግረዋል። ችግሩ በዚህ  ከቀጠለ በመጪው የፈረንጆች አዲስ  አመት ከዚህ የበለጠ አሰቃቂ አደጋ ሊያጋጥም እንደሚችል ስጋታቸውን  ገልጸዋል:: ይህ በዚህ እያለ የዑጋንዳ መከላከያ ሃይል ቦር የሚገኘውን ...

Read More »

የኢሳትየድጋፍኮሚቴበኖርዌይየባንክሒሳብቁጥርከፈተ

ሚያዚያ ፲፬ (አስራ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳትኖርዌይየድጋፍኮሚቴ፤በኦስሎናበተለያዩአካባቢዎችኢሳትን  ለማጠናከርናየአቅማቸውንለማበርከትለሚተጉየኢሳትደጋፊዎችናቤተሰቦች፤በያሉበትቀላልእናአመቺየሆነውንየአከፋፈልመንገድይጠቀሙዘንድበማሰብ፤በኖርዌይኦስሎበኢሳትስም  የባንክሒሳብቁጥርመክፈቱንበደስታገልጿል። በተለያየምክንያትየባንክሒሳብቁጥራችንለመጠቀምሁኔታዎችየማያመቿችሁየኢሳትደጋፊዎችለዚሁበተዘጋጁየገነዘብመቀበያደረሰኞችበመጠቀምኢሳትንበመደገፍለድምፅአልባወገንዎድምፅ እንዲሆኑ ኮሚቴው አስታውቋል። የሂሳብ ቁጥሩን በድረገጻችን የምታገኙት መሆኑን ለማስታወቅ እንወዳለን። የባንክ ሒሳብ ቁጥር DNB 1503 462 8537 Oslo Norway ሲሆን ለተጨማሪ መረጃ ፦ 452 06 390 / 947 11 734  ይደውሉ ። የኢሳት የድጋፍ ኮሚቴ በኖርዌይ

Read More »

በአፋር የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ 8 ሰዎች በፌደራል ፖሊሶች ተገደሉ

ሚያዚያ ፲፫ (አስራ ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቁርቁራ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ በአፋር እና በሶማሊ ጎሳ አባላት መካከል የተነሳውን ውዝግብ ተከትሎ የፌደራል ፖሊስ በወሰደው እርምጃ 8 ሰዎች መገደላቸውን የአካባቢው ሰዎች እና የአፋር ሰብአዊ መብቶች ድርጅት ሲገልጽ ፣ አፋር ህዝብ ፓርቲ ባወጣው መግለጫ ደግሞ የሟቾቹን ቁጥር 12 አድርሶታል። የፌደራል ፖሊስ የወሰደውን እርምጃ ተከትሎ በአዋሽ ሰባት ኪሎ አካባቢ ህዝቡ ወደ ወደ አውራ ...

Read More »

በአዊ ዞን የሚገኙ የመኢአድ አባላት ስቃይ እየደረሰባቸው ነው

ሚያዚያ ፲፫ (አስራ ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢሳት ያነጋገራቸው በአዊ ዞን የሚኖሩ የመኢአድ አባላት እንደተናገሩት የመንግስት ታጣቂዎች ኢህአዴግ አባላት ለመሆን ፈቃደኛያልሆኑ የፓርቲውን አባላት እያሳደዱና ድብደባ እየፈጸሙባቸው ነው። አቶ ዘሪሁን ባንቲሁን የተባለው አርሶ አደር ለኢሳት እንደገለጹት ሁለት መለዮ የለበሱ ታጣቂዎች ምሽት ላይ ቤታቸውን አስከፍተው በፈጸሙባቸው ድበደባ ለከፍተኛ አካል ጉዳት ተዳርገዋል። ሌሎች የመኢአድ አባላትም እንዲሁ የገዢው ፓርቲ አባላት ካልሆናችሁ በሚል ተመሳሳይ ...

Read More »

የስቀለት በአል እየተከበረ ነው

ሚያዚያ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የክርስቶስ እየሱስን ስቅለት ለመዘከር በየአመቱ የሚከበረው የስቅለት በአል ዘንድሮም በጾምና በጸሎት እየተከበረ ነው። የኢሳት ዘጋቢ ያነጋገራቸው አንዳንድ ምእመናን በጾም በጸሎትና ስግደታቸው ወቅት እግዚአብሄር ኢትዮጵያን እንዲጎበኝ መለመናቸውን ተናግረዋል። “በአገራችን ችጋር ጠፍቶ ሁሉም በደስታ እንዲኖር እመኛለሁ” የምትለው አንዲት የ19 ዓመት ወጣት፣ የዘንድሮው የፋሲካ በአል ለሁሉም ደስታን ይዞ እንዲመጣ ተመኝታለች። ከጾም ጸሎት በተጨማሪ የታመሙትን በመጠየቅ ...

Read More »

በጭልጋ የተነሳው ተቃውሞ ሊያገረሽ እንደሚችል ተማሪዎች አስጠነቀቁ

ሚያዚያ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፉት ሶስት ቀናት ከቅማንት ህዝብ የማንነት እና የአስተዳደር ጥያቄ ጋር ተያይዞ የተነሳው ተቃውሞ ዛሬ ጋብ ብሎ የዋለ ቢሆንም፣ መንግስት ያሰራቸውን የብሄረሰቡን ወኪሎችና መምህራኖችን የማይፈታ ከሆነ፣ ነገ ቅዳሜ በድጋሜ  ተቃውሞ እንደሚያስነሱ ተማሪዎች አስጠንቅቀዋል። የወረዳው ባለስልጣናት በበኩላቸው ቀሳውስቱንና አገር ሽማግሌዎችን በመያዝ ከተማሪዎች ጋር ለመነጋገር የሽምግልና ጥረት ጀምረዋል። የልዩ ሃይል የፖሊስ አባላት ዛሬም ድረስ በአይከል ...

Read More »