ጥቅምት ፴(ሠላሳ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ለደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫኪር ታማኝ የሆኑ የደህንነቶች ሰራተኞች ለኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የጦር መሳሪያ እና ሌሎች እቃዎችን ጭነው ሲጓዙ የነበሩ 4 መኪኖችን አስቁመዋል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቃል አቀባይ ስቴቨን ዱጃሪክ እንደገለጹት የደህንነት ሰራተኞች መሳሪያዎቹ ለአንድ ተቃዋሚ ሃይል ሊሰጥ ነው በሚል እንደያዙትና በሹፌሮቹ ላይ ጉዳት እንዳደረሱባቸው ገልጸዋል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቃል አቀባይ መኪኖቹ በአስቸኳይ እንዲለቀቁ ...
Read More »Author Archives: Central
ኢህአዴግ በሚያካሂደው የፖለቲካ ስልጠና ላይ ህዝቡ ቅሬታዎችን እያሰማ ነው
ጥቅምት ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በየስብሰባዎቹ የተሳተፉ ምንጮች ለዘጋቢያችን እንደተናገሩት በየመድረኩ የጋዜጠኞች መታሰር፣ የሃይማኖት እኩልነትና ነጻነት አለመከበር፣ የመልካም አስተዳደር ችግሮች መባባስ፣የሙስናና ብልሹ አሠራር መንሰራፋት፣ የህወሃት የበላይነት መኖር፣ የድህነት መንሰራፋትና የዋጋ ግሽበት አለመቀረፍ፣ በተቃዋሚ ፓርቲዎች ላይ ወከባና እስር መጠናከር በተደጋሚሚ የሚነሱና ኢህአዴግ በቂ ምላሽ ሊሰጥባቸው ያልቻለባቸው አበይት ጉዳዮች መሆናቸው ታውቆአል፡፡ ጥያቄዎቹ በተለይ በግንባሩ አባላትና በካድሬዎች ጭምር የሚነሱ ...
Read More »በኢትዮጵያ ውስጥ የተፈጸሙና የሚፈጸሙ ወንጀሎችን መረጃ የሚይዝ መረጃ ፍትህ ማእከል የተባለ ድረገጽ ይፋ ሆነ
ጥቅምት ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የድረገጹ አዘጋጆች ለኢሳት በላኩት መግለጫ እንደጠቀሱት ድረገጹ በኢትዮጵያ ውስጥ ወንጀሎችን ያቀዱ፣ ለወንጀሎቹ ውሳኔ የሰጡ፣ ወሳኔዎችን ያስፈጸሙ፣ የመሩና ያቀነባበሩትን በሰሜን አሜሪካ፣ በአውሮፓ እንዲሁም በየትኛውም የምእራብ ሀገሮች እንደ የሀገሮቹ የህግ አግባብ መሰረት ክስ ለመመሥረት የሚያስችሉ ልዩ ልዩ መረጃዎችንና ምስክሮችን ማሰባሰብ እና ማጠናቀር አላማ አድርጓል። ወንጀል በፈጸሙት ላይ በቂ መረጃዎች ከተሰበሰቡ በኋላ ህግ ፊት ...
Read More »ከአባይ ግድብ ስራ ጋር በተያያዘ በተወሰኑ የህወሃት ደጋፊዎች ከፍተኛ የደን ጭፍጨፋ እና ምዝበራ እየተካሄደ ነው
ጥቅምት ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአባይ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት እቅድ እንደሚያሳየው ግድቡ ሲጠናቀቅ 1600 ኪሎሜትር ስኩየር መሬት የሚሸፍን ውሃ የሚተኛበት ሲሆን፣ የዚህ መሬት አካል 90 በመቶው በደን የተሸፈነነ ነው። በኢትዮጵያ ውስጥ አንጻራዊ በሆነ መልኩ የተሻለ የደን ሽፋን አለው የሚባለው ግድቡ የሚሰራበት የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ቢሆንም፣ ከ200 ኪሎ ሜትር ያላነሰ ስፋት ያለው የክልሉ ደን በፍጥነት እየተጨፈጨፈ ነው። ...
Read More »የደህንነት ሃይሎች ዜጎችን እያፈኑ መውሰዱን ቀጥለውበታል
ጥቅምት ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰሞኑን ተጠናክሮ የቀጠለው የገዢው ፓርቲ አፈና መንግስት ራሱ ያስታጠቃቸውን ታጣቂዎች ትጥቅ እስከማስፈታት መድረሱን ምንጮች ገለጹ በትግራይና በአማራ ክልሎች ባለፉት ሶስት ቀናት ሲካሄድ የነበረው አፈና ቀጥሎ ጥቅምት 26 ቀን 2007 ኣም የሰላም ታጋይ እየጠባለ የሚታወቅ ወጣት ሽሻይ አዘናው በመቀሌ ከተማ በትግራይ ክልል የፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ገ/ህይወት ካህሳይ እና በደህንነት ሃይሎች ከሚሰራበት የኢትዮጵያ ...
