በኢትዮጵያ ውስጥ የተፈጸሙና የሚፈጸሙ ወንጀሎችን መረጃ የሚይዝ መረጃ ፍትህ ማእከል የተባለ ድረገጽ ይፋ ሆነ

ጥቅምት (ሃያ ሰባ) ቀን ፳፻፯ / ኢሳት ዜና :-የድረገጹ አዘጋጆች ለኢሳት በላኩት መግለጫ እንደጠቀሱት ድረገጹ በኢትዮጵያ ውስጥ ወንጀሎችን ያቀዱ፣ ለወንጀሎቹ ውሳኔ የሰጡ፣ ወሳኔዎችን ያስፈጸሙ፣ የመሩና ያቀነባበሩትን በሰሜን አሜሪካ፣ በአውሮፓ እንዲሁም በየትኛውም የምእራብ ሀገሮች እንደ የሀገሮቹ

የህግ አግባብ መሰረት ክስ ለመመሥረት የሚያስችሉ ልዩ ልዩ መረጃዎችንና ምስክሮችን ማሰባሰብ እና ማጠናቀር አላማ አድርጓል።

ወንጀል በፈጸሙት ላይ በቂ መረጃዎች ከተሰበሰቡ በኋላ ህግ ፊት የማቅረብ በተለይም ወንጀል ፈጻሚዎቹ በምዕራብ አገሮች መሸሸጊያ እንዲሁም የመኖሪያ ፈቃድ እንዳያገኙ እና ያሸሹት ገንዘብም ሆነ የገዙትን ንብረት ለማሳገድ እንቅስቃሴ እንደላቸው አዘጋጆች በመግለጫቸው ጠቅሰዋል።

ድረገጹ የሚያሰባስባቸውና መዝግቦ የሚይዛቸው የወንጀል አይነቶች  የሰብዓዊ መብት ረገጣ ፣የዘር ማጥፋት ወንጀል፣ የጦር ወንጀል፣ የጅምላ ግድያዎች፤ አስገድዶ መድፈር፣ አሰቃቂ ድብደባና ሰቆቃ መሆናቸው በመግለጫው ተመልክቷል።

ህዝቡ የሕወሓትና የኢሕአዴግ የሲቪል ከፍተኛ ባለሥልጣኖችና ውሳኔ ሰጭዎች፣ የሕወሓት/ኢሕአዴግ የደህንነት፣ ወታደራዊና የፌዴራል ፓሊስ ከፍተኛ ኃላፊዎች፣አዛዦችና ውሳኔ ሰጭዎች፣ በየእርከኑ የሚገኙ የሕወሓት/ኢሕአዴግ የመከላከያ አዛዦች፣የደህንነት የፌዲራል ፓሊስ ውሳኔ አስፈጽሚዎች፣ ውሳኔ

ፈጻሚዎች፣ ሰቆቃ ፈጻሚና ገራፊ መርማሪዎች፣ በዜጎች ላይ በግፍ የፈረዱ፣ከወንጀለኞች የተባበሩና በየእርከኑ የሚገኙ የፌደራልና የከፍተኛ ፍርድቤት ዳኞችና አቃብያነ ህግ እንዲሁም በየክልሉ በየደረጃው የሚገኙ የፌደራልና የክልል ፖሊስ አዛዦች፣ የልዩ ሃይል አዛዦች፣የፖሊስ መሪማሪዎች፣ በየክልሉ የሚገኙ

የደህንነት ሃላፊዎች፣ ቁልፍ የደህንነት አባላት፣የየክልሉ ሚሊሽያ አዛዦችና በተዋረድ የሚገኙ ሹሞች፣  በየእርከኑ የሚገኙና በግፍ በዜጎች ላይ ፍርድ በመስጠት ንጹሃን ዜጎችን ያጠቁና ያስጠቁ ዳኞችና አቃብያነ ህግ፣ በተለያዩ የሃገሪቱ የአስተዳደር ክልሎች ከየማዘጋጃ ቤቱ ህጋዊ የቤት ባለቤትነት ይዞታና የካርታ

ማስረጃዎችን አሰርቀው በማውጣት የተጭበረበረ ሰነዶችን እያቀረቡ የህዝብን ንብረት የወሰዱና ለዚህም ተግባራቸው የተባበሯቸውን ግለስቦች ማንነት መዝግቦ መያዝና ማገለጥ እንደሚኖርበት በመግለጫው ላይ ሰፍሯል።

በተለያዩ የመንግስት መስሪያቤቶች ከህጋዊ ጨረታ ውጪ በአገር ውስጥና በውጪ አገር ከሚገኙ ኩባንያዎች ጋር በመመሳጠር በኰሚሽንና በሃሰት በተዘጋጀ የሰነድ ማስረጃ በርካታ ገንዘብ የዘረፉ ግለሰቦች ማንነትና ዝርዝር የወንጀል ድርጊቶች፣ ከአገር ወደ ውጪ፣ከውጪ ወደ አገር ውስጥ የሚገቡ ሸቀጦች ከቀረጥ ነፃ

ሆነው እንዲገቡና እንዲወጡ በማድረግ በአየር ለአየር ንግድ የከበሩና ህጋዊ የንግድ ድርጅቶችን በማዘጋት የግል ሃብትና ንብረት እየዘረፉ የሚገኙ ሰዎችን ማንነትና አድራጐት በዝርዝር መያዝ አስፈላጊ መሆኑንም ጠቅሷል።

በኢትዮጵያ ውስጥ ቤተሰብ ዘመድ በአገዛዙ የተገደሉባችው፣ አሰቃቂ ድብደባ ፣ሰቆቃ የተፈጸመባችው፤በየጊዜው ስለ ተፈፀሙ ልዩ ልዩ መንግስታዊ ወንጀሎች፣ ግፍ፣ ግድያ፣ ሰቆቃ፣አድራጊዎችና ፈጻሚዎች ማንነት የሚያውቁ፣ ቤተሰብ፣ ዘመድ አዝማድ፣ ጓደኛ የደረሱበትን የማያውቁ፣ ወንጀሎች የት፣ በማን፣ መቼ

እንደተፈጸሙ የሚያውቁ፣ እማኝ የሆኑ፣ ወንጀሎችን በሚመለክት ያዩ፣የሰሙ ግለሰቦችን የሚያውቁ፤ ስለወንጀሎቹ ዝርዝርና ሰለ አድራጊዎቹ ማንነት የሚያውቁ መረጃዎችን ለማዕከሉ በመስጠት እንዲተባበሩ ጥሪ ቀርቧል።

የመረጃ ፍትህ ማእከል በሰብአዊ መብት ተሟጋቾችና በህግ ባለሙያዎች የተቋቋመ ሲሆን እስካሁን የ73 ተፈላጊ የሲቪል፣ ወታደራዊና የደህነት ሰዎችን ስም ዝርዝር አዘጋጅቷል። ተጨማሪ ተፈላጊዎችን ስም ለማዘጋጀት ከህብረተሰቡ ጋር በመተባባር እንደሚሰራም ገልጿል። መረጃ ለመስጠት የሚፈልጉ

editor@masreja.com ወይም በስልክ ቁጥር 1 ( 800) 3851804 መጠቀም ይችላሉ።