በአዊ ዞን የሚገኙ የመኢአድ አባላት ስቃይ እየደረሰባቸው ነው

ሚያዚያ ፲፫ (አስራ ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢሳት ያነጋገራቸው በአዊ ዞን የሚኖሩ የመኢአድ አባላት እንደተናገሩት የመንግስት ታጣቂዎች ኢህአዴግ አባላት ለመሆን ፈቃደኛያልሆኑ የፓርቲውን አባላት እያሳደዱና ድብደባ እየፈጸሙባቸው ነው።

አቶ ዘሪሁን ባንቲሁን የተባለው አርሶ አደር ለኢሳት እንደገለጹት ሁለት መለዮ የለበሱ ታጣቂዎች ምሽት ላይ ቤታቸውን አስከፍተው በፈጸሙባቸው ድበደባ ለከፍተኛ አካል ጉዳት ተዳርገዋል።

ሌሎች የመኢአድ አባላትም እንዲሁ የገዢው ፓርቲ አባላት ካልሆናችሁ በሚል ተመሳሳይ ድብደባና ማዋከብ ደርሶባቸዋል።

ገዢው ፓርቲ መጪውን ምርጫ በተመለከተ ካሰፈራቸው የማሸነፊያ ስትራቴጂዎች መካከል አንዱ የተቃዋሚ ድርጅት መሪዎችን አሳምኖ  ወደ ፓርቲው ማምጣትና በተቃዋሚ ስም በምርጫ እንዲወዳደሩ ማድረግ እንዲሁም ይህን መመሪያ ለመቀበል ፈቃደና ባልሆኑት ላይ ደግሞ ከማንኳስስ ጀምሮ ያሉ እርምጃዎች እንዲወሰዱ ኢሳት ሰሞኑን ይፋ ባደረገው የኢህአዴግ የምርጫ ስትራቴጂ መግለጹ ይታወቃል።

በጉዳዩ ላይ የአዊ ዞን የፖሊስ ጽህፈት ቤትን ለማነገጋር ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።