Read More »የኢህአዴግ መንግስት ከአረብ ሃገራት ጋር በአሰሪና ሰራተኛ ግንኙነት ላይ ሊያደርገው ያሰበው ስምምነት በአረብ ሃገራት መሪዎች ተቀባይነት ማጣቱ ታወቀ
ጥቅምት ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰሞኑን በጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ በኢትዮጵያ እና በአረብ ሀገራት መካከል ያለውን ግንኙነት እንዲሁም መንግስት ወደ አረብ አገራት በሚላኩ ዜጎች ጉዳይ ሊፈጽመው ያሰበው ስምምነት ምን ደረጃ ላይ እንደደረሰ ግምገማ ተካሂዶ ነበር። መንግስት ተጓዝ ሰራተኞችን በሚመለከተ ያወጣው ህግ በአረብ መንግስታት እውቅና የተነፈገው ሲሆን፣ የአረብ አገራት ባለስልጣናት ኢትዮጵያውያን ሰራተኞች የሙያ ክህሎት የላቸውም፣ በአገሪቱ ...
Read More »በደብረማርቆስ ዩኒቨርስቲ ውሃ መጥፋቱን ተማሪዎች ተናገሩ
ጥቅምት ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በዩኒቨርስቲው ውስጥ በሚታየው ተደጋጋሚ የሃይል መቆራረጥና የውሃ እጥረት ተማሪዎች ትምህርታቸውን በአግባቡ ለመከታተል አልቻሉም። ከውሃ እጥረት ጋር በተያያዘ ከጽዳት ጋር ለተያያዙ በሽታዎች ሊደራጉ እንደሚችሉ ተማሪዎች ፍርሃታቸውን ገልጸዋል።
Read More »በቅርቡ በጋምቤላ ተከስቶ በነበረው ግጭት የሞቱ ሰዎች ስም ዝርዝር ይፋ ሆነ
ጥቅምት ፳፭ (ሃያ አምት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የቀድሞው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባዔ የአሁኑ የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ( ሰመጉ) ባወጣው 132ኛ ልዩ መግለጫ በክልሉ በመንገሽና ጎደሬ ወረዳዎች ተፈጥሮ በነበረው ግጭት የተገደሉ የ60 ሰዎች ስም ዝርዝር ይፋ አድርጓል። በሪፖርቱ እንደቀረበው 27 የአማራ፣ 27 የመዠንገር፣ 2 የከፋና 4 የኦሮሞ ተወላጆች ተገድለዋል። እንዲሁም 16 የአማራና 6 የመዠንገር ተወላጆች የአካል ጉዳት ሲደርስባቸው፣ 36 የአማራ ...
Read More »መንግስት የተቃዋሚ መሪዎችን እያደነ ማሰሩን ቀጥሎአል
ጥቅምት ፳፭ (ሃያ አምት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ካለፉት ሁለት ቀናት ጀምሮ መንግስት በተለያዩ አካባቢዎች ያሉ የተቃዋሚ አመራሮችን በመያዝ እያሰረ ነው:: በትግራይ ክልል በምዕራባዊያን ዞን ቃፍታ ሁመራ ወረዳ ዳንሻ ከተማ የአረና ፓርቲ የማእከላዊ ኮሚቴ አባል አቶ ዘነበ ሲሳይ ጥቅምት 25፣ 2007 ዓም ከቤታቸው ተነጥለው በመወሰድ ሲታሰሩ፣ በተመሳሳይ ቀን በሁመራ የአረና የቁጥጥር ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ አማረ ተወልደ ታስረዋል። ከወራት ...
Read More »በነ ወርቅነህ አገኘሁ መዝገብ ብይን ለመስጠት የተያዘው ቀጠሮ ተራዘመ
ጥቅምት ፳፭ (ሃያ አምት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፌዴራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ክስ በመሰረተባቸው አቶ ዘላለም ወርቅነህ፣ ሃብታሙ አያሌው፣ አብርሃ ደስታ ፣ ዳንኤል ሺበሺ፣ የሽዋስ አሰፋና በሌሎች 5 ተካሳሾች ላይ ዋስትናን በተመለከተ ሊሰጥ የነበረውን ውሳኔ አራዘመ። ፍርድ ቤቱ የሁሉም ጠበቆች ተዘጋጅተው ባለመቅረባቸው ውሳኔውን ለህዳር 2 ፣ 2007 ማራዘሙን አስታውቋል። እስረኞቹ በሽብር ወንጀል ተከሰው ለወራት በእስር እየተሰቃዩ ...
Read More